Anole Press

Anole Press

Abel Mulugeta የሚባለውን ዘፋኝ ከዚህ ቀደም የወደድኸው/ያደመጥኸው የፖለቲካ አመለካከቱ ካንተ ጋር የሚመሳሰል ስለነበር ነው እንዴ ?! ከዚህ ሰው ጋር የሚያገናኝህ እኮ ሙዚቃ ነው .....
24/07/2025

Abel Mulugeta የሚባለውን ዘፋኝ ከዚህ ቀደም የወደድኸው/ያደመጥኸው የፖለቲካ አመለካከቱ ካንተ ጋር የሚመሳሰል ስለነበር ነው እንዴ ?!
ከዚህ ሰው ጋር የሚያገናኝህ እኮ ሙዚቃ ነው ...ከተመቸህ ትሰማዋለህ ካልተመቸህ ታልፈዋለህ ...That's it .
ልክ እንዳንተ እሱም የፖለቲካ አመለካከት አለው ። ልክ እንዳንተ እሱም የሚያምንበት አስተሳሰብ አለው ። አንተም ያሻህን ማመን መብትህ ነው እሱም መብቱ ነው ። ያንተም የእርሱም መከበር አለበት ።
እንደ ፋብሪካ እቃ ካልተመሳሰልን ጠላቴ ነው ካልኸኝ original ደደብ እንደሆንህ ላስታውስህ እወዳለሁ
ሰልጥን እንጂ ...ከእኔ የፖለቲካ አመለካከት ጋር ካልተመሳሰለ ሰርቶ አይብላ ማለት ድንቁርና ነው ።

ሚኒስትሩ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው!!! የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም እንደ ወትሮ ከመደበኛ ስራቸው ወደ ቤታቸው በመ...
30/06/2025

ሚኒስትሩ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው!!!

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም እንደ ወትሮ ከመደበኛ ስራቸው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ከምሽቱ 1:00 አካባቢ መኖሪያቤታቸው የሚገኝበት ካርል አደባባይ ላይ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ነበር። በእለቱ ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ሆስፒታል አምርተው በቂ የህክምና አገልግሎት አግኝተው አሁን ላይ በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሁነቱን ለርካሽ ፖለቲካዊ ግብ ለመጠቀም ከአውድ ውጪ ባልተረጋገጠ መረጃና በአሉባልታ የሚናፈሰው የማህበራዊ ሚዲያ ዘገባ የተሳሳተና መሰረተቢስ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ሚስቴር አበክሮ ለመግለጽ ይወዳል፡፡ በቅርቡም ክቡር ሚኒስትሩ ከበቂ የጤና እርፍት ቆይታ በሃላ ወደ መደበኛ ስራ ገበታቸው የሚመለሱ መሆናቸውን በአክብሮት እንገልፃለን።

Kabajamoo Ministeerri keenya fayyaa guutuu irratti argamu!!!

Ministirri Daldalaa fi Walitti Hidhaaminsaa Naannawaa Kab.Kassaahun Goofee (Dr.) Waxabajjii 15 bara 2017 akkuma barame hojii idilee isaanii irraa gara mana isaanitti osoo deebi'aa jiruunii galgala naannoo sa'aatii 1:00 tti balaa tasaa konkolaataa naannoo Qe’ee mana jireenya isaanii addabaabayii kaarl irratti isaan muudateera. Kanarraa kan ka’e Hospitaala galuun yaala gahaa argatanii yeroo ammaa kana fayyaa guutuu irratti argamu. Haa ta'u malee galtee bu’aa siyaasaa rakasa ta’eef jecha oduun miidiyaalee hawaasaa adda addaa irratti naanna'aa jiru odeeffannoo kijibaa dhugaa irraa kan fagaate fi oduu dogongoraa ta'uu isaa Ministeerri Daldalaa fi Walitti HidhaaminsaaNaannawaa cimsee ibsuu barbaada,kabajamoo Ministeerrichis yeroo dhiyootti hojii idilee isaatti kan deebi’an ta’uu beeksisuu barbaadna.

Wondwosen Andualem Abaye
Bonsa B Negera

የብርሀን አእማድ- ፒራንዴሎ /ተፈሪ መኮንን/መጭው ጊዜ ብሩህ ነው።ባለቅኔው ‹‹ሀገር ወዳድ ይባላል›› ያለው አዋሽ አሁንም መፍሰሱን ቀጥሏል። ‹‹ሀገሬን›› ማለት የጀመረውና የሱዳን እና የሲ...
29/01/2025

የብርሀን አእማድ- ፒራንዴሎ /ተፈሪ መኮንን/

መጭው ጊዜ ብሩህ ነው።

ባለቅኔው ‹‹ሀገር ወዳድ ይባላል›› ያለው አዋሽ አሁንም መፍሰሱን ቀጥሏል። ‹‹ሀገሬን›› ማለት የጀመረውና የሱዳን እና የሲና በረሃ ሰልችቶት በኢትዮጵያ ምድር ከደጋው ጎጆ የቀለሰው አባይም በሰነፍ ልጀቹ እየተበሳጨ ቆይቶ፤ ሀገሩን ለማገልገል ደፋ ቀና ማለት ይዟል። ዓመለ ሸጋው ጊቤ... አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት እየቆጠረ፤ 'ለወገን አለኝታ ነኝ' እያለ ነው። ዋቢ ሸበሌ የሶማሌን ምድር በስስት ሲቃኝ ይታየኛል። ገናሌ መስኖ ገብቷል። ብላቴ አትክልት ያለማል። ደዴሳ እና ሙገር በበጋ ጎርፍ አስቸግረዋል። ሰላም የራቀው ተከዜ ግን ኃይል ማመንጨቱን አቋርጦ ይጎርፋል።

ወጣቱ መሪ በጎርፉ ተቸግሯል።
አንበጣ፣ ድርቅ፣ ኮሮና፣ ግሽበት፣ ጦርነት ህልሙን ሊነጥቁት ታግለውታል። በሰላም ጉዳይ ህሊናው በእጅጉ ተነዋውጧል። እንደ ንጉሥ ክርዮን ያለ ፈተና ገጥሞት፤ መከራው ሲጠናበት፤ ‹‹በአትዮጵያ አንድነት ከመጣችሁብኝ፤ አንገቴ ይቆረጣል እንጂ አይደረገም። ብዕር የጨበጠ እጃችን ክላሽ ማንሳት አይገደውም። ይህ የኖርንበት እና በብዙ የምናውቀው አካሄድ ነው›› እያለ ይብከነከናል- ይብሰከሰካል።

እንደ ባራክ ኦባማ፤ ‹‹የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ብሆንም፤ ከአሸባሪዎች ጋር አልሞዳሞድም›› ማለት ቢጀምርም፤ ደጋግሞ ወንድሞቹን ይማጻናል፤ ይለምናል። ጉዞው የግሪክ ትራጀዲ ቅርጽ ይዞ፤ የክርዮንን ፈተና ተጋፍጧል።

ልዕልት አንቲገን የቤተሰብ ፍቅር ተምሳሌ ተደርጋ የምትቀርብ ወጣት ልጃገረድ ናት። ስለ አባቷ ስለ ንጉሥ ኤዲፐስ መከራን ተቀብላለች። የመከራው ተካፋይ ሆና፤ ኦዲፐስ ዓይኑ ጠፍቶ እውር በሆነ ጊዜ መንገድ መሪው ሆናለች። አሁን ደግሞ በወንድሟ በፖሊነስ ተቸግራለች።
ፖሊነስ ህግ ጥሶ፣ የሞት ፍርድ ተፈረዶበት ተሰቅሏል። በቴብዝ ልማድ በሞት ፍርድ የተቀጣ ሰው እንዳይቀበር ህግ ይከለክላል። እርሷ ግን ስለ ወንድሟ ፍቅር ይህን ሕግ ጥሳ በድብቅ ለመቅበር ወሰነች። ከክርዮን ሰማ። 'ተይ' አላት። 'እምቢ' አለች።

ክርዮን፣ ልጁ አንቲገንን በጣም እንደሚወዳት ያውቃል። ግን አንቲገን ህግን ከጣሰች፤ ክርዮን እያለቀሰም ቢሆን ይቀጣታል። በዚህ እርምጃው ከልጁ ይቀያየማል። ስለዚህ ተጨንቋል። ‹‹ንጉሥ እንደ ፈቃዱ የሚያድር ከመሰለሽ ተሳስተሻል አንቲገን›› እያለ ይለምናታል። ‹‹ንጉሥነት ሥራዬ ነው›› ይላታል። ንጉሥ ህግ የማስከበር ግዴታ ያለበት አሽከር እንደሆነ ለማስረዳት ይጣጣራል።
አንቲገን ግን ‹‹ታሳዝነኛለህ ክርዮን …… እኔ ግን የልቤን የምሞላ ንግስት ነኝ!›› እያለች፤ ህግ ተላልፋ ወንድሟን ለመቀበር መወሰኗን ትናገራለች። በለበጣ መንፈስ፤ ‹‹ታሳዝነኛለህ ክርዮን …›› ያለችውን ይዞ፤ ‹‹ታዲያ ምነው ካዘንሽልኝ፤ ህይወትሽን ልስጥሽ ስልሽ እሺ ብትይኝ? መስኮቴ ስር ተጋድሞ የሚበሰብሰው የወንድምሽ እሬሳ ለቴብዝ ሰላም በቂ መስዋዕት አይደለም? አንቲገን፤ ልጄ ያፈቅርሻል …ደምሽን ከመስዋዕቱ እንድቀላቅለው አታድርጊኝ! የፈሰሰው ደም ይበቃናል። እኔም የሚበቃኝን ዕዳ ከፍያለሁ።"

አንቲገን ሸብረክ አትልም። ‹‹አይምሰልህ! … አሜን አልክ! ንጉስ ሆንክ! እናም ዕድሜ ልክህን መስዋዕትህን ስታቀርብ፣ ዕዳህን ስትገፈግፍ ትኖራለህ። አያበቃም!›› እያለች በእምቢታዋ ጸናች። ክርዮን በጣም አዝኖና ተቆጥቶ፤
‹‹… እንዴት አትረጂኝም አንቲገን። ይኸው እኔ ልረዳሽ እጥር የለም?! ሀገሪቱ በሁከት ተንጣ የሚደርስላት ባጣች በዚያ ሰዓት፤ የህዝቧን አደራ' እሺ ' ብሎ የሚቀበል አንድ ሰው የግድ ያስፈልግ ነበር። አንድ የሆነ ሰው ይህን ሸክም "አሜን" ብሎ ተቀብሎ፤ ሁከት በሚንጣት መርከብ ፊት ቆሞ፤ ሊመራት ግድ ነበር!

‹‹መርከቧ ከሥሯ ሺህ ቦታ ተሸንቁራ፤ ከወለል እስከ ሠገነት በወንጀል …በድህነትና በድንቁርና ታፍና ነው ያገኘኋት! መዘውሯ ከነፋሱ ጋር ይዋልላል። … ሠራተኞቿ ሊያቀኗት አልፈለጉም። … ይልቅ እንደ ጠላት ጓዳ ይመዘብሯት ነበር… መኮንኖቿ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ማምለጫ ጀልባ ለመያዝ ሲሽቀዳደሙ፤ ሰዎቿንና ሀብቷን ይዛ ለመስጠም ስታጣጥር ነበር ያገኘኋት! እናም ይህ ሰዓት በ‹እሺ› እና ‹እምቢ› ምንነት የቃላት ጨዋታ ለመጫወት የሚቻልበት ሰዓት ነው?! 'ንጉስ መሆን ጥቅሙ፤ …. ንጉስ መሆን ጉዳቱ' ብሎ የግል ሀሳብን ግራ ቀኝ የሚያዳምጡበት ሰዓት ነው ወይ? ....
‹‹ሳታቅማሚ ዘለሽ መሪውን ትጨብጫለሽ፤ መርከቧን ታቀኛለሽ፤ ማዕበሉን ትታገያለሽ! ጮኸሽ ትዕዛዝ ትሰጫለሽ። አንዱ የመርከቧን ህልውና ለመፈታተን ከመጣ፤ በቀጥታ ትተኩሻለሽ! ቀጥታ ትተኩሻለሽ! … እገሌ አትይውም። ስም የለሽ፤ መልክ የለሽ ነው። በጆሮሽ እንደሚያፏጨው ንፋስ፤ መርከቧን እንደሚንጣት ሞገድ፣ ስም የለሽ ምጣት ነው! ታዲያ ስትተኩሽ… በጥይትሽ ተመትቶ የወደቀው ሰው፤ ትናንት ጠምቶሽ ውሃ ያጠጣሽ ሰው ይሆናል። አለያም ደግፎሽ ከሠገነቱ ያወጣሽ ጎበዝ ይሆናል። … ግን ስም የለውም። ማንም ስም የለውም… ።! አንቺ መሪውን የጨበጥሽው እንኳን ስም የለሽም። መርከቢቷ ብቻ ናት ስም ያላት… ሀገር ብቻ ናት ስም ያላት!... እ…። አሁንስ ገባሽ?፤ ተረዳሽኝ!?›› ይላታል።

አንቲገን ግን፤ ‹‹ልረዳህ አይደለም እዚህ የመጣሁት። ይኸ ያልከው ሁሉ ለአንተ ይጠቅምህ ይሆናል። እኔ ግን እዚህ የመጣሁት እምቢታየን ለመግለጽ ብቻ ነው›› ትለዋች።
‹‹እምቢታ ቀላል ነው፣ አንቲገን። እምቢታ ቀላል ነው። ዕዳው ሞት ቢሆን እንኳን፣ እምቢታ ቀላል ነው። ቁጭ ብሎ የሚመጣውን መጠበቅ ብቻ ነው። ያ የሰነፍ ሰው ድርሻ ነው። እሺ ስትይ ግን፣ ላብሽን ማንጠፍጠፍ፤ እጅሽን ጠቅልለሽ፤ እስከ አንገትሽ ድረስ በህይወት ማጥ ውስጥ መዘፈቅ ይኖርብሻል›› ይላታል።

እንደ ሴቴ ሸረሪት ጽንስ ራሱን በራሱ የሚውጠው፤ ከውቂያኖስ መግባት የሚመኘው አዋሽ፤ አሁን ወደ ብርሃን መውጫ በእርጋታ እየፈሰሰ ነው። አባይ ጉባ ተሰናድቶ፤ ብርሃን እያፈሰሰ ነው። ጊቤ ኮሽታ ሳያሰማ፤ በኮይሻ ብልጽግናን በጸጥታ እየተጣራ ነው። የኢትዮጵያ ወንዞች፤ ‹‹የኢኮኖሚ ዋልታ፤ ቡና ቡና›› በሚሉት የጅማዎቹ ህጻናት ዜማ ዚቅ ‹‹ስንዴ ስንዴ›› እያሉ ነው።

መጭው ጊዜ ብሩህ ነው።
Abiy Ahmed Ali
Sandokan Debebe Jemaneh
Kassahun Gofe Balami
Addisu Arega Kitessa
Wondwosen Andualem Abaye
Negera Duguma Gutema
Haftay Gebre-Egziabher
Ashinie Astin
Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ
Jantirar Abay - ጃንጥራር አባይ

ሀሳብን ከመፍራት- ሀሳብ ወደማፍራት ስትሄድ ከቃል ወደ ባህል ታድጋለህ።

 #የኮርደር _ልማት_በሻሸመኔ👉ባለአምስት በሯን ከተማ ባለብዙ ውበት እና ባለብዙ እድገት የሚያደርግ ስርነቀል ልማት።👉የህዝብ ተባባሪነት + የአመራር ቁርጠኝነት = የሻሽቱ የከፍታ ሰገነት ❤
19/08/2024

#የኮርደር _ልማት_በሻሸመኔ
👉ባለአምስት በሯን ከተማ ባለብዙ ውበት እና ባለብዙ እድገት የሚያደርግ ስርነቀል ልማት።
👉የህዝብ ተባባሪነት + የአመራር ቁርጠኝነት = የሻሽቱ የከፍታ ሰገነት ❤

የነሀሴ ወር 2016 ዓም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ሃምሌ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግስትተወስኗል:: በመሆኑም የነዳጅ ማደያዎች ካልተገ...
06/08/2024

የነሀሴ ወር 2016 ዓም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ሃምሌ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግስትተወስኗል:: በመሆኑም የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ታዘዋል:: በየደረጃው የሚገኝ የንግድ መዋቅራችን በነዳጅ ስርጭትና ሽያጭ ዙሪያ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ስራዎች ተጀምረዋል::

The government has decided that the retail sale of petroleum products will continue with the price of July without any increase in prices. Therefore, it has been ordered that petrol stations should implement without unnecessary product storage and increase in prices. Our Trade structure at every level should have strict control and monitoring of petroleum distribution and sales. And they have begun.

Kassahu Gofe (phd)

ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)  ምክንያታዊ...
03/08/2024

ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

ከብሔራዊ የንግድ ተቋማት የፀረ ንግድና ገበያ መቆጣጠር የጋራ ኮሚቴ አባላት ጋር የህገ ወጥ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪና ምርትን የማከማቸት ህገ ወጥ ተግባራት ዙሪያ ሰፊ ውይይቶች እየተከናወኑ ሲሆን በየክልሉ እየተተገበሩ ያሉ ተግባራት አፈፃፀምም በየእለቱ በዝርዝር እየተገመገሙ ነው።

በሪፖርቱ እጅግ አበረታች የሆነ ጅምር የህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙና በሚቀጥሉት ቀናትም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።

ለአብነት በትላንትናው ቀን ብቻ 324 የንግድ ድርጅቶች ማሰጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን 542 የንግድ ተቋማት ታሽገው የንግድ ፍቃዳቸው እንዲታገድ ተደርጓል። በቀጣይም የንግዱ ማህበረሰብ ህጋዊነትን ብቻ ተከትሎ ሊሰራ ይገባል።

አሁንም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል።የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያውን ተከትሎ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።ሙሉ በመሉ ወደ ትግበራ የገባውን የማክሮ ኢኮ...
03/08/2024

አሁንም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያውን ተከትሎ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

ሙሉ በመሉ ወደ ትግበራ የገባውን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ ምርት የሚደብቁ እና ያልተገባ ዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለኢቲቪ አስታውቋል።

ማሻሻያውን ተከትሎ ያልተገባ ጥቅምን ፍለጋ በሚንቀሳቀሱ ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን እና ይህም ቀጣይነት እንደሚኖረው ነው ቢሮው ያስታወቀው።

በተመሳሳይ፥ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያውን ተከትሎ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ በሦስት ከተሞች የሚገኙ 30 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ይህን መሰል ድርጊት ላይ በሚሰማሩ ነጋዴዎች ላይ በቅድሚያ የማስተማር፣ በመቀጠልም ሕጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለፅ፣ ሌሎችም ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቡ ነው ቢሮው ያሳሰበው።

"የዋጋ ንረቱን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዋጋ ንረቱን...
04/07/2024

"የዋጋ ንረቱን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዋጋ ንረቱን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቀ ማድረግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ.ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ተገኝተው ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ኾኖ ቀጥሏል ብለዋል፡፡ በአንዳንድ ሀገራት ከ60 በመቶ በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ መኾኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

በኢትዮጵያም የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግሥት በርካታ ኢንሸቲቮችን ቀርጾ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡ በተለይ የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

ምርታማነትን ለማሻሻል እየሠራን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘንድሮው ዓመት ከዓለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ከ100 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት መሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም መንግሥት 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በመተው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

የኑሮ ውድነቱ በዜጎቻችን ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለማቃለል እየሠራን ነው ብለዋል። በዚህም የዋጋ ንረቱን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቀ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Anole Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share