
18/05/2023
በጉራጌ ዞን ከ2000 በላይ የእኖር ሙስሊም ተማሪዎችን በአለባበሳቸው ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው እንዲርቁ በማድረግ ረገድና ከዚያም በኋላ ያሻውን ሙስሊም ሲያሳስር፣ ሲያስገርፍና ሲያሰቃይ የነበረው የዞኑ የጸጥታ ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ግርማ ከኃላፊነቱ ተነስቷል።
ለእኖር ሙስሊሞች የሚጠቅመው፤ የግለሰቡ ከኃላፊነቱ መነሳት ብቻ ሳይሆን እስካሁን በፈጸማቸው ዘግናኝ ወንጀሎች ተጠያቂ መደረግ አለበት። ከዞኑ ጀምሮ እስከ ጉንችሬ ድረስ እንዲሁም እስከ ፌዴራልና ክልሉ ድረስ ያለው ሰንሰለቱ ተጣርቶ ግብረ አበሮቹም ላይ ተገቢው እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።
የእኖር ሙስሊም ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸውም የሞራል ካሳ ተክሰው፤ ተማሪዎቹ የእምነት ነፃነታቸው ተከብሮ በክብር በኒቃባቸው ሊማሩ ይገባል።
ተገቢው መፍትሄ እስኪ ገኝ ድረስ እስከ ድል ደጅ በአላህ ፈቃድ ትግላችን ይቀጥላል።