
17/06/2025
ድሬዳዋ ከተማ ስሑል ሽረን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ወጣ
በ35ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ከስሁል ሽረ የተጫወተው ድሬዳዋ ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ የመቆየት ዕድሉን አስፍቷል፡፡ 9 ሰአት በወንጂ ሁለገብ ስቴዲየም ያደረገውን ጨዋታ 4 ለ 2 አሸንፏል፡፡
መስዑድ መሀመድ የድሬዳዋ ከተማን ሁለት ግበች ሲያስቆጥር ዩኋንስ ደረጄ እና ሀቢብ ከማል ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ብርሀኑ አዳሙ እና አላዛር ሽመለስ ከፕሪሚየር ሊጉ ቀድሞ መውረዱን ላረጋገጠው ስሑል ሽረ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
ሊጠናቀቅ አንድ ጨዋታ ብቻ በቀረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ከነበረበት 15ኛ ደረጃ ወደ 12ኛ ከፍ ብሏል፡፡
አራት ክለቦች ከሊጉ በሚወርዱበት አመት አዳማ ከተማ፣ መቐለ ሰባእንደርታ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ፋሲል ከነማ መቆየታቸውን ለማረጋገጥ የመጨረሻውን ሳምንት ለመጠበቅ የተገደዱ ናቸው፡፡
በአንተነህ ሲሳይ