Wariye Najiib Dayiib

Wariye Najiib Dayiib ku sodhawaada bogeena si aad wararkena ula.socotaan iyo warbixinada like follow saara aad nala socotaane

01/01/2022

በመላው ዓለም የምትኖሩ ወዳጆቻችን እና ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2022 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ"ጠ/ሚ አቢይ አህመድ

ታህሳስ 23 ቀን 2014 - ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ዛሬ የገባውን የ2022 የጎርጎሳውያን አዲስ ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስት አቢይ በመልካም ምኞት መግለጫቸው "በመላው ዓለም የምትኖሩ ወዳጆቻችን እና ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2022 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ" ብለዋል በትዊተር ገፃቸው።

31/12/2021
31/12/2021

መንግሥት ከአሸባሪዎች ጋር እንደማይደራደር አስታወቀ

: አገር ዐቀፍ ምክክሩ በሕዝቦች መካከል ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር እንጂ ከአሸባሪዎች ጋር መደራደርን ታሳቢ ያደረገ አይደለም ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።

ሚኒስትር ዴኤታው በጎርጎሮሳዊያኑ 2021 የተከወኑ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮችና በቀጣይ 2022 የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከ"ሆርን ሪቪው" ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

በዚህም የውስጥ ችግሮችን መፍታት የውጭ ጫናዎችን ለመቋቋም እንደሚያስችል በማስገንዘብ ብሔራዊ መግባባት በሚለው ሐሳብ ላይ ግልጽነት ሊኖር ይገባል ብለዋል።

የታሰቡት አገራዊ የምክክር መድረኮች በሕዝቡ እና በፖለቲካ ልሂቃኑ መካከል የጋራ መግባባት ማስፈንን ታሳቢ ያደረጉ እንጂ አሸባሪ ከተባሉ አካላት ጋር መደራደር ማለት እንዳልሆነ አሳውቀዋል።

አሸባሪው ትሕነግ አፈጣጠሩ ለአመጽ እንጅ ለሰላም የሚመች እንዳልሆነ አስታውሰው የየትኛውም አገር መንግሥት ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ሲደራደር አይተን አናውቅም እኛም አንደራደርም ማለታቸውን ከብልፅግና ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

Address

Addis Ababa

Opening Hours

09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wariye Najiib Dayiib posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share