
08/06/2024
ቢትዬ በሕይወት እስካለሽና በሕይወት እስካለሁ ድረስ ላንቺ መደረግ ያለበትን ሁሉ አደርጋለሁ። አንድም ቀን እንደ ልጆች ተጫዉተሽ; ቦረቀሽ ሳታውቂ ይኸው ድፍን ስድስት አመት ቆዘምሽ። አባትሽንና እናትሽን አባ; እማ ብለሽ ሳትጠሪ; ከወንድምሽና ከእህትሽ ሳትጫወቺ; የጠፈጠሽንና የወደድሽውን ምግብ መርጠሽ ሳትበይ; ውሃ ጠማኝ; ሽንቴ መጣ;... ሳትይ አመታት ነጎዱ።ትምህርት ቤት ብትገቢ ኖሮ በዚህ ሰኔ ከኬጂ ትመረቂ ነበር። ስድስት ጊዜ ልደትሽ ስናከብርልሽ Happy Birthday ብለሽ ሳትዘምርና ሳትደሰቺ... በቃ... ከሥራ ተመልሼ ወደ ቤት ሲገባ በአልጋ ተኝተሽ እጄን ጥብቅ አርገሽ አይን አይኔን ሲታይኝ የማደርገው ይጠፋኛል። ምን እያልሽኝ እንደሆነ አይገባኝም። ቢቲዬ ምን ላድርግ?... በምን ቋንቋ ፍላጎትሽን ልረዳ? የኔ ሕይወት ተቋርጦ ያንቺ ይጀመራል ቢባል ደስ ባለኝ። ተስፋ... ከቀን ወደ ቀን እየራቀን መጣ። የምችላቸው ነገሮች የማልችላቸው ሆኑ። የማውቃቸው ነገሮች የማላውቃቸው ሆኑ። እስከ ዛሬ ብቻችንን ሞክረናል። አሁን ደግሞ በአደባባይ በሕዝብ ፊት እንሞክረው። ላንቺ ይሆናል የተባለውን ሁሉ ከመሞከር ወደኋላ አንልም።
Help 6-Year-Old Bithia Get the Care and Support She Needs Bith… Amanuel Tadesse Heboto needs your support for Support Bithia's Journey Towards Better Care