Global News

Global News ተአማኒና ግልፅ መረጃዎችን በፍጥነት እናደርሳለን

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በምክር ቤቶች የጋራ ስብስባ ያደረጉት ንግግር የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው ተባለጥቅምት 8/2015  የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30፣ 2...
18/10/2022

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በምክር ቤቶች የጋራ ስብስባ ያደረጉት ንግግር የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው ተባለ

ጥቅምት 8/2015 የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30፣ 2015 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

በዛሬው ዕለት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብስባ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን አዳምጧል፡፡

የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ የድጋፍ ሞሽኑን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት የፕሬዚዳንቷ የመክፈቻ ንግግር የፌዴራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የዳሰሰና የንግግሩ ይዘት መንግስት በ2015 ሊያከናውናቸው የሚገቡ ዐበይት ተግባራትን ያካተተ መሆኑን አስታውሰዋል።

የድጋፍ ሞሽኑ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት ተደርጎበት የሚጸድቅ ሲሆን ውይይት የሚደረግበት ጊዜ ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ አስታውቀዋል፡፡

የምከር ቤቱ 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ መጽደቁን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

ፈተናው ያለምንም ችግር በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀጥቅምት 8/2015    የ12ኛ ክፍል 2ኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ያለምንም ችግር በሁሉም የፈተና...
18/10/2022

ፈተናው ያለምንም ችግር በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

ጥቅምት 8/2015 የ12ኛ ክፍል 2ኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ያለምንም ችግር በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በሰላም መጀመሩን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።

ፈተናው የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው መርኃ ግብር መሠረት እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ "ከመጀመሪያው ዙር ተምረን በርካታ ነገሮችን ስላስተካከልን የዚህ ዙር ፈተና በተጀመረበት መልኩ እንደሚጠናቀቅ ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።

የ12ኛ ክፍል የ2ኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መሠጠት የተጀመረ ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ፈተናውን በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀምረዋል።

ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ እንዲፈተኑ መደረጉ በትምህርት ሥርዓቱ ያለውን የሞራል ስብራት የሚጠግን መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ይህም ከፍተኛ ትርጉም እንዳለው ማኅበረሰቡም በሚገባ የተረዳ እና የደገፈው በመሆኑ በጣም ደስተኞች ነን ብለዋል።

የ2ኛው ዙር ፈተና ከጅምሩ ምንም ችግር አላየንበትም ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይ በፈተና ሥርዓቱ ያሉ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ቀርፈን ወደ አዲስ ምዕራፍ እንገባለን ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስፈተነ ይገኛል።

የ2ኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

18/10/2022

እንኳን ወደ ፔጃችን መጡ በዚህ ፔጅ ላይ አዳዲስ ወቅታዊና ታአማኒ ሀገራዊ ና አለማቀፍ ዜናዎችን ያገኛሉ፡፡

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Telephone

+251925899632

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Global News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Global News:

Share