Dada Media House

Dada Media House እንቅጭ እንቅጩን

(የግል አስተያየት) ጸሐፊዋ አበባ ብርሃኑ "እስኪ ለድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ደግሞ  ፍቅር ስጡት" ትላለች።  ጸሐፊዋ ትቀጥልና "የዚህ  ድምፃዊ  እጮኛ  ቀነኒ አዱኛ : አብረው ከሚኖሩበት አ...
18/06/2025

(የግል አስተያየት) ጸሐፊዋ አበባ ብርሃኑ "እስኪ ለድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ደግሞ ፍቅር ስጡት" ትላለች። ጸሐፊዋ ትቀጥልና "የዚህ ድምፃዊ እጮኛ ቀነኒ አዱኛ : አብረው ከሚኖሩበት አፓርታማ ላይ እራሷን ወርውራ እንዳጠፋች ለፍርድ ቤት የተናገረው ድምፃዊው: በዚህም ሞቷ ምክኒያት ታስሮ የነበረና ሰሞኑን ደግሞ ከእስር እንደተለቀቀ ይታወቃል።
( የችሎት ሂደቱ ለማንኛውም ሚዲያ ዝግ በመደረጉ እና ሌሎች ምክንያቶች --- ለጊዜው ምንም ልንል አልቻልንም)

ቀነኒ አዱኛ:- ነፍስ ይማር!
እስኪ ለድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ደግሞ ፍቅር ስጡት።"

🚨በጋዛ የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት ! የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ ላይ በሁለት ቀናት ውስጥ ቢያንስ 89 ፍልስጤማውያንን መግደላቸው ተነገረ ።የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ ላይ በሁለት...
18/06/2025

🚨በጋዛ የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት !

የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ ላይ በሁለት ቀናት ውስጥ ቢያንስ 89 ፍልስጤማውያንን መግደላቸው ተነገረ ።

የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ ላይ በሁለት ቀናት ውስጥ ቢያንስ 89 ፍልስጤማውያንን ገድለዋል፣ አብዛኛዎቹ በእርዳታ ማከፋፈያ ማዕከላት ለምግብ ሲሰለፉ በጥይት ተደብድበዋል ወይም ተተኩሶባቸው መሆኑን የዘገበው The New Arab Staff የዜና ወኪል ነዉ ።

እንደ ዘገባዉ ከሆነ እሮብ እለት ብቻ በራፋህ ፣ካን ዮኒስ ፣ጋዛ ከተማ እና የመሀል ማጋዚ የስደተኞች መጠለያ ካምፕን ጨምሮ 32 ተጨማሪ በጋዛ በተደረጉ ጥቃቶች እና ተኩስ ተገድለዋል። ብሏል ።

ማክሰኞ እለትም በካን ዮኒስ ዋና መንገድ ላይ የጋዛ ሰብአዊ ፋውንዴሽን (GHF) ዱቄት ለመቀበል የተሰበሰበ ህዝብ ላይ የእስራኤል ታንኮች፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ከባድ መትረየስ ባደረሰችዉ ጥቃት ከ70 በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን ገልጿል ።

የጋዛ ሲቪል መከላከያ ቃል አቀባይ ማህሙድ ባሳል እንዳሉት በጥቃቱ ከ200 በላይ ቆስለዋል።

"የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወደ ዜጎቹ ተኮሱ።ከደቂቃዎች በኋላ የእስራኤል ታንኮች በዜጎቹ ላይ ብዙ ጥይቶችን በመተኮሳቸው ብዙ ሰማዕታት እና ቆስለዋል" ብሏል።

በጋዛ ከተማ ደቡባዊ ክፍል በእስራኤል በተያዘችው ኔትዛሪም ኮሪደር አቅራቢያ 11 ንፁሃን ዜጎች በእስራኤል በተኩስ መገደላቸውን የተገለፀ ሲሆን የ38 አመቱ ሰኢድ አቡ ሊባ “ህፃናትን ጨምሮ በደርዘን የሚቆጠሩ ሲቪሎች ተገድለዋል፣ እና ማንም ሊረዳውም ሆነ ህይወት ሊያድን አይችልም” ሲል ለአልጀዚራ ተናግሯል።ሌላው በህይወት የተረፈው መሀመድ አቡ ቀሽፋ "በተአምር ተርፌያለሁ" ብሏል።

ከኦክቶበር 7 2023 ጀምሮ፣ እስራኤል በጋዛ ላይ ያደረሰችው ጥቃት ከ185,000 በላይ ሰዎችን ገድሏል፣ የጋዛ ባለስልጣናት እንደሚሉት፣ አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው። ከ11,000 በላይ የሚሆኑት ከፍርስራሹ ስር ጠፍተዋል።

ማክሰኞ የዓለም ጤና ድርጅት የነዳጅ እጥረት ቀድሞውኑ የተደበደበውን የጋዛን የጤና ዘርፍ እያሽመደመደ መሆኑን አስጠንቅቋል ።
የሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲዎች የተፈቀደው የተወሰነ እርዳታ የጋዛን 2.3 ሚሊዮን ሰዎች ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉን አስጠንቅቀዋል ።

የመንግስታቱ ድርጅት ምክትል ቃል አቀባይ ፋርሃን ሃቅ በበኩላቸዉ ይህ ክስ “ተቀባይነት የለውም” ብለዋል።

“አሜሪካ ጦርነቱን ብትቀላቀል የኃያልነቷ ታሪክ የዛኑ ቀን ያበቃል" ▶️አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አሜሪካ ጦርነቱን ብትቀላቀል የኃያልነቷ ታሪክ የዛኑ ቀን ያበቃል ሲሉ የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ኻ...
18/06/2025

“አሜሪካ ጦርነቱን ብትቀላቀል የኃያልነቷ ታሪክ የዛኑ ቀን ያበቃል"

▶️አያቶላህ አሊ ኻሚኒ

አሜሪካ ጦርነቱን ብትቀላቀል የኃያልነቷ ታሪክ የዛኑ ቀን ያበቃል ሲሉ የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ገለጹ።

የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላሂ አሊ ኻሚኒ ዛሬ በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት፤ በኃይል አልያም በጉልበት የሚመጣ ጦርነትም ይሁን ሰላም አንቀበልም ብለዋል።

አል አረቢያ እንደዘገበው፤ ኢራን በታሪኳ በጉልበት ለመጣ ኃይል እጅ ሰጥታ አታውቅም በማለት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እጅ መስጠት አለባት ሲሉ ላስተላለፉት መልዕክት ምላሽ ሰጥተዋል።

"የኢራንን ታሪክ ሚያቁ ሰዎች ኢራን በማስፈራራት ለመጣ ኃይል አንበርክካ እንጂ ተንበርክካ እንደማታቅ ይረዳሉ" ብለዋል።

ኻሚኒ በመቀጠልም "እስራኤል ከባድ ስህተት ሰርታለች እና መቀጣት አለባት። የአየር ክልላችንን ስለጣሰች እስራኤልን ይቅር አንልም" ብለዋል።

#ኢራን #አሜሪካ #ትራምፕ #እስራኤል

ቻይና፣ ትራምፕ በኢራን እና በእስራኤል ግጭት ላይ ቤንዚን እየጨመሩ ነው አለች ቻይና፣ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ዕለት በእስራኤል እና በኢራን መካከል እየተባባሰ ባለው ግጭ...
17/06/2025

ቻይና፣ ትራምፕ በኢራን እና በእስራኤል ግጭት ላይ ቤንዚን እየጨመሩ ነው አለች

ቻይና፣ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ዕለት በእስራኤል እና በኢራን መካከል እየተባባሰ ባለው ግጭት “በእሳት ላይ ቤንዚን ጨምረዋል” ስትል ፕሬዝዳንቱን ወቅሳለች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጉኦ ጂያኩን በትራምፕ መግለጫ ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፤ እሳቱን ማቀጣጠል፣ ማገዶ መጨመር፣ ማስፈራራት እና ግፊት መጨመር ሁኔታውን ለማረጋጋት አይረዳም።

ይልቁንም ግጭቱን ያባብሰዋል ማለታቸውን አናዶሉ እና አል አረቢያ ዘግበዋል።

ትራምፕ “እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት እንደማትቀንስ ነው የማውቀው” ሲሉ ኢራን እና እስራኤል መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ እየፈለጉ እንዳልሆነ ተናግረው ነበር።

ቢቢሲ ዛሬ ከሰዓት ባወጣወ ዘገባ ደግሞ ጭራሹን ትራምፕ፣ ኢራንና እስራኤል ስምምነት ላይ እንዲደርሱ እንደማይፈልጉ አሳውቀዋል።

ለአምስተኛው ቀን እስራኤል እና ኢራን የአየር እና የሚሳኤል ጥቃት መለዋወጣቸውን የቀጠሉ ሲሆን፤ ቴል አቪቭ በተለያዩ የኢራን ጦር ሃይሎች እና ወሳኝ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ስትሰነዝር ኢራን በበርካታ የእስራኤል ከተሞች የባስቲክ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ቀጥላለች።

ጥቃቶቹ በሁለቱም ሀገራት በሰው ሕይወት፣ በመሰረተ ልማት እና በወታደራዊ ተቋማት ላይ ብርቱ ጉዳት ያደረሱ ነበሩ።


#ቻይና #አሜሪካ

Israeli rescue crews in Ramat Gan, a city on the eastern edge of Tel Aviv, picked through rubble on June 14 after Iran’s...
14/06/2025

Israeli rescue crews in Ramat Gan, a city on the eastern edge of Tel Aviv, picked through rubble on June 14 after Iran’s retaliatory missile and drone strikes, triggered by Israel’s attack on Iranian soil in the early hours of June 13.

Israel’s air strikes on June 13 killed at least 78 people, including 20 children and over 300 were injured in Iran, while Iran’s retaliation killed at least 3 people and injured over 91 in Israel.

ዝም ብለህ ሥራ!ያስነሣህ ያውቅሃል፣ውድህ ያልቅሃል፣ሥራህ ይገልጥሃል፣ያደለው ያይሃል፤ዝም ብለህ ሥራይች ሀገር መች አጣች ሺ ተሥፋዎች አውሪ፣ይች ሀገር መች አጣች አቃቂር ነጋሪ፣ይች ሀገር መች...
13/09/2024

ዝም ብለህ ሥራ!

ያስነሣህ ያውቅሃል፣
ውድህ ያልቅሃል፣
ሥራህ ይገልጥሃል፣
ያደለው ያይሃል፤

ዝም ብለህ ሥራ

ይች ሀገር መች አጣች ሺ ተሥፋዎች አውሪ፣
ይች ሀገር መች አጣች አቃቂር ነጋሪ፣
ይች ሀገር መች አጣች ቱማታ ቀማሪ፣
ይች ሀገር መች አጣች ተችና አነዋሪ፣

ዝም ብለህ ሥራ!

ለሞተው ሕዳሴ ካሳየህ ትንሣኤ፣
ግንባሩ ተንዶ ከሆነ ጉባኤ፣
ከተማው ከሞቀ በሦስት ወር ሱባኤ፣
ሥራ አይቶ ከጮኸ የሠናይ ጸላዔ፣

ዝም ብለህ ሥራ!

ወንጪና ሐላላ፣ እንጦጦ ጎርጎራ፣
ባያገኝም ሰሚ ሲናገር ሲጣራ፣
ዓባይ ስሙኝ ቢልም አሻቅቦ እያየ ድልድይ እንደ ጣራ፣
ዓለም ዝም ቢልም ለአረንጓዴ ዐሻራ፣

ዝም ብለህ ሥራ!

ሕዝብ እንደሁ ገብቶታል ዕሴት በቁዔቱ፣
ቢያደነቁረውም ልሂቅ በየዓይነቱ፣
ያየውን ጭላንጭል ይሻዋል በብርቱ፣
አይቷልና ፍሬ በዓይኑ በብረቱ፣

ዝም ብለህ ሥራ!

በዘመንህ ካየህ ኃያላን ሲወድቁ፣
ብርቱዎች ነን ያሉት ሲፈጩ ሲደቁ፣
ለክፉ ያበሩት ሲሰነጣጠቁ፣
ሩቆቹ ቀርበው ቅርቦቹ ሲርቁ፣

ዝም ብለህ ሥራ!

ያሳይሃል ገና
ሲናድ ያ ተራራ፣
ሲሞላ ጎተራ፣
ችግኙ ሲያፈራ፣
ኢትዮጵያ ስትመራ፣

ዝም ብለህ ሥራ!

አትስማ ፈጽሞ
አንበሳው ቢያጓራ፣
ቀበሮው ቢያቁራራ፣
ጭልፊቱ ቢያጭራራ፣
ዘንዶው ቢያስፈራራ፣
ሁሌም ስለሚበልጥ ያለው ካንተ ጋራ፤

ዝም ብለህ ሥራ!

Via Daniel kibret

🗣️ “Is Haaland the most complete centre-forward we have ever seen in this game?”, BeIN Sports asked Pep Guardiola after ...
24/08/2024

🗣️ “Is Haaland the most complete centre-forward we have ever seen in this game?”, BeIN Sports asked Pep Guardiola after the hat-trick…

🇦🇷 Pep Guardiola: “The most complete centre forward ever seen is Lionel Messi”, his reply with smile on face.

🚨 𝐁𝐑𝐄𝐀𝐊𝐈𝐍𝐆: Mikel Merino, on his way to London today to complete Arsenal move! 🔴⚪️Spanish midfielder saying goodbye to h...
23/08/2024

🚨 𝐁𝐑𝐄𝐀𝐊𝐈𝐍𝐆: Mikel Merino, on his way to London today to complete Arsenal move! 🔴⚪️

Spanish midfielder saying goodbye to his teammates and Real Sociedad staff ahead of flying to England 🛫

Medical tests booked for Merino then he will sign four year contract with an option for furter season, 2029.

𝑯𝒆’𝒔 𝒄𝒐𝒎𝒊𝒏𝒈! 🛩️🇪🇸

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dada Media House posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share