E.C.N

E.C.N Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from E.C.N, TV Channel, Lideta, Addis Ababa.

We are Ethiopian Community Network a new media outlet, with the dreams and goal of achieving intercultural synchronization by filling the information gap in the current ERA

ግንቦት እና ኢትዮጵያ
26/05/2025

ግንቦት እና ኢትዮጵያ

#ኢቢሲ #ኢቲቪ - Media Network Tv...

26/05/2025

አፍሪካ የውበት አርማ .....የህብረብሔራዊነት መገለጫ

የአፍሪካ ቀን በትላንትላው ዕለት ግንቦት 17 ቀን /2017 ዓ .ም በእራስ አምባ ሆቴል ተከበረ።

አፍሪካ የራሷ ቀለምና ውበት ያላት አሀጉር ስትሆን በአፍሪካ አሀጉር ውስጥ እጅግ ብዛት ያላቸው ሀገራት ሲኖሩ በአሀጉሪቱ ውስጥም የተለያ ቋንቋዎች ፣ ሀይማኖቶች ፣ባህሎች ይገኛሉ።

ልዩነት ውበታችን ነው የምትለው የፍሪካ አሀጉር በቀለም በቋንቋ የተሳሰረ ማንነት ያላት ሀጉር ናት።
በቀኝ ገዥዎች ቅርምት ጊዜ የአፍሪካ አሀጉር በአውሮፓውያን ተወራ በብዙ መልኩ ያላትን አንፁር ሀብት ማጣቷ የማይዘነጋ ነው።

ፖርቹጋልን ተከትለው ወደ አሀጉሪቱ የገቡት እንግሊዝና ፈረንሳይ የከፋፍለህ ግዛ መርህን በመከተል በቋንቋቸው በብሔራቸው በሀይማኖታቸው እንዲሸማቀቁ በማድረግ ለዘመናት ተፅኖ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ከአደዋ ጦርነት በኋላ በፍሪካ ምድር የነፃነት ነፀብራቅ ያበራ ሲሆን ከዚሁ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፀንሳሽነት የአፍሪካ ህብረት በ1912 መመስረቱን ተከትሎ አፍሪካውያን ስለ ማንነታቸው በነፃነት በልበ ሙሉነት መናገር ችለዋል።
የአፍሪካ አባት ጉንቱ ዲፕሎማት እየተባሉ የሚፀሩት ቀዳማዊ ሀይለስላሴ በተለይም የሞኖሮቢያና የካዛብላንካን ቡድንን በማስማማት አፍሪካ አንድነች አንድነታችን ያስፈልገናል በማለት የአፍሪካ ህብረት እንዲመሰረት ጉልህ ሚናን ተጫውተዋል።

በአፍሪካ ህብረት መመስረት አስተዋፆ የነበራቸው ጃንሆይ ብቻ ሳይሆኑ የስቻው ቀኝ ክንድ የነበረው ከሀረርጌ የገጠሪቱ ክፍል የተገኘው አቶ ከተማ ይፍርም ይገኝበታል።

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ታምቦ ሜቤኬ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ሲነሳ አቶ ከተማ ይፍሩን ሳያነሱ ማለፍ አይቻልም ይላሉ።
የአቶ ከተማ ይፍሩ አስተዋፆኦ በአፍሪካ ህብረት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የኢኪኖሚ ኮሚሽን እንዲመሰረትና መቀመጫውም አዲስ አበባ እንዲሆን አድርጓዋል።

በትላንትላው ዕለትም ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እራስ አምባ ሆቴል ከተለያዩ ሀገራት የመጡ እንግዶች በተገኙበት የአፍሪካ ቀን በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በመልካሙ አዲስ

ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

20/05/2025

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ቅርሶችን የማስመለስ ስራውን አጠናክሮ እየስራ እንደሆነ ገለፀ።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ቅርሶችን የማልማት የመንከባከብ እንዲሁም ከሰው ሰራሽና ከተፈጥሮአዊ አደጋዎች መጠበቅ ቅርሶችን በሳይንሳዊ መንገድ የመመዝገብና የመቆጣጠር ቅርሶች ጉዳት ሲደርስባቸው የመጠገን ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው።
ቅርሶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ ሀላፊነትን አንግቦ የተቋቋመው ተቋም 81 አመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ ተቋም ነው።
ባለ ስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት ለመወጣት የተለያዩ ጥረቶችን ያደረገ ሲሆን በጥረቶችም አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል ከእነዚህ መካከልም 12 የሚዳሰሱ ቋሚ ቅርሶችና 6 የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች በዩንስኮ የቅርስ ዝርዝር ውስጥ በማስመዝገብ በአፍሪካ የቀዳሚነትን ደረጃ መያዝ ተችሏል።
በተጨማሪም በርካታ ቅርሶችን የመጠገንና በተለዩዩ ጊዚያት በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር የወጡ ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረቶችም እየተደረጉ ነው።
ከ30 በላይ ቅርሶች እሴቶቻቸውን ጠብቀው መጠገን የተቻለ ሲሆን የቅርስ ምርምር ፈቃድ አሰጣጥና የቅርስ ስብስቦችን መረጃ ወደ ዲጂታል አገልግሎት ለመለወጥ የተለያዩ ተግባራትን የተደረጉ ሲሆን ከ30 በላይ የቅርስ ምርምሮችን ፈቃድ በመስጠት ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።
ባለ ስልጣን መስሪያ ቤቱ የሀገር ውስጥ ቅርሶችን ከመጠበቅና ከመንከባከብ ባሻገር በውጪ ሀገር ያሉ የኢትዮጵያ ቅርሶችን የማስመልስ ስራውን አጠናክሮ እየሰራ ይገኛል።
ከዚሁም ባሻገር ቅርሶች በማህበራዊ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች አስተዋፆ እንዲኖራቸው እየተሰራ እንደሆነም ባለ ስልጣን መስሪያ ቤቱ አሰታውቋል።
በ2016 ዓ.ም ተቋሙ የተመሰረተበትን 80ኛ አመት ጉዞ መሰረት በማድረግ የመጀመሪያውን የቅርስ ምርምር ጉባዩ አካሂዷል።
በዘንድሮው አመት የሚካሔደው ሁለተኛው የቅርስ ምርምር ጉባኤ በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 14-15/2017 በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ግቢ ይካሔዳል።

ለዘገባው ፦ መልካሙ አዲስ

ግንቦት 12 ቀን 09/2017 ዓ.ም

16/05/2025

(ECN) Ethiopian Community Network Telvsion & Radio. የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ኔትወርክ ቴሌቪዥን እና ራዲዬ አገልግሎት ድርጅ መረጃዎቻችንን በቴሌግራም በዩቲዩብ በዋትሳፕ ይከታተሉን ። ቴሌግራም ገጽ፡ (ኢሲኤን)https://t.me/ECNTvForU ዩቲዩብ ገጽ ፡https://youtube.com/?si=SPvn1EMPHjIOBOSv

በዋትሳፕ ገጽ፡https://chat.whatsapp.com/IvPipQnHZbfDetj26wEL0Z የሁላችንም ድምፅ!

21/04/2023

Eid Mubarak to all Muslim followers! I hope you had a blessed month of Ramadan and enjoyed the festivities of Eid al-Fitr. We want to share with you best wis...

Address

Lideta
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when E.C.N posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category