Negarit Mereja - ነጋሪት መረጃ

Negarit Mereja - ነጋሪት መረጃ ነጋሪት መረጃ ለወቅታዊና አዳዲስ መረጃዎች።

12/11/2024
እናመሰግናለን 🙏ቀነኒ ኬኛ!
10/08/2024

እናመሰግናለን 🙏
ቀነኒ ኬኛ!

በፓሪስ ኦሎምፒክ የወንዶች ማራቶን የመጀመሪያው ወርቅ ለኢትዮጵያ በታምራት ቶላ! እንኳን ደስ ያለን!ታምራት የኦሎምፒክ ክብረወሰን በመስበር ነው ይህንን ድል ለሀገሩ ያስገኘው።  in   - M...
10/08/2024

በፓሪስ ኦሎምፒክ የወንዶች ማራቶን የመጀመሪያው ወርቅ ለኢትዮጵያ በታምራት ቶላ! እንኳን ደስ ያለን!

ታምራት የኦሎምፒክ ክብረወሰን በመስበር ነው ይህንን ድል ለሀገሩ ያስገኘው።

in - Men's Marathon

Tamirat Tola 🇪🇹 (2:06:26 OR) wins 's first🥇

📷: Getty Images

ጎፋ በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለበደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን በደረሰው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የ...
25/07/2024

ጎፋ በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን በደረሰው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

ጽህፈት ቤቱ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ ባወጣው የሁኔታዎች መግለጫ ላይ ነው በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል ያመለከተው።

እሁድ ሐምሌ 14 እና ሰኞ ሐምሌ 15/ 2016 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ተቀብረው የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ዛሬም ለአራተኛ ቀን እየተካሄደ ነው።

በአደጋው ስፍራ የሚገኙት የቢቢሲ ዘጋቢዎች እንደገለጹት ዛሬን ጨምሮ በአካባቢው እየጣለ ባለው ዝናብ ውስጥ ጭምር ከተንሸራተተው መሬት ስር ለማውጣት የሚደረገው የነፍስ አድን ጥረት ቀጥሏል።

ባለፉት ቀናት በተደረጉት የፍለጋ ጥረቶች በአደጋው ሕይወታቸው አልፎ የተገኙ ሰዎች ቁጥር 257 የደረሰ ሲሆን፣ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ስጋታቸውን መግለጻቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) አመልክቷል።

በአዲስ አበባ ከ7,540 በላይ እግረኞች ተቀጡአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ተላፈው በተገኙ 7ሺ 540 በላይ እግረኞች መቀጣታቸው ዛሬ ከከተማዋ ም/ቤት ተሠምቷል።በዚህም መሠረት 3,994 እግረኞች...
17/07/2024

በአዲስ አበባ ከ7,540 በላይ እግረኞች ተቀጡ

አዲስ አበባ ከተማ ደንብ ተላፈው በተገኙ 7ሺ 540 በላይ እግረኞች መቀጣታቸው ዛሬ ከከተማዋ ም/ቤት ተሠምቷል።

በዚህም መሠረት 3,994 እግረኞች በገንዘብ 3,426ቱ ደግሞ በማህበራዊ አገልግሎት መቀጣታቸው ተገልጿል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቶማስ ማቲው ክሩክስ ማነው?******************በምረጡኝ ቅስቀሳው ወቅት ዶናልድ ትራምፕ ላይ በጥይት ጥቃት የፈፀመው ወጣት ቶማስ ማቲው ክ...
14/07/2024

ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቶማስ ማቲው ክሩክስ ማነው?
******************

በምረጡኝ ቅስቀሳው ወቅት ዶናልድ ትራምፕ ላይ በጥይት ጥቃት የፈፀመው ወጣት ቶማስ ማቲው ክሩክስ እንደሚባል ኤፍቢአይ ገልጿል።

ይህ የ20 ዓመት ወጣት የግድያ ሙከራው ከተፈፀመባት ቦታ (በትለር) 70 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ቤተል ፓርክ ይኖር እንደነበር ተገልጿል።

ወጣቱ እ.ኤ.ኤ በ2022 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከቤተል ፓርክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማጠናቀቁን ፒትስበርግ ትሪቡን ሪቪው ጋዜጣ ዘግቧል።

ክሩክስ የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊ መሆኑን የመንግሥት የመራጮች መዛግብት ያሳያሉ።

እንደ አሜሪካ ሚዲያዎች ዘገባ፥ ጥቃት አድራሹ ወጣት በ2021 አክትብሉ (ActBlue) ለተባለው የሊበራል የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን 15 ዶላር ለግሷል።

እሱ በፈፀመው ጥቃት አንድ ታዳሚ ሲሞት ሁለት ሌሎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል ተብሏል።

ታዲያ ይህ የ20 ዓመት ጥቃት አድራሽ ወጣት ወዲያው በተወሰደበት እርምጃ መገደሉንም ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ኤፍቢአይ ባወጣው መግለጫ ክሩክስ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራ ውስጥ የተሳተፈበት ጉዳይ ምን እንደሆነ ጥልቅ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል።

ወንጀሉን የፈፀመው ክሩክስ በጊዜው መታወቂያ ባለመያዙ መርማሪዎቹ ማንነቱን ለማወቅ ዲኤንኤ ተጠቅመዋል ሲል ኤፍቢአይ ተናግሯል።

ኤፍቢአይ የጥቃቱን ዓላማ እና ሌላ ሰው ከኋላው ስለመኖሩ እየመረመርኩ ነው ብሏል።

የኤፍቢአይ የፒትስበርግ ልዩ ወኪል የሆኑት ኬቨን ሮጄክ ቅዳሜ ምሽት በሰጡት አጭር መግለጫ፥ “በአሁኑ ጊዜ ተለይቶ የሚታወቅ ምክንያት የለንም፤ ምክንያቱን ለማወቅ ያለድካም እንሰራለን" ሲሉ ተሰምተዋል።


ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጪ በመሔድ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካን አገር ገብቷል።
14/07/2024

ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጪ በመሔድ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካን አገር ገብቷል።

አትወርሱም አዲስ ፊልም የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 12:00 ሰዓት በ Hamus Media የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል!!https://youtube.com/?si=hoJ_XXPXAVyoNiSU
21/06/2024

አትወርሱም አዲስ ፊልም የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 12:00 ሰዓት በ Hamus Media የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል!!
https://youtube.com/?si=hoJ_XXPXAVyoNiSU

09/05/2024

ዛሬ ግንቦት ገባ
ግንቦት ማለት ገነባ፣ ሠራ፣ ቆፈረ፣ ሰረሰረ ማለት ነው።

ገበሬው ለእርሻ መሬቱን መዘጋጀቱን ያመለክታል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Negarit Mereja - ነጋሪት መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share