Ethio News

04/05/2022
04/05/2022

፨እስካሁን ድረስ ጥሪ ያደረጉ ዩንቨርሲቲዎች ዝርዝር

✅ከሚያዚያ 24 እስከ ሚያዚያ 30/2014 ጥሪ ያደረጉ ዩንቨርሲቲዎች

📌አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (24-28)
📌ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ (27-28)
📌ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ (29-30)
📌 ባህርዳር ዩንቨርሲቲ(28-30)
📌ኮተቤ የት/ት ዩንቨርሲቲ(28-29)
📌 ASTU/AASTU (28-29)

✅ከግንቦት 01 እስከ ግንቦት 06/2014 ጥሪ ያደረጉ ዩንቨርሲቲዎች

📌ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ (01-05)
📌ቡሌሆራ ዩንቨርሲቲ (01-02)
📌መደወላቡ ዩንቨርሲቲ (01-02)
📌አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (01-02)
📌ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (01-02)
📌ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (03-04)
📌መቱ ዩኒቨርሲቲ (03-04)
📌ደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ (04-05)
📌ጅማ ዩኒቨርስቲ (04-05)

✅ከግንቦት 06 እስከ ግንቦት 14/2014 ጥሪ ያደረጉ ዩንቨርሲቲዎች

📌ደብረታቦር ዩንቨርሲቲ (08-09)
📌ኦዳ ቡልቱም ዩንቨርሲቲ (08-09)
📌ሐረማያ ዩንቨርሲቲ (12-14)
📌መቅደላ አምባ ዩንቨርሲቲ (10-11)
📌እንጅባራ ዩንቨርሲቲ (09-11)
news

04/05/2022

Point?3?EU
እስካሁን ባለው የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ያሳወቁ ተቋማት እና የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መግቢያ/ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ፦

📌ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ...........ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም

📌 ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ............ሚያዚያ 28 እና 29/2014
📌 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ............ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም

📌 መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ............... ግንቦት 10 እና 11 /2014 ዓ/ም

📌 Wolkite University............ ግንቦት 03 እና 04/2014 ዓ.ም

📌Injibara University............. ከግንቦት 9_11 2014ዓ.ም
📌አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ..............ሚያዚያ 24 እና 25/2014 ዓ/ም

Share አድርጉት
news

04/05/2022



መግቢያ / ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ፦

👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2014 ዓ/ም ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ

👉 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም

👉 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም

👉 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም

👉 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም

👉 ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም

👉 ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1 /2014 ዓ/ም

👉 ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም

👉 ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14

👉 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም

👉 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም

👉 መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 10 እና 11 /2014 ዓ/ም

👉 ጅማ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 4 እና 5 /2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 4 እና 5 /2014 ዓ/ም

✅ስለ ዩኒቨርስቲ መረጃ ከፈለጋችሁ ሼር አድርጉ ።
💥ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ📍
news

29/04/2022

ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ ሚያዚያ 21 ፤ በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡

ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከቅዱስ ኡራኤል አካባቢ ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ እና በዙሪያዋ የሚገኙ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናሉ።

በዚህም መሰረት፦

🛣 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሀያ ሁለት ወይም ዘሪሁን ህንፃ አካባቢ ዝግ ይደረጋል፣

🛣 ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር ኦሎምፒያ፤

🛣 ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ፤

🛣 ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ እና ከሜኪሲኮ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚጓዙ ሜክሲኮ አደባባይ፤

🛣 ከጌጃ ሰፈርና ከጎማ ቁጠባ በሰንጋ ተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ የቀድሞው ደሳለኝ ሆቴል መስቀለኛ ላይ፤

🛣 ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ለሚጓዙ ጎማ ቁጠባ ላይ እና ከሜክሲኮ ወደ ፖስታ ቤት ለሚሄዱ ሚትሮሎጂ አካባቢ እንዲሁም ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በር አካባቢ፤

🛣 ከተክለኃይማኖት በጎላ ሚካኤል ለሚመጡ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ላይ እና ከተክለኃይማኖት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ለሚመጡ ተክለኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከተክለ ኃይማኖት በሶማሌ ተራ ወደ ባንኮ ዲሮማ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሸዋ ሱፐር ማርኬት ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

🛣 ከቀድሞ አትክልት ተራ አካባቢ በአሮጌው ፖስታ ቤት ወደ ቸርችል ጎዳና የሚወስደው መንገድ አሮጌው ፖስታ ቤት፤

🛣 ከደጎል አደባባይ ወደ እሪ በከንቱ ደጎል አደባባይ ላይ እና ከአራት ኪሎ በፓርላማ ወደ ውጭ ጉዳይ የሚወስደው መንገድ ሸራተን ሆቴል መውረጃ ላይ፤

🛣 ከ4 ኪሎ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ ይዘጋል።

🛣 ከካዛንቺስ ሼል ወደ ፍል ውሀ እና ወደ ባምቢስ የሚወስዱት መንገዶች ካዛንስ ሼል ላይ ከቀኑ7፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጠር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው።

ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት ይቻላል።

news

27/04/2022

የአበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ጥሪ ፦

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሚያዚያ 24 ቀን እና ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ የሚያስፈልጋችሁ ነገሮች ከላይ ተዘርዝረዋል አንብቧቸው።

ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ https://portal.aau.edu.et ማግኘት ትችላላችሁ።

በሌሌላ በኩንል ፤ ተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከሚያዚያ 27 እና 28 2014 ዓ.ም እንዲያመለክቱ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አቅርቧል።
news
news

27/04/2022

እርስ በእርስ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ መቀያየር እንደማይቻል የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል

የትምህርት ሚኒስቴር በትናንት እለት የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ማደረጉ ይታወቃል።

መደባውን ተከትሎ ከዚህ ቀደም እንደነበሩ ጊዜያት ሁሉ አንዳንድ አካላት " ተማሪዎችን እና ወላጆችን ገንዘብ ክፈሉ ምደባ እናስተካክላለን ፣ ወደ ፈለጋችሁበት እንድትመደቡ እናደርጋለን " በሚል የማጭበርበር እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።

በሌላ በኩል አንዳንድ ተማሪዎች እና ወላጆች የዩኒቨርሲቲ እርስ በእርስ መቀያየር ይቻል እንደሆነ ጥያቄ አቅርበዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳሳወቀው ተማሪዎች ምደባን ተከትሎ ከማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ላይ ከተሰማሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ፤ ምደባ እንቀይራችኃለን የሚሉትም ሀሰተኞች መሆናቸው እንዲሁም እርስ በእርስ ምደባ መቀያየር የሚባል ነገር እንደሌለ አስገንዝቧል።

በዚሁ አጋጣሚ ዩኒቨርሲቲዎች በአጭር ጊዜ ተማሪዎችን እንዲጠሩ አቅጣጫ በመቀመጡ ተማሪዎች እና ወላጆች አስፈላጊውን ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።
News

News

Send a message to learn more

27/04/2022

•.¸♡[ Mizan_Tepi ]♡¸.• UNIVERSITY

አድራሻ ❓

📚 ሚዛን ደቡብ ክልል ላይ ቤንቺ ማጂ ዞን ውስጥ
የምትገኝ ሞቅ ያለች ከተማ ናት ፤ ቅርንጫፍ ግቢው ደግሞ በሸካ ዞን ውስጥ ይገኛል ።ከአዲስ አበባ
ሚዛን 570km ርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች ናቸው፤ great east africa reftvalley በመባልም ትታወቃለች ።

የአየር ሁኔታ ❓

📚 ሞቃታማ ሆና አልፎ አልፎ ከባድ ዝናብም ይዘንባል።

የካንፓሶች ብዛት ❓

📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎች ሁለት ናቸው ። እነሱም ፦

✅ Main campus: ሚዛን ተፈሪ ከአዲስ አበባ 570km ግቢው ውስጥ ደስ የሚል ወንዝ አለ ስያሜውም ሾንጋ ይባላል አመቱን ሙሉ ንፁህ እና ምንም የማይቀንስ በመሆኑ ለትምሮ አሪፍ ነው ።
በዚ የሚሰጡ ፊልዶች ፦

➡all social
➡Agri
➡ Medicine
➡ Health..
➡ Business and economics
➡ Law...

✅Tepi campus: ከአዲስ አበባ 611 km ከሚዛን ደግሞ 60ኪሜ ርቀት ሸካ ወረዳ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት ፤ ሀገሩ የማርና የወተት ሀገር ነው ።

በውስጡም ፦

🔔Engineering departments
⭕ Electrical engineering
⭕ Mechanical Engineering
⭕ Civil engineering....
🔔Computer science
⭕ CS
⭕ IS
⭕ IT...
🔔Natural computational
🔔Social computational

📚የህክምና ተማሪዎች የሚማሩት በአማን የመማርያ ሆስፒታል ሲሆን የሚገኘውም በዋናው ግቢ ከተማ ሚዛን ተፈሪ ነው።

ካፌ ምግብ ❓

📚ጥሩ የሚባል አይነት ነው ፤ አንዳንዴ ቢደብርም ያን ያክል የሚያስጠላ አይደለም ። በቃ በልቶ ለመማር አሪፍ ነው ።

ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓

📚 Food price ከሌሎች ግቢዎች አንፃር ቅናሽ የሚባል ነው። ግቢ ውስጥ ያሉት ላውንቾች ዋጋቸው ቅናሽ ቢሆንም ምግባቸው ግን ብዙም አይነፋም ፤ ብዙ የዋጋ ልዩነት ስለሌለው ውጭ መጠቀም ይሻላል ። ሚዛን ለምትገቡ ተማሪዎች ትኩስ ነገራት ቡና ግቢ ውስጥ ሁለት ብር ሲሆን ወጣ ካላቹህ አንድ ብር ብቻ ➕ ፤ ሻይም በተመሳሳይ ዋጋ ፤ ለውዝ እስፕሪስ ምናምን ግቢ ውስጥም ይሁን ውጭ እኩል ናቸው 3 እና 5 ብር ነው ።

📚avocado 🍌 ሙዝ እና የፍራፍሬ ዘር ባጠቃላይ በጣም ርካሽ ናቸው ። የ10 በር 20 ፍሬ ምናምን ይሸጣል።

የዕቃ ስርቆተ ❓

📚 ለፍሬሽ ተማሪዎች ብዙም አስጊ ነገር የለም ግን ማታ ማታ ከግቢ ውጭ ብዙ እንዳትዞሩ ሎካሎች አንዳንዴ hang ያደርጋሉ ይባላል።

ውሃ ፤ መብራት ፤ WIFI ❓

📚 ውሃ በጣም ጥሩ ነው ፤ መብራት ምንም አይልም ፤ WIFI በጣም ያናድዳል።

ሽንት ቤት ❓

📚 ጥሩ ነው ፤ በአንፃራዊነት ከሌሎች ግቢዎች የተሻለ ነው ።


📚 በተረፈ እንኳን ወደ ምድረ ገነት በሰላም መጣቹህ ብለው የሚቀበሏቹህ የከተማው ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በተለያየ ምክንያት ኑሯቸውን ሚዛን ያደረጉ ምርጥዬ ወገኖቻቹህ ናቸው ።

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
news

27/04/2022

ወላይታ ሶዶ ዮኒቨርሲቲ ❓

📚በደቡብ ክልል የምትገኝ ከተማ ነች...!

የአየር ሁኔታ ❓

📚 ወቅቶች አላቸው የሚበርድበት ግዜ በተለይ የጥቅምት ወር ከሚያዚያ ወደዛ ደግሞ ሞቀት ነው ።

፦ በአጠቃላይ 3 ካንፓስ አለ ፦

✅መእን ካምፓስ

📚 all department ትምህርቶች ይሰጣሉ ፦
including Vet.medicine፦

✅Agroeconamics,
✅Agrobussines.

📚✅Otona campus:

🎯 health science
🎯 (Medicine, ho, nursing, midwifer
,🎯pharmacy
🎯 clncal pharmacy...etc)

✅Dawuro tarcha campus:
some of agriculture department

የካፌ ምግብ ❓

📚በጣም ጥሩ የሚባል ነው ፤ እንደ ብዙ ግቢዎች አያስከፋም ...! በተቻለ አቅም ተማሪው ለማስደሰት ይጣራል ...!

የሰላም ሁኔታ ❓

📚 ግብያችን ለየት የምይያደርገው፣ ሰላም አምባሳደር ናት። ምንም ሐሳብ አይግቡ!

ሽንት ቤት ❓

📚ትንሽ ይደብራል ግን የሚለመድ አይነት ነው ፤ በተማሪዎች ዕንዝላልነት የተነሳ አስጠሊ ስፍራ ሆኗል ፤ ይሻሻላል ብለን እናስባለን...!

ውሃ ፤ መብራት ፤ WIFI ❓

📚 ምንም አያሳስብም ዘጭ ናቸው ፤ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ እነዚህ ነገራቶች በጣም ነው የተሟሉት...አንዳንድ ብሎኮች ጋር ውሃ ቢያስቸግርም ..! የሚያሳስብ አይደለም..!


የዕቃ ስሮቆት ❓

💬 ሶዶ ላይ ሌባ በጣም አስቀያም ነው፣ ስለዚህ ስትመጡ ራሳችው ጠብቁ! ፤ ለሌቦች እንዳትጋለጡ በጥንቃቄ ነው አካሄዳችሁ መሆን ያለበት ፤ በጣም ጭልፊቶች ነው ያሉት...!

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
news

27/04/2022

#ጂንካ ዩኒቨርሲቲ

አድራሻ ❓

📚 በደቡብ ክልል የምትገኝ አረንጓዴ መሬት ነች ጂንካ .....አሜሪካ ራሱ የጂንካን ያህል አትነፈም ይባላል.፤ ከአዲስ አበባ አርባምንጭ በ505km ነው ፤ ከአርባምንጭ ጂንካ የ 150 ብር መንገድ አጠቃላይ ከሸገር 700km አከባቢ ይሆናል ...!

የአየር ሁኔታ ❓

📚 የአየሩ ሁኔታ በመጀመሪያዎቹ ወራቶች አካባቢ ቀዝቀዝ ይላል ሌላውን ጊዜ ግን ሙቀቱ አይጣል ነው ፤ Almost ምቹ የአየር ፀባይ አላት።

📚 ጊቢው የተከፈተው በቅርብ በ2010 ነው ግን በጣም አድጓል እያደገም ነው ...!

✅ በNatural science ፦

🎯Agriculture...
🎯Agroeconomics
🎯Computer science(it)
🎯Competition
🎯Sport science *new*

✅በSocial science ፦

🎯 Competition,
🎯 Law,
🎯 Fb (Accounting andManagment,)
🎯 Economics) በቅርቡ ብዙ አዳዲስ Field ይጀምራሉ ተብሏል "።

wIFI፤ ውሃ እና መብራት ❓

📚 ውሃ እና መብራት ያበደ ነው በጣም ጀስ ይላል ፤ እየተንቦራጨቅ ነው የምንማረው ፤ WIFI የለም በሉት የስም ነው.......ዳታ በደንብ ይሰራል ከሱ ...!

የካፌ ምግብ ❓

📚በጣም አሪፍ ነው ፤ በጣም ትንሽ ተማሪ ስለሆነ የሚማረው በጥራት ነው የሚሰራው ፤ የቤት ምግብ በሉት ..!

ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓

📚 ሲጀመር ብዙ ሰው ካፌ ተመጋቢ ነው ፤ አንዳንድ ልጆች ላውንጅም ....ምናምን ይጠቀማሉ ዋጋው ተመጣጣኝ ነው ከ 15 -25 የትኛውም ምግብ ይገኛል ፤ የሆነ ወቅት ላይም ፍራፍሬ ምናምን በሽ ነው ።

ሽንት ቤት ❓

📚 በጣም አሪፍ ነው ይመቻል ፤ ትንሽ ተማሪ ስላለ በጥንቃቄ እነ በፅዳት ይያዛል ...!

የፀጥታ ሁኔታ ❓

📚 ጂንካ የፍቅር ሀገር ነች ፤ ችግሮች ሁሉ በፍቅር ነው የሚፈቱት ....ኮሽ ብሎ አያውቅም ...!

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
news

27/04/2022

Injibara university


አድራሻው ❓

እንጅባራ ዩኒቨርስቲይ ከአዲስ አበባ በ 440km የሚገኝ ሲሆን አገው ምድር ይገኛል ፤ በባስ (በዋልያ,በጎልደን ,በየኛ ,በአባይ 7:30 ላይ ዘጭ ትላላችሁ በታታ 12:00 ላይ ዘጭ ትላላችሁ ::

የአየር ንብረት ❓

📚 ቀዝቃዛ ነው እናም ወፍራም ልብሶችና ጃኬት ያስፈልጋል ፡፡ ብርዱን ያለበለዚያ አትችሉትም ...!

ዲፓርትመንት ❓

✅ በSocial 14 ዲፓርትመንት ሲኖረው እነሱም ፦

🎯 Law
🎯 economics
🎯 management
🎯 accounting ....
🎯 Banking ....etc

✅በNatural 12 department አለው ፦

🎯 Computer science ,
🎯 It ,
🎯 competition ,
🎯 Agricultural economics ,
🎯 narm
🎯 plant .... etc

የካፌ ምግብ ❓

📚 አቦ በቃ አይነፋም፤ ውጪ በጣም ይሻሻል ነው ...አዛ የሆነ ምግብ ነው የሚቀርበው ....ምግብ በጣም ይከብዳል ....!

ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓

📚 ይሄ በጣም ያበደ ነው ....በጣም ነው ደስ የሚለው ፤ ከ 20-30 ብር አማርጠህ ፅድት ያለ ምግብ ትበላለህ ፤ ምግቡ የ non _cafe በጣም አንደኛ ቤተ መንግስት ያስንቃል .....!

መብራት ፤ ውሃ ፤ Network ፤ wifi ❓

📚 በጣም ችግር ነው ፤ ውሃም መብራትም በጣም ይጠፋሉ ፤ networks ራሱ በደንብ አይሰራም ፤ WIFi ቅንጦት ነው ሲያምርህ ይቅር ፤ ከቻላችሁ power bank እና solar system ያለው ባትሪ ይዛችሁ ኑ

📚*ላይብረሪ እና የላውንች ችግር ስላለ ከወዲሁ ዝግጅት አርጉ ፤ ብዙ አትጓጉ....ደስታ የሚባል ነገር የለም ...!..

የሰላም ሁኔታ ❓

📚 የፍቅር ሀገር ነው ፡ ፤ ፓለቲካ ,የብሔር ,የሰላም ችግር አያሳስባችሁ ፡፡ እዚ ከእህል በቀር ዘር አያውቁም .....!

የሽንት ቤት ነገር ❓

📚 ምንም አይልም ከሌሎች ነገሮች አንፃር የተሻለ ነው ፤ መሻሻል ግን ይቀረዋል .... !

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
news

27/04/2022

ሰመራ UNIVERSITY

አድራሻ ❓

📚 ሰመራ በአፋር ክልል የምትገኝ ዮኒቨርስቲ ነች ።

የአየር ሁኔታው ❓

📚 በጣም ሞቃታማ ነው ስለዚህ ከበድ ያለ ብርድ ልብስ ፈፅሞ አያስፈልግም ይህም ማለት ግን ምንም አይነት አንሶላ አያስፈልግም ማለት አይደለም መጀመሪያ ሴሚስተር ላይ ቀለል ያሉ አንሶላዎች ያስፈልጋችኋል ።


የካንፓሶች ብዛት ❓

📚 ግቢው አንድ ብቻ ነው ምንም branch የለውም።

✅ በግቢው የሚሰጡ ኮሌጆች እንደሚከተለው ተገልጿል ፦

1.College of engineering and technology
1.1 Chemical Engineering
1.2 Electrical Engineering
1.3 Civil Engineering
1.4 Mechanical Engineering
1.5 Construction Technology & Management (CoTM)
1.6 Water resource & irrigation engineering
2. College of business and economics
2.1 Accounting
2.2 Management
3.college of health science
3.1 Bsc.nursing
3.2 midwifery
4.College of Agriculture
4.1 Narm
4.2 RDA
4.3 Horticulture
5.College of Computational science
5.1 Biology
5.2 Chemistry
5.3 Statistics
5.4
6.Language and literature
እና ሌሎችም

📚 ማህበረሰቡ በጣም ጨዋ እና ሠው ወዳድ እንግዳ ተቀባይ ነው ።

የካፌ ምግብ ❓

📚 እንደ ማንኛውም ዮኒቨርስቲ ያን ያክል አስደሳች የሚባል አይደለም ፤ የሚቀርቡ ምግቦች ምሳ ላይ ሻል ይላሉ በተረፈ ትንሽ ከበድ ይላል ።

ከካፌ ምግብ ውጪ ያሉት❓

📚 መጀመሪያ ላይ እንደገባችሁም ቢሆን Non-cafe መመዝገብ ትችላላቹ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ጋ አይቻልም ::ግቢ ውስጥ ቡና 3 ብር (ውጪ ላይ 5 ብር ) ሻይ 2 ብር ምግቦች እስከ 15 ብር (ውጪ ላይ እስከ 25 ብር ) ይገኛሉ ።

የረብሽ ሁኔታ ❓

📚በተረፈ ግቢያችን ከሀገሪቱ ዩንቨርሲቲዎች አንፃር ሲታይ ሰላማዊ ግቢ ነው። የፍቅር ሀገር ነው ።

ውሃ ፥ መብራት፤ WIFI ❓

📚 መብራት አሳሳቢ አይደለም ከነ አይጠፋም ፤ ውሃ እና WIFi በቂ ባይኖንም ለማቅረብ ይሞከራል ።

ሽንት ቤት ❓

📚 የትም ግቢ ካለው አይለይም የፀዳ ባይባልም ፤ ለመጠቀም ያክል ይሆናል ።

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
news

Address

Bole
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio News:

Share