KASu//TV

KASu//TV No one do anything

Best Ethiopia singer   fetene
23/02/2025

Best Ethiopia singer fetene

Same woman, same motorcycle... 71 years apart.
15/07/2023

Same woman, same motorcycle... 71 years apart.

በአምቦ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈአዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ከልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ ተልተሌ በሚባለው ቦታ በደረሰ የት...
26/06/2023

በአምቦ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ከልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ ተልተሌ በሚባለው ቦታ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በአምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

አደጋው የደረሰው ዛሬ 3፡00 ላይ ሲሆን ÷ ከአምቦ ወደ ጉደር ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረ አነስተኛ የሕዝብ ተሸከርካሪ ከሌላ የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው ነው፡፡

👉👉ዶ/ር ታዘባቸው "ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል" ተወስኖለታል፡፡ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው ዶ/ር ታዘባቸው ውዴ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ...
15/04/2023

👉👉ዶ/ር ታዘባቸው "ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል" ተወስኖለታል፡፡

ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው ዶ/ር ታዘባቸው ውዴ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማህፀንና ፅንስ ሬዚደንትነት ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው ስፔሻላይዜሽን ትምህርቱን ለማጠናቀቅ ሁለት ወራት ሲቀረው በአንደኛው አይኑ ላይ ባለበት መንሸዋረር ምክንያት ትምህርቱን እንዲያቆም መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ወደሌላ የትምህርት ክፍል ተዘዋውሮ ከአንደኛ ዓመት እንዲጀምር መወሰኑም አይዘነጋም፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የባለሙያዎች ቡድን በማቋቋም የዶ/ር ታዘባቸውን ቅሬታ ሲመረምር ቆይቷል፡፡

የባለሙያዎች ቡድን የቀረቡለትን መረጃና ማስረጃዎች ከመረመሩና እንደገና የማጣራት ሥራ ካከናወኑ በኋላ ዶ/ር ታዘባቸው ወደ ትምህርቱ እንዲመለስ የውሳኔ ምክረ ሃሳባቸውን ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ አቅርበዋል።

የዩኒቨርስቲው ቦርድም የባለሙያዎቹን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ዶ/ር ታዘባቸው ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል ወስኗል፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው ትምህርቱን አቋርጦ በቆየበት ወቅት ድጋፍ ላደረጉለትና ውሳኔውን በመቃወም ለተሟገቱለት አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

      እራሱን ልጅ ያሬድ እያለ የሚጠራው ወጣት በትላንትናው እለት በተፈጠረ አለመግባባት ትንሽ የአካል ጉዳት ደረሰበት!
12/04/2023



እራሱን ልጅ ያሬድ እያለ የሚጠራው ወጣት በትላንትናው እለት በተፈጠረ አለመግባባት ትንሽ የአካል ጉዳት ደረሰበት!

ቴሌግራም 👉 https://t.me/Merejanews      ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በ“ከባድ የሙስና ወንጀል” ከተከሰሱት ግለሰቦች ውስጥ አምስቱ በፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ! ...
12/04/2023

ቴሌግራም 👉 https://t.me/Merejanews

ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በ“ከባድ የሙስና ወንጀል” ከተከሰሱት ግለሰቦች ውስጥ አምስቱ በፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ!

ከአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በ“ከባድ የሙስና ወንጀል” ክስ ከተመሰረተባቸው ግለሰቦች ውስጥ የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን ጨምሮ፤ አምስት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ።

በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፤ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ በፍርድ ቤቱ በይኗል።

ይህን ብይን የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 4/2015 የዋለው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ችሎት ነው።ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው፤ “ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ፤ ወንጀሉን በበቂ ሁኔታ ባለማስረዳቱ” መሆኑን ገልጿል።

በነጻ ከተሰናበቱት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አብርሃም ሰርሞሎ እና የከተማይቱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬይትን ሲመሩ የነበሩት ኩምሳ ቶላ እንደሚገኙበት ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

👉👉ስንታየሁ ቸኮል በዛሬው ዕለት በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተፈቷል። እንኳን ለቤትህ አበቃህ!
12/04/2023

👉👉ስንታየሁ ቸኮል በዛሬው ዕለት በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተፈቷል።
እንኳን ለቤትህ አበቃህ!




ቴሌግራም  👉 https://t.me/Merejanewsበሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተውን የሰደድ እሳት መቆጣጠር አለመቻሉ ተገለፀ   |  ከባለፈው መጋቢት 29 ቀን ጀምሮ በሰሜን ተራሮች...
11/04/2023

ቴሌግራም 👉 https://t.me/Merejanews

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተውን የሰደድ እሳት መቆጣጠር አለመቻሉ ተገለፀ

| ከባለፈው መጋቢት 29 ቀን ጀምሮ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተውን የሰደድ እሳት እስካሁን መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሰደድ እሳት መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከ ቀኑ 9 ሰዓት ባልታወቀ ምክንያት መነሳቱ ተጠቁሟል።

የፓርኩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዛናው ከፍያለው እንደተናገሩት÷ እሳቱን ለማጥፋት የአካባቢው ማህበረሰብ ቢሞክርም መቆጣጠር አለመቻሉንና ከ600 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እሳቱን ለማጥፋት መግባታቸውን ጠቁመዋል።

የቦታ አቀማመጡ ገደላማ መሆኑ እሳቱን ለመቆጣጠር ፈተና ሆኖብናል ያሉት ሃላፊው÷ እሳቱ ግጭ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በኩል እንደተነሳ አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ እስከ ዛሬ ማለትም እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2015 ድረስ እሳቱ ከቁጥጥር ውጭ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በዚህም በፓርኩ የተነሳውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡



👉👉👉ምስኪኖቹ የደቡብ ኦሞ ዜጎቻችን የእኛን እጅ ይጠብቃሉ!
11/04/2023

👉👉👉ምስኪኖቹ የደቡብ ኦሞ ዜጎቻችን የእኛን እጅ ይጠብቃሉ!



መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ታሰረች      |
11/04/2023

መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ታሰረች



|

📍Ensaro amhara region Ethiopia 🇪🇹 Ethiopia Land of Origins Travel to Ethiopia Visit Amhara RISE UP Hiking
10/04/2023

📍Ensaro amhara region Ethiopia 🇪🇹
Ethiopia Land of Origins Travel to Ethiopia Visit Amhara RISE UP Hiking





ቴሌግራም 👉 https://t.me/Merejanews    የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የሚከተሉትን ጥሪዎች በድጋሜ አስተላልፏል!1. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸውን በይፋ እንዲሰርዙ ፣ ው...
10/04/2023

ቴሌግራም 👉 https://t.me/Merejanews



የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የሚከተሉትን ጥሪዎች በድጋሜ አስተላልፏል!

1. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸውን በይፋ እንዲሰርዙ ፣ ውሳኔው ስለመሰረዙ በአደባባይ እንዲገልጹ እና የአማራ ልዩ ኃይል አባላት እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ካምፓቻቸው እና ወደ ግዳጅ ቦታቸው እንዲመለሱ በይፋ ጥሪ እንዲያደርጉ፤

2. በፌዴራል መንግስቱ ውሳኔ እና ትዕዛዝ ከስራ ውጭ የሆኑት የአማራ ልዩ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች ፣ የብርጌድ እና የክፍለ ጦር አዛዦች ወደ ኃላፊነታቸው እና ምድብ ቦታቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ፤

3. የክልሉ መንግስት ለልዩ ኃይሉ አስፈላጊ የሆኑ የስንቅ እና ሎጂስቲክ እንዲያቀርብ እና ደሞዝ እንዲከፍል፤

4. በካምፕ እና በግዳጅ ቦታችሁ ላይ የምትገኙ ውድ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ሠራዊቱ እንዲበተን የሚደረጉ ጥረቶችን እና የፕሮፖጋንዳ ጥቃቶችን በመቋቋም በተለመደው ሥነ-ምግባር ፣ ዲስፕሊን እና ጨዋነት የሠራዊቱን የእዝ ሰንሰለት አክብራችሁ እና ጠብቃችሁ ከህዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ፤

5. ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና አመራሮች በሙሉ በግፍ እየተጠቃ ካለው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ከአማራ ሕዝብ ጎን እንድትቆሙ እና ለግጭት ከሚጋብዙ ማናቸውም ሁኔታዎች እንድትቆጠቡ፤

6. የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዞን እና የወረዳ አመራሮች በሙሉ በዚህ ፈታኝ ወቅት ከልዩ ኃይል ፖሊስ ሰራዊት እና ከሕዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ፤

7. የአማራ ሕዝብ በየአካባቢው ላሉት የልዩ ኃይል አባላት አስፈላጊውን ስንቅ እና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ድርጅታችን አብን ጥሪውን አቅርቧል።

አብን መላው የአማራ ሕዝብ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከሀገር ወዳዱ የአማራ ልዩ ኃይል ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አቅርቧል።

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KASu//TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to KASu//TV:

Share