15/05/2025
እንኳን ደስ አላችሁ የማክሮ- ኢኮኖሚ ማሻሻያ አድርገናል ከተባለ ጊዜ ጀምሮ ...
* ኢትዮ-ቴሌኮም ከፍተኛ የታሪፍ ማሻሻያ ጭማሪ አደረገ
* መብራት ሃይል ሶስት እጥፍ የዋጋ ጭማሪ አደረገ
* የውሃ አገልግሎት የክፍያ ታሪፉን እላይ ሰቀለው
* የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአገልግሎት ተጨማሪ እሴት ታክስ ማስከፈል ጀመረ
* ነዳጅ በሊትር በየወሩ ከሃያና ከአስር ብር በላይ ይጨምራል
* የትኛውም የመንግስት አገልግሎቶች እንደ ቀልድ የሚጨምሩት ክፍያ የማይቀመስ ሆነ
* መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች ሆነ የትኛውም ምርት በየቀኑ የዋጋ ተመናቸው ከፍ እያለ አስቸገረ .
* ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በየወሩ ከእጥፍ በላይ ይጨምራሉ
* አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሰው ኪስ መግባት እስኪቀራቸው ድረስ ህብረተሰቡን አማረሩ ..
* መንግስት በታክስ ሀንግ መስራት ጀመረ ... ወዘተረፈ
ነገር ግን የሰራተኛው ደሞዝ ባለበት ደርቋል። ደሞዝ ቢጨመርም እንኳን ለአንድ ቀን ምሳ የማትበቃ 700 ብር ጠብ ትደረጋለች። የገንዘባችን የመግዛት አቅም ተመናምኖ እርቃኑን ቀርቷል። ህዝቡ በተአምርና በአስማት ሌላውን ነገር ትቶ ትንፋሹን ለማስቀጠል ብቻ ህይወቱን ይገፋል።
በጎን በኩል ደግሞ ሚዲያው ፣ ካድሬው ፣ የገፅታ ግንባታ ባለሞያው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መላው አለም እየተደመመበት እንደሆነ ይነግሩናል። አስፓልት ፣ መብራት ፣ ዘንባባ በባዶ ሆዶችሁ እያያችሁ ተደመሙ ይሉናል።
የኢኮኖሚ እድገት ማለት .. በየቀኑ የሚጨምር የዋጋ ንረት እንደሆነ አስበው ነው መሰለኝ ... የሸቀጦች ፣ የአገልግሎት ዋጋ በጨመረ ቁጥር የኢኮኖሚ እድገቱን ቁጥር እየጨመሩ በአውራው መንግስታቸው ተደመሙ።
እኛ ኢትዮጵያ የምናላት ሀገር ... ለእነሱ ኖርዌይ ሆና ትታያለች። እኛ ግን የተወደደውን ኑሮዬን እንጂ የካድሬውን ኖርዌይ አናውቅም 😃 !!