05/04/2023
Traditional Marketing vs Digital Marketing
ከተለመደው ባህላዊ ማስታወቂያ (Traditional Marketing ) ዲጂታል ማስታወቂያ(Digital Marketing) ለምን የተሻለ ሆነ?
የአንድን ድርጅት ወይም ተቋም ምርት እና አገልግሎት ለማስተዋወቅ ደንበኞችን ትኩረት በመሳብ ከሚሰሩ ስራዎች ማስታወቂያ ወይም ማርኬቲንግ አንዱ ነው፡፡ ማረኬቲንግ ከሚሰራባቸው መንገዶች አንዱ ባህላዊ ማስታወቂያ ሲሆን ሁለተኛው እና ዘመናዊው ደግሞ ዲጂታል ማርኬቲንግ ነው፡፡ በዛሬው ፅሁፋችን የሁለቱን ልዩነት እና በአሁን ሰዓት ዲጂታል ማረኬቲንግ ለምን የተሻለ አማራጭ ሆነ የሚለውን ለማይት እንሞክራለን፡፡
የተለመደው ባህላዊ የማስታወቂያ ዘዴ ትራዲሺናል ማርኬቲንግ ምርት እና አገልግሎትን ለማስተዋወቅ እና ለመሸጥ በመገናኛ ብዙሃን (Main Stream Mass Media) ማለትም በቴሌቪዢን፣ በሬዲዮ፣ በጋዜጣ፣ እንዲሁም የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን በመጠቀም ማለትም እንደ ባነር፣ ፍላይር፣ ቢልቦርድ፣ ፖስታ፣ ስልክን ወዘተ በመጠቀም የደንበኛ መስረታችንን ለማስፋት ምርት እና አገልግሎታችን በደንበኞች አእምሮ ውስጥ በማይረሳ መልኩ ለማስቀመጥ እና ተፈላጊነት ለመጨር የምንጠቀመው የማስተዋወቅ ወይም የማርኬቲንግ ዘረፍ ነው፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ዘዴ ዘለግ ላለ ግዜ እስከአሁንም ድረስ አገልግሎት ላይ ያለ ሲሆን በዋጋ ውድነት እንዲሁም ውጤቱን ወዲያውን በቀጥታ ለመመዘን የሚያስችል ስርዓት ወይም ቴከጅኖሎጂ ባለመኖሩ በአሁን ሰዓት ብልጫውን ለዲጂታል ማርኬቲንግ(Digital Marketing) በማስረከብ ላይ ይገኛል፡፡
ለመሆኑ ዲጂታል ማርኬተንግ ምንድን ነው?
ዲጂታል ማርኬቲንግ ማለት በበይነመረብ (Internet) እና ማህበራዊ ሚዲያን ( Social Media ) በመጠቀም በዝነስን የምናስተዋውቅበት መንገድ ወይም ዘዴ ነው፡፡ በአሁን ሰዓት የሰዎች ኢንተርኔትን አና የእጅ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን (Smart Phones ) አዘውተሮ ከመጠቀም አልፎ አንዱ ይህይዎት ዘይቤ ክፍል እየሁነ መምጣቱ እነዚህን ዘዴዎች ተጠቅሞ ምርት እና አገልግሎትን በበይነ መርብ ማስተዋወቅ እጅግ ተመራጭ አድርጎታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዲጂታል ማስታወቂያን ከተለመደው ባህላዊ ማስታወቂያ በተሻለ መልኩ ተመራጭ ያደረገበት ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም የተወሰኑትን ለማየት ያህል፤
• ከዋጋ አንፃር
ከዋጋ አንፃር ሲታይ ዲጂታል ማርኬቲንግ እጅግ እርካሽ ከመሆኑም በላይ በቀላሉ በማቀድ ወጪያችንን መቆጣጠር እና ባለን በጀት ላይ ብቻ ተመስርተን ማስተዋወቅ እንዲሁም ከእኛ ምርት እና አገልግሎት አንፃር ትክክለኛ ደንበኞችን በምናገኝበት መገነኛ ዘዴ ለመጠቀም የበጀት ድልድል በማድረግ ማስተዋወቅ እንችላለን፡፡ ማስታወቂያውን ካስጀመርነው በኋላ ውጤቱ ብዙም አርኪ ካለሆነ ማቋረጥ የምንችል ሲሆን በተለመደው ማስተዋወቅ ግን እንድ ጊዜ ተዋውለን ወጪ ካደረግን በኋላ በመሃል ማቋረጥ አንችልም፡፡ በባህላዊ ዘዴ ስንሰራ መጨረሻ ላይ የምርት እና አገልግሎት ሽያጫችንን ሁኔታ ገምግመን ወይም በሌላ መልኩ ከደንበኞች ያለውን መስተጋብር ቆይተን ካልተረዳን በስተቅር ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለማስተዋወቅ ያወጣነው ወጪ በትክክል የተፈለገውን ውጤት እያመጣ መሆን አለመሆኑን ማወቅ እና መረዳት ከባድ ነው፡፡ ዲጂታል ማርኬቲንግ ግን ይህንን ችግር በእጀጉ ያቃልላል፡፡
• መስተጋብር (Engagement)
በዲጂታል ማርኬቲንግ በምናደርገው ማስታወቂያ ስንት ሰው እንደተመለከተው ምን አይነት ስሜት እንዳደረባቸው በሚሰጡት አስተያየት የመውደድ ወይም የመጥላት ምልክት በቀላሉ መረዳት እንችላለን፡፡ ለሚጠይቁት ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ በመስጠት ብዥታቸውን ማጥራት ያስችለናል፡፡ ከሚሰጡት አስተያየት በመነሳት መስተካከል ካለበት እናስተካክላለን፣ ስህተት ከሆነ እናርማለን፤ የተሻለ ከሆነ አጎልብተን እናስቀጥላለን፣ ወይም ያልተረዱነት ነጥብ ካለ እና ተሳስተዋል ብልን ካሰብን ተጨማሪ ማብራሪያ እንሰጣልን፡፡ ይህም ለደንበኞች ያለንን ክብር ከማሳየትም ባሻገር ቤተሰባዊ ቅርርብ በመፍጠር ደንበኝነታችንን ቋሚ እና ዘላቂ እንዲሆን እንተጋለን፡፡ ምክነያቱም በዲጂታል ማርኬቲንግ የተግባቦት ስርዓቱ ከአንድ በኩል የሚፈስ የመልእክት ስርዓት ብቻ ሳይሆን በሁለቱም በኩል (Two Way Communication) ስልሆነ ነው
• ውጤት
በዲጂታል ማርኬቲንግ ወይም ማስታወቂያ እያንዳንዱ ተግባር ውጤታማ ከመሆኑም ባሻገር ውጤቱን ወዲያ ማወቅ መመዝን መገምገም እንችላለን፡፡ በወጤቱ መሰረት መውሰድ ያለብን እርምጃ ካለ ወዲያውን ለማስተካከል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል
• ተደራሽነት
ከተለመደው ባህላዊ ማስታወቂያ በተሻለ መልኩ ዲጂታል ማስታወቂያ (Digital Marketing) በአንድ ጊዜ ለበመላው አለም ለሚኖሩ ደንበኞች ተደራሽ ማድረግ የሚቻል ሲሆን እንደ ባህላዊ ማስታወቂያ መልእክታችንን በጅምላ ለሁሉም ተመልካች ወይም አንባቢ በድፍኑ ማስተጋባት ሳይሆን መልእክታችን መድረስ ለምንፈልገው ትክክለኛ ደንበኛ ብቻ በጥናት ላይ ተመስርተን በፆታ፣ በመኖሪያ አካባቢ በፍላጎት ወዘተ ማስተዋወቅ እንችላለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከተደራሽነት አንፃር ስናይ ባህላዊ ማስታወቂያ ለአገር ውስጥ ብቻ ማስተዋወቅ ሲያስችል ዲጂታል ግን በአለም አቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ ሰዓት ማድረስ ይቻላላ፡፡
በሌላ በኩል በተለመደው የባህላዊ ማስታወቂያ ዘዴ ተጠቅመን ምርት እና አገልግሎታችንን ስናስተዋውቅ ማስታወቂያው ለምን ያህል ለተፈለግነው ትክክለኛ ደንበኛ ተደራሽ እንደሆነ ፣ድንበኞች የእኛን ማስታወቂያ ካዩ በኋላ ምን አይነት ስሜት እንዳሳደሩ እና ምን አይነት ጥያቄ እንደተፈጠረባቸው ፣ ለምርት እና አገልግሎታችን ፍላጎት ማሳየት አለማሳየታቸውን የምናውቅበት መንገድ በጣም እድሉ የሳሳ ነው፡፡ ይህም ለማስታወቂያ የምናወጣው ወጪ ከዲጂታል ማስታወቂያ አንፃር ሲታይ ውድ ከመሆኑም በላይ ያወጣነው ወጪ ምን ያህል ውጤታማ መሆኑ አለመሆኑ ወዲያውኑ ለመለካት የምንችልበት መንገድ አለመኖሩ እንዲሁም ከደንበኞች ለሚነሳ ቅሬታ እና አስተያየት አድናቆት እና ሃሳብ በቀላሉ የምናስተናግድበት ስርዓት አለመኖሩ ዘመናዊውን የዲጂታል ማስታወቂያ ተመራጭ እያደረገው መጥቷል፡፡
ለዛሬ ይህን ያህል ካልን በቀጣይ ስለዲጂታል ማርኬቲንግ ዝርዝር ጥቅሞች፣ የተለያዩ የዲጂታል ማርኬቲንግ አይነቶችና ጥቅሞች እንዲሁም አሰራር ስትራቴጂ እና አጠቃቀም ለማሳይት እንሞክራለን፡፡ ምልዕክቱ ለሌሎችም ይደርስ ዘንድ በማጋራት Like , Share Comment በማድረግ ይተባበሩን፡፡ እናመሰግናለን!!
ለማንኛውም ዲጂታል ማርኬቲንግ አገልግሎተ እንዲሁም ነፃ ምክር በስልክ ቁጥር 0923753535 በመደወል ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን በመከታተል ማገኘት ይችላሉ፡፡ https://t.me/EdgetDigital
Telegram (http://t.me/EdgetDigital)
Edget Digital Marketing and Promotion
Let's work together for Mutual Growth!
🌐 Website Design and Development
🎯 Digital Marketing
Let's work together for Mutual Growth! 🌐 Website Design and Development 🎯 Digital Marketing 📢 Social Media Marketing and management 🏗 SEO 🖱 PPC 🏷 promotional Items 📞 0923753535 🌐 www.edgetdigital.com 📩 [email protected]