
29/05/2025
ቱለማውን ከመሬቱም ከፖለቲካውም ያባረሩት የጅማ ባለጊዜዎች ጉድ‼️
የብልፅግና መንግስት ሁሉንም የሀገሪቱን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መዋቅሮች በራሱ ሰዎች ቁጥጥር አስገብቶ ረጅም አመታት የመግዛት ሕልም እንዳለው ይታወቃል።
ይህንን ሕልሙን ለማሳካት ደግሞ የኔ ታማኝ የሚላቸውን፤ የብሄሬ ሰዎች የሚላቸውን፤ የሰፈሬ ሰዎች የሚላቸውን ሰዎች መልምሎ በየጊዜውም እየመለመለ ጠንካራ የባለጊዜዎች ሰንሰለት ፈጥሯል። የዚህ ሰንሰለት ኮር ደግሞ የጅማ ሰዎች ናቸው። ከጅማ ደግሞ የጎማ እና የአጋሮ አከባቢ ሰዎች ቀዳሚዎቹ ናቸው። ለባለጊዜዎቹም ባለጊዜ አሏቸው።
ከእነዚህ የጅማ ስኳድ ተብለው ከሚታወቁት ባለጊዜዎች መካከል አንድ ሰው እናስተዋውቃችሁ።
አቶ መኪዮ መሃመድ ይባላሉ። እኝህ ሰው የሀገሪቱን ዋና ዋና ኢኮኖሚ እንዲቆጣጠሩ በቀጥታ በአብይ አህመድ ተሹመው በሀላፊነት እየሰሩ ካሉ ሰዎች መካከል እንደሆኑ አስምራችሁ ያዙ።
አቶ መኪዮ መሃመድ በኢህአዴግ ግዜ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የኢህአዴግ አደራጅ ሆኖ አገልግሏል። ቀጥሎ ደግሞ በአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትርነት ዘመን ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ውስጥ ሰርተዋል።
ቀጥሎ ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 የጅማ ከተማ ከንቲባ ሆነው ከሰሩ በኋላ ከእነ ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ እና ፍቃዱ ተሰማ ጋራ ተጋጭተው ከጅማ ከተማ ከንቲባነት ተነስተው ለአጭር ግዜ የኦሮሚያ ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኋላፊ ሆነው ሰርተዋል። ለአራት ወራት አከባቢ በዚህ ቦታ ላይ ከቆዩ በኃላ ከአመራርነት በእነ ሽመልስ ጫና ተባረሩ።
ከዛ በኃላ መኪዮ ከኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ቢሮ መባረራቸውን አንድ ቶፊቅ በሚባል የጠቅላይ ሚንስትሩ አጃቢ በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደረሳቸው።ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይህን እንደሰሙ መኪዮን በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት የደህንነት ጉዳዮችን አማካሪ ድኤታ አድርገው ሾሙት።
በነገራችን ላይ መኪዮ እና ዶር ዶ/ር አብይ በጅማ ውስጥ የአንድ አከባቢ፣ ማለትም አሁን ተደራጅቶ በባለግዜነት ስሜት የሀገሪቱን ሃብት እየዘረፉ ካሉ የጎማ እና አጋሮ አከባቢ ሰዎች ናቸው።
መኪዮ የጠሚው የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ድኤታ ሆነው ከተሾሙ ጀምሮ የጅማ አከባቢ ሰዎች በተለያዩ ወሳኝ የስልጣን እና ጥቅም ቦታዎች እንደ ጉምሩክ እና ደህንነት ቢሮዎችና በመሳሰሉት በብዛት እንዲሰገሰጉ አደረጉ። እንዲሁም ሌሎች የአከባቢው ወጣቶች ምንም አይነት የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ ሳይኖራቸው የግንባታ ፈቃድ እንዲያገኙ በማድረግ የህዳሴን ግድብ ፕሮጀክት ጨምሮ፣ ዶር አብይ የሚያስገነባቸው የተለያዩ ሪዞርቶች እና ቤተ መንግስት እንዲሁም በከፍተኛ በጀት የተለያዩ ከተሞች ውስጥ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ግንባታ ላይ ያለ ጫረታ እንዲወስዱ አድርገዋል።
ከእዚህ ውጪ በዚህ ሂደት በርካታ የጅማ ሰዎች እነ መኪዮ በዘረጉት የባለግዜ ኔትዎርክ የቡና ኤክስፖርት፣ የኤሌክትሪክ መኪና ጨምሮ አዋጭ ናቸው የሚባለው እቃዎች ኢምፖርት ላይ በስፋት እንዲሰማሩ አድርጓል።
ከጅማ አከባቢ ተወላጆችን ሃብታም ከማድረግ ባለፈ ከመኪዮ ጋር የተለየ ቀረቤታ ያላቸው ሰዎች ሃብት ላይ ሃብት እንዲደርቡ እያደረገ ነው። ለምሳሌ መኪዮን የሚያውቁ ብዙ ሰዎች እንደሚሉት የማማ ወተት ባለቤት የሆነችው ወ/ሮ ሰሃራ አህመድ ከአቶ መኪዮ ጋር ባላት ቅርርብ ምክንያት ነው የጫት Export ላይ በስፋት እየተሳተፈች ያለችው።
በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር ድኤታ ስልጣኑን በመጠቀም በባልግዜ ስሜት ይሄንን እና ሌሎች ህገወጥ ስራዎችን ሲያደርግ የነበረው አቶ መኪዮ መሃመድ በአሁኑ ግዜ በባህል እና ስፖርት ሚንስትር የስፖርት ዘርፍ ሚንስትር ድኤታ ሆኖ በቅርቡ በጠቅላይ ሚንስትሩ ሌላ ሹመት ተሰጥቶታል።
በኦህዴድ ብልፅግና ውስጥ በመጀመሪያ ጠ/ሚው ለወንበሩ ማስጠበቂያ እንደ ተገን አድርጎ ሲጠቀመው የነበረው የሸዋን መዋቅር ነበር:: በጊዜ ሂደት ግን የሰፈሩን እና የጅማ ሰዎችን ብቻ በዙሪያው በመሰብሰብ ተገን አድርጎ አደራጅቷል:: ይህ ደግሞ የሸዋን መዋቅር በሚዘውሩት እነ ኦቦ ሽመልስ ዘንድ በሌላ ልንተካ ነው የሚል ስጋትን ፈጥሯል:: ከዚህም አልፎ ኢኮኖሚካሊ አዋጭ የሆነው የቱለማ/ሸዋ መሬት ላይ የጅማው ስኳድ አዛዥ ናዛዥ ሆኖ መቀመጡ ውስጥ ውስጡን እያባላቸው ያለ ጉዳይ ሆኗል::
ቱለማው ንቃ❗️ ሸዋ ወጥር❗️ አለበለዚያ ሳያጠፉህ አይተኙልህም❗️