Ethio News Tube

Ethio News Tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio News Tube, Media/News Company, Addis Ababa.

የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ*********************ክቡራን ደንበኞቻች፡የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የክፍያ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል። የተሻሻለውን የ...
18/11/2023

የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ
*********************

ክቡራን ደንበኞቻች፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የክፍያ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል።

የተሻሻለውን የአገልግሎት ክፍያ በተመለከት ከደንበኞቻችን ባገኘነው ግብረ መልስ መሠረት በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ድጋሚ የክፍያ ማሻሻያዎች አድርገናል፡፡

በድጋሚ ማሻሻያ የተደረገባቸው አገልግሎቶች እና የተሻሻለው ክፍያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡

1. በወዲአህ በተከፈቱ ሂሳቦች በቅርንጫፍም ሆነ በሞባይል ባንኪንግ የሚደረግ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አግልግሎት ከክፍያ ነፃ ነው፤
2. በሙዳራባህ ውል የተከፈቱና እና ለረጅም ጊዜ ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦች (Inactive Accounts) ከክፍያ ነፃ ናቸው፤
3. በቅርንጫፍ የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 10,000 - ብር 5
• ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 - ብር 10
• ከብር 100,001 በላይ - ብር 10 ሲደመር በእያንዳንዱ 100 ሺ 5 ብር (ከ100 ብር ያልበለጠ)

4. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሌላ ደንበኛ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 50,000 - ነፃ
• ከብር 50,001 እስከ ብር 100,000 - ብር 5
• ከብር 100,001 እስከ ብር 200,000 - ብር 10
• ከብር 200,001 እስከ ብር 300,000 - ብር 15
• ከብር 300,001 በላይ - ብር 20

5. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ሌላ ባንክ ወደሚገኝ ሂሳብ ገንዘብ ለማስተላለፍ (RTGS) ብር 50 የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፤
6. ከ P2P የገንዘብ ዝውውር በ ኢትስዊች (ETSWITCH) 5 ብር እና የኢትስዊች ክፍያን በመደመር የአገልግሎት ክፍያ ይከፈልበታል፤
7. ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ ከ50 ብር በታች ለማስገባት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ የለም፤
8. በሲቢኢ ብር በቀን ከ3 ጊዜ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ሲኖር ገንዘብ የማስገባት አገልግሎት እንደሚከተለው የአገልግሎት ክፍያ ይታሰብበታል፡

• ከብር 50 በታች - ነፃ
• ከብር 51 እስከ ብር 500 - ብር 6.45
• ከብር 501 እስከ ብር 2,000 - ብር 7.60
• ከብር 2,001 እስከ ብር 3,000 - ብር 8.18
• ከብር 3,001 እስከ ብር 4,000 - ብር 9.33
• ከብር 4,001 እስከ ብር 5,000 - ብር 10.48
• ከብር 5,001 እስከ ብር 6,000 - ብር 11.63
• ከብር 6,001 በላይ - የሚገባው ገንዘብ 0.2 በመቶ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

"የኢትዮጵያን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" "የኢትዮጵያውን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" ያሉት...
16/11/2023

"የኢትዮጵያን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ"

"የኢትዮጵያውን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" ያሉት በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ኢሳቅ አህመድ ሀሰን በሶማሊያ ሶሻል ሚዲያዎች የእለቱ ሳቅ የሚጭር መነጋገሪያ ሆኗል ሲል ሶማሊ ፈጣን መረጃ ዘገባ ያሳያል።

ሰውዬው በሶሻል ሚዲያ ብቅ ብለው በአፍ ሶማሊ ቋንቋ "አብይን ትመስላለህ እያሉ ህይወቴን አደጋ ውስጥ የከተቱብኝ ሰዎች አሉ። እኔ ሳልሆን አብይ ነው እኔን የሚመሰለው። በዚህ ምክንያት ለህይወቴ ሰለሰጋሁ ያለጠባቂ መንቀሳቀስ አቁሜለሁ። በዛ ላይ የአባቱ እና አባቴ ስም አንድ ነው። ወደ ኢትዮጵያ የሄድኩት በመለስ ዘመን ነው አሁን መሄድ ብፈልግም ለደህንነቴ ስጋት ስላለብኝ ጠባቂ ያስፈልገኛል።" ብለዋል።

በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ይህን መልእክት ያስተላለፉት ለቀልድ ይሁን የምራቸውን ግን የታወቀ ነገር የለም ሲል ሶማሊ ፈጣን መረጃ ዘግቦታል።

በትጋት ህዝብን እያገለገልኩ ባለውበት ሆስፒታል አገር አቀፍ የህክምና ስፔሻሊቲ ፈተና ለመፈተን የድጋፍ ደብዳቤ እንዲፃፍልኝ ስጠይቅ እኔን የማይወክል የስራ ሞራሌን የሚነካ ደብዳቤ ተፅፎብኛል ...
14/11/2023

በትጋት ህዝብን እያገለገልኩ ባለውበት ሆስፒታል አገር አቀፍ የህክምና ስፔሻሊቲ ፈተና ለመፈተን የድጋፍ ደብዳቤ እንዲፃፍልኝ ስጠይቅ እኔን የማይወክል የስራ ሞራሌን የሚነካ ደብዳቤ ተፅፎብኛል ሲሉ ዶክተር ካላሌ ኮይርታ ገለፁ

እኔ ዶ/ር ካላሌ ኮይርታ ከጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል በዝውውር ከመጣሁበት ጊዜ (1/5/14 ዓ.ም) አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በካራት መ/ደ/ሆስፒታል በህክምና ሙያ ህብሬተሰቤን እያገለገልኩ እገኛለሁ።

ከዚህ በፊትም በመምህርነት ሙያዬም ለሦስት ተከታታይ አመታት ይህንኑ ህብረተሰብ በትጋትና በቅንነት ማገልገሌ የሥራ ባልደረቦቼ ህያው ምስክር ናቸው።

አሁንም ቢሆን ለወደፊትም ህብረተሰቤን በእውነትና በቅንነት ከማገልገል አልቆጠብም።

ይሁን እንጅ አሁን ለ2016 ዓ.ም በወጣው አገር አቀፍ የህክምና ስፔሻሊቲ ፈተና ምልመላ መስፈርት በሚጠይቀው የሆስፒታሉ የድጋፍ ደብዳቤ መሠረት ለጠየኩት ምላሽ የተሰጠኝ ደብዳቤ ይህ ነው። እኔ ግን እስከ አሁን በተመደብኩበት ቦታ ሁሉ በትጋት ከማገልገለም በላይ አንድም ጊዜ በሥራ ክፍተት ወይም ድካም ምክንያት ከዚህ በፊት የተሰጠኝ ማስጠንቀቅያ ወይም የተጻፈብኝ የዲስፕሊን ደብዳቤ ሳይኖር እንዲሁም ላለፉት 16 (አሥራ ስድስት) ወራት ለሠራተኞች ስላልተከፈለው የትርፍ ሰዓት ሥራ ክፍያን በተመለከተ ከሳምንት በፊት ባቀረብነው የመብት ጥያቄ ከዚህም በፊት በተደጋጋሚ በምናቀርበው አበቱታና ህጋዊ ጥያቄ ምክንያት ሆን ብለው በቂም-በቀል መንፈስ ይመስል አሁን እራሴ ለውድድር ድጋፍ ብዬ ለሚመለከተው አካል ባቀረብኩት ደብዳቤ ላይ በተጠቀሰው ተወካይ ኃላፊ ትዕዛዝ መሠረትና በሰው ሃብቱ አስተዳደርና ልማት ቡድን መሪ በጋራ እንድህ የሥራ ሞራሌን ልጎዳ በምችል መንገድ ተጽፎልኛል ብለዋል።

ሀሰተኛ ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች ተያዙ።ሀሰተኛ የውጪ ሀገራትና የኢትዮጵያን ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ሀሰተኛ...
09/11/2023

ሀሰተኛ ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች ተያዙ።

ሀሰተኛ የውጪ ሀገራትና የኢትዮጵያን ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሀሰተኛ ገንዘብ በማዘጋጀት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የተያዙት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ቦሌ አዲስ ትምህርት ቤት አካባቢ ነው።

የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሦስት ግለሰቦች ሙሉ ግቢ የመኖሪያ ቤት በመከራየት ሀሰተኛ ብር እና የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በማተም እንደሚያሰራጩ እና የከበሩ ማዕድናትን በህገ-ወጥ መንገድ እንደሚያዘዋውሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ባሰባሰበው ማስረጃ አረጋገጧል ፡፡

ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተደረገ ብርበራ ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘቦችን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን መሳሪያዎች ፣ ልዩ ልዩ ኬሚካሎችን ፣ በሀሰተኛ መንገድ የታተሙ ገንዘቦች ፣ በገንዘብ ልክ ተቆራርጠው የተዘጋጁ ወረቀቶችን እንዲሁም የዘንዶ ቆዳዎችን በኤግዚቢትነት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘብ ከማዘጋጀት በተጨማሪ የፀና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው እየኖሩ ያሉና በህገ-ወጥ መንገድ የከበሩ ማእድናትን እንደሚዘዋውሩ በምርመራ ማረጋገጡ ተጠቅሷል፡፡

ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ በተለያዩ ክ/ከተሞች ውስጥ በተመሳሳይ መንገድ ሀሰተኛ ገንዘቦችን ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች እንደተያዙ ፖሊስ አስታውሶ መሰል የወንጀል ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ በመሆኑ ወንጀሉን በመከላከል እና ህገ-ወጦችን ተጠያቂ የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ጃል ማሮ የተካፈለበት በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል በዳሬሰላም ሁለተኛው ዙር የሰላም ውይይት ተጀመረበፌደራል መንግስቱ እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በታንዛንያ...
09/11/2023

ጃል ማሮ የተካፈለበት በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል በዳሬሰላም ሁለተኛው ዙር የሰላም ውይይት ተጀመረ

በፌደራል መንግስቱ እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በታንዛንያ ዳሬሰላም ሁለተኛው ዙር የሰላም ውይይት ትላንት ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም መጀመሩን ጉዳዩን ከሚከታተሉ ሁለት ዲፕሎማቶች አዲስ ስታንዳርድ አረጋግጣለች።

በሰላም ውይይቱ ላይ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መሪ ኩምሳ ደሪባ በቅጽል ስሙ ጃል ማሮ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት ጃል ማሮ በሶስተኛ ወገን አደራዳሪዎች አመቻችነት በምዕራብ ኦሮምያ ከሚገኝ ጫካ ወደ አቅራቢያው ወደ ሚገኘው የደንቢዶሎ አየር ማረፊያ እንዲበር መደረጉን ጠቁመው ከዚያም ወደ ድርድሩ ቦታ በተዘጋጀለት ሄሎኮፕተር መጓዙን ተናግረዋል።

በዚህም ሂደት ጃል ማሮ ለመጀመሪያ ግዜ ከፌደራል መንግስቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ፊት ለፊት ለመገናኘት መቻሉንም አመላክተዋል ሲል አዲስ ስታንዳርድ ነው የዘገበው።

ምክር ቤቱ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአገራዊ...
08/11/2023

ምክር ቤቱ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያደምጥ ሲሆን፤ የግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።

በተጨማሪም የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲሁም የልዩ ኢኮኖሚ ዞን ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ የምክር ቤቱ መረጃ ያሳያል።

ወላጆች ጥንቃቄ⚠️⚠️⚠️ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቲክ ቶክ የሚባል አፕ ከመጣ በኃላ በሀገራችን ብዙ ወጣቶች ለገንዘብ ና ለfollow ብለው * ከባህል * ከእምነት ያፈነገጡ ነገር ማደረጉን ተያይዘው...
05/11/2023

ወላጆች ጥንቃቄ⚠️⚠️⚠️

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቲክ ቶክ የሚባል አፕ ከመጣ በኃላ በሀገራችን ብዙ ወጣቶች

ለገንዘብ ና ለfollow ብለው

* ከባህል
* ከእምነት

ያፈነገጡ ነገር ማደረጉን ተያይዘውታል

እነዚህ ሁለት ትንንሽ ልጆች ልብሳቸውን እንኳን በደንብ መልበስ የማይችሉ ልጆች

በቀጥታ ስርጭት

* ከንፈሬን ሳመኝ
* እንደዚህ አድርገኝ
* እንደዚህ አድርጊኝ
እያሉ ሲለቁ

ተከታታዮቻቸው ደሞ እንደነሱ ትንንሽ ልጆች ስለሆኑ

ወላጆች በተቻላችሁ መጠን እነዚህ ልጆችን የሚከተሉ ልጆች ካላችሁ አሁኑኑ ከስልካችው ላይ unfollow አስደርጏቸው

እነዚህ ልጆች የውስጥ ብታንታ እንኳን በደንብ መልበስ ሳይችሉ ዘመኑ ባመጣው ቴክኖሎጂ የሚከተሏቸውን ትንንሽ ልጆችን ጥሩ ትምህርት ማስተማር ሲገባቸው እነሱ ግን ብልግና ና እዚህ ግባ የማይባል ነገር እያሰተማሩ ስለሆነ

ወላጆች ለፍታችሁ ልጆቻችሁ አስድጋችሁ በማንም ባለጌ ሰዎች ምክንያት ልጆቻችሁ እንዳይበላሹባችሁ ጥንቃቄ አድርጉ ⚠️

እንዲሁም ወላጆች ልጆቻችሁ በየቀኑ ስልክ ላይ የሚያዩትን ነገር ምን እንደሆነ ማወቅ ና መከታተል ግዴታም አለባችሁ 🛑

ነገ ጥሩ ደረጃ የሚደርስ እንዲሁም

* ሀገሩንና ቤተሰቡን የሚያኮራ
ስነምግባር ያለው ልጆች አሳድጉ

⚠️⚠️⚠️

🌴🌴🌴

«ኢትዮጵያ የባህር በር የግድ ያስፈልጋታል» ጠ/ሚ አብይ አህመድ  news «የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ ስለሆነ ኢትዮጵያ አሁን የግድ የባህር በር ያስፈልጋታል፣ ከዚህ ቀደም ኢትዮ...
15/10/2023

«ኢትዮጵያ የባህር በር የግድ ያስፈልጋታል» ጠ/ሚ አብይ አህመድ
news
«የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ ስለሆነ ኢትዮጵያ አሁን የግድ የባህር በር ያስፈልጋታል፣ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ የባህር በር እንደነበራት ታሪክ ይናገራል ስለዚህ እነዚህን የባህር በሮች በንግግር እና ውይይት ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ አለብን፣ ይህ ብቻ አይደለም በሰጥቶ መቀበል ከህዳሴ ግድብ፣ ከአየር መንገድ፣ ከቴሌ ድርሻ በመስጠት የባህር በር ድርሻ መውሰድን የመሳሰሉ አማራጮችን መጠቀም አለብን፣ በፍፁም ግን በጉልበት በጦርነት የባህር በር ይኑረን ብለን ጦር አንመዝም» ሲሉ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከጠብታ ውኃ እስከ ባህር ውኃ በተሰኘ ለፓርላማ አባላት በሰጡት ማብራሪያ የተናገሩት

የWolaita times ባለቤት የሆነው አሸባሪው ናትናኤል ጌቾ በታሎ በህግ ሊጠየቅ ይገባል!! ከወላይታ አመራሮች ሁለንተናዊ ድጋፍ እየተሰጠው ህዝብን ከህዝብ ጋሪ ለማጋጨት ሀሰተኛ መረጃዎችን...
26/07/2023

የWolaita times ባለቤት የሆነው አሸባሪው ናትናኤል ጌቾ በታሎ በህግ ሊጠየቅ ይገባል!!

ከወላይታ አመራሮች ሁለንተናዊ ድጋፍ እየተሰጠው ህዝብን ከህዝብ ጋሪ ለማጋጨት ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የሽብር ተግባር በመፈጸም ላይ ይገኛል።

ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የwolaita times ባለቤት ሲሆን በወላይታ ሶዶ ከተማ ጽ/ቤት ከፍቶ ሚዲያውን ወደ ህጋዊ ሚዲያ ለማሳደግ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እንጅ ይህ ግለሰብ የሚዲያ ህግን ባልተከተለ መልኩ በተደጋጋሚ የጋሞ ህዝብን ከወንድም የወላይታ ህዝብ ጋሪ ለማጋጨት ሀሰተኛ መረጃዎችን በሚዲያው በማሰራጨት ላይ ይገኛል። የጋሞ ህዝብን የማከፋፈል አጀንዳ ሆን ብሎ ያሰራጫል በአጠቃላይ በውሸት መረጃ የጋሞን ዞን ገጽታ ለማጠልሸት ቀንና ማታ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በመሆኑም ይህ አሸባሪ ግለሰብ አድራሻው እየታወቀ ሚዲያው የእሱ መሆኑ እየታወቀ እንዲህ አይነት የአሸባሪነት ወንጀል እየሰራ በህግ የማይጠየቅበት አግባብ ተገቢ ስላልሆነ አስፈላጊው መረጃ ተደራጅቶ በህግ መጠየቅ አለበት።

ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ቱሪስቶችን የማስተናገድ ብቃት ያላቸው ባለኮከብ ፦ ሆቴሎች ፣ ሎጆች ፣ ሪዞርቶች በበቂ ሁኔታ ያሉባት  የመንፈስ እርካታ የምትሰጠው  አርባምንጭ ከተማ Well ...
13/07/2023

ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ቱሪስቶችን የማስተናገድ ብቃት ያላቸው ባለኮከብ ፦ ሆቴሎች ፣ ሎጆች ፣ ሪዞርቶች በበቂ ሁኔታ ያሉባት የመንፈስ እርካታ የምትሰጠው አርባምንጭ ከተማ Well Come እያለች ትገኛለች ..............🌹🇪🇹

ነገሩ እንዴት ነው?
21/06/2023

ነገሩ እንዴት ነው?

በመኪና ተዘዋውረው ሀሰተኛ ሰነድ ተጠቅመው ሲለምኑ የነበሩ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዲላ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀሰኔ 5-2015 ዲላ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን መነሻቸውን አ...
14/06/2023

በመኪና ተዘዋውረው ሀሰተኛ ሰነድ ተጠቅመው ሲለምኑ የነበሩ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዲላ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ

ሰኔ 5-2015 ዲላ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን

መነሻቸውን አዳማ አድርገው ሀዋሳን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ላይ መሰል ማጭበርበር ፈፅመው ህመምተኛ ያልሆነን ሰው ባነር አሰርተው እንዲሁም ቲሸርት አሳትመው ገንዘብ ሲሰበስቡ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዲላ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል መከላከል ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር መብራቱ ምንዳዬ እንደገለፁት ልመናን መሰረት አድርጎ ገዛኸኝ ተሾመ የተባለ ግለሰብ የሽንት ፊኛ ችግር እንዳለበት ሰው በማስመሰል በሰውነቱ ላይ ጨርቅ አስሮ ሌላ ሰው የተጠቀመበትን የሽንት ማስወገጃ ቁስ ተጠቅሞ በመኪናና በሞንታርቦ በመታገዝ እየቀሰቀሱ ገንዘብ ሲሰበስቡ ውለዋል።

በዚህም የተቀነባባረ ሴራ ያለበት ነው ግብረአበሮቹ የህመምተኛውን ፎቶ የያዘ ቲሸርት አሳትመዋል የማህበረሰቡን ቀልብ መሳብ የሚችል ነገሮችን ሁሉ በመጠቀም ሽንት በሀይላንድ በመያዝ ጠጅና ሀሬቄ መጠጦችን በመያዝ ገንዘብ ከህብረተሰቡ ሲሰበስቡ በህብረተሰቡ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

ህብረተሰቡም መሰል ድርጊት የሚፈፅሙ አካላት እንዳሉ በመረዳት መረጃዎችን በደንብ በማጣራት ጥርጣሬ ካለ ለፖሊስ ወዲያው ጥቆማ መስጠት እንዳለበት ገልፀው በ24 ሰአት ውስጥ በኤግዚቢትነት ከተያዙ ማስረጃዎች ጋር ለፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡም ገልፀዋል።

የዲላ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ውብሸት ተሰማ እንደገለፁት መነሻቸውን አዳማ አድርገው እንደተነሱና ሀዋሳና በሌሎች ከተሞች መሰል ድርጊት የፈፀሙ ልምድ ያላቸው እንደሆኑ ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል።በዚህም የመንግስት የስራ ኃላፊዎችንም አሳስተዋል ግለሰቡን የአንጀት ካንሰር በሽተኛ ለማስመሰል የተለያዩ ማደናገሪያ የሀሰት ሰነዶችን ባነሮችንና ቲሸርቶችን አሳትው ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲዘርፉ ነበረ ብለዋል።

ማህበረሰቡ ኢትዮጵያዊ ዕሴቶችን መሰረት ያደረገ መደጋገፍና መረዳዳት እርስ በርስ የመተሳሰብ የመረዳዳት በጎ ባህላችንን የሚጎዳና በትክክል ህመም ውስጥ ያሉትን እንዳይረዱ ጥርጣሬ እንዲፈጠር የሚያደርግና በጎ ዕሴቶችን የሚሸረሽር ወንጀል ነው ብለዋል።

መሰል የመንግስት ተቋማትና የህክምና ተቋማት የሰጡትን ማስረጃዎችን በደንብ ማጣራት ያስፈልጋል ።
መሰለል አጠራጣሪ ድርጊቶች ሲፈጠሩ በቶሎ ለፀጥታ አካላት በማሳወቅ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚሻ መግለፃቸውን የዲላ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቦአል።

Address

Addis Ababa
00111111

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio News Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio News Tube:

Share