
16/09/2025
መንገድ አሳዮታለሁ በማለት ከ70 ዓመት አዛዉንት ላይ 14ሺ ብር ሰርቆ የተሠወረው ግለሰብ ተያዘ።
ወላይታ ሶዶ መስከረም 6/2018 ዓ/ም(ደኢፖኮ) በወላይታ ሶዶ ከተማ በአራዳ ቀበሌ ክልል በዋጃ ቄሮ ቀጠና ላይ ተጠርጣሪው ግለሰብ ነዋሪነታቸው ዋጃ ቄሮ የሆነው አዛውንት 14000/አሥራ አራት ሺህ /ብር ይዘው ሲጓዙ አይቶ መንገድ ልምራዎት በማለት ከተጠጋቸው በኋላ በኪሳቸው ያለውን ገንዘብ ሰርቆ ልብስና ጫማ ገዝቶ ቀሪዉን 4000/አራት ሺህ /ብር በእጁ ይዞ እያለ ግል ተበዳዩ ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ያደረሰን መረጃ አመላክቷል።