Gaammo Media House/ጋሞ ሚዲያ ሐወስ

Gaammo Media House/ጋሞ ሚዲያ ሐወስ It would introduce 1stly about Gaammo socially,culturally,politically ,economically and other all wel

ሰበር አስደሳች ዜና! የጋሞዎች ጋራ በዓል ሌላሼ/ዮዮዮ ዮዮዮ ማስቃላ ዘመን መለወጫ ምደምቁበት ዱቡሻ መሠረት ልጣል ነው❤💪🖤‼️*******************በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልል ጋሞ ዞን...
04/01/2025

ሰበር አስደሳች ዜና! የጋሞዎች ጋራ በዓል ሌላሼ/ዮዮዮ ዮዮዮ ማስቃላ ዘመን መለወጫ ምደምቁበት ዱቡሻ መሠረት ልጣል ነው❤💪🖤‼️
*******************
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልል ጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳና ከምባ ወረዳ ቀበሌያት ጋራ ሲያከብሩ የቆዩበት ጥንታዊው የጮዬ ሶዴ ደሬዎች ዘመን መለወጫ ሎላሼ/ዮዮ ዮዮ ማስቃላ ሽኝት በዓል ለማክበር የተጋበዙ የደ/ቡ/ኢትዮ ክልል ር/መስተዳደር ክቡር፣የጋሞ ዞን ር/መስተዳድር ክቡ አባይነህ አበራና ሥራ አስፈፃሚዎች፣ሠላም ሰባኪና በቅርብ ግዜ በዘርፉ ተሸላሚ አባቶች፣ሶዴ ደሬዎች ባህላዊ ንጉስ የሆኑ ካዎ ታደሰ ዘውዴን ጨምሮ ከወረዳ መዋቅር እስከ ክልላችን በተለያዩ ኃላፊነት ደረጃዎች የሚገኙ እንገዳዎች በተገኙበት፤

ጋሞ 42'ቱ ደሬዎች ጋራ አንድ ምያደርገን ጋራ ድቡሻ ሎላሼ/ዮዮ ዮዮዮ ማስቃላ በዓል ማከበሪያ ባህላዊ አደባባይ አደረሽ እንደገነባ በሪዕሰ መስተዳደራችን መሠረቸ ድንጋይ እንደምጣል በውስጥ መስመር ግልፅ መረጃ ምንጮች አድርሶናል❤💪🖤

በዓሉን ለማክበር በዞኑ መንግስት ወጪና በወረዳው መንግስት በኩል የተለያዩ ሥራዎች በትኩረት እየተሠሩ እንዳለም ሠምተናል፤እንዲሁም ባሁኑ ሰዓት ከቦታው እየዘገቡ ካሉት የጋሞ ቴቪ'ን ጨሞሮ የተለያዩ ማ/ሚዲያ ባለቤቶች ተገኝቶ ይበልጥ እንደምያደምቁም ይጠበቃል።

ዮዮዮዮ ዮዮዮዮ ጋሞዎች ሎላሼ/ማስቃላ
Ane wontto ha yiite Sode Fange Dubusha Siiqon gaagos,kaw'oo,Zaruman Layththa gaththanaw issippe nu Bayra Aawatan Xoosse wosissoos ❤🎂🖤‼️‼️

Via ZuullaZuulla Kamma Kaarana

30/12/2024
“ጮዬ ማስቃላ” "የጋሞ ዞን ባሕላዊ እሴቶች ከሆኑ አንዱና ዋነኛው የ" ዮ ጋሞ ማስቃላ” ዘመን መለወጫ (laytha laame) አንዱ ነው።“ጮዬ ማስቃላ” በጋሞ ብሔረሰብ ለየት ባለ መልኩ የሚ...
30/12/2024

“ጮዬ ማስቃላ”
"የጋሞ ዞን ባሕላዊ እሴቶች ከሆኑ አንዱና ዋነኛው የ" ዮ ጋሞ ማስቃላ” ዘመን መለወጫ (laytha laame) አንዱ ነው።

“ጮዬ ማስቃላ” በጋሞ ብሔረሰብ ለየት ባለ መልኩ የሚከበር እጅግ ማራኪ በዓል ነው

“ጮዬ” በዳራማሎ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ 24 ቀበሌዎች ውስጥ አንዷ ነች፡፡

ቀበሌዋ ከወረዳው ዋና ከተማ ዋጫ 31 ኪ.ሜ ርቀትና ከጋሞ ዞን መዲና አርባምንጭ በ197 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች።

“የዮ ማስቃላ” በዓል በዞኑ በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች በመስከረም ወር ላይ ይከበራል ።

የ”ጮዬ ማስቃላ” በዓል ግን የራሱን ባሕላዊ የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት ተከትሎ በታኅሣሥ ወር የሚከበር የዘመን መለወጫ ነው።

ዳራማሎ ወረዳን ለየት የሚያደርጋት በጋሞ ዞን የመስቀል በዓልን ሦስት ጊዜ የምታከብር ብቸኛ ወረዳ በመሆኗ ነው።

ወረዳዋ በታኅሣሥ ወር የ”ጮዬ ማስቃላን” ፣ በጥቅምት ወር የ”ጉጌ ማስቃላ” እና በአብዛኛው የጋሞ ዞን የሚከበረውን “የዮ ማስቃላ” በዓል በመስከረም ታከብራለች።

ጮዬ ማስቃላ የሚከበረው የደረሰ አዝመራ ከተሰበሰበ በኋላ የሀገር ሽማግሌዎች ቀኑን ቆጥረው በታኅሣሥ ወር ሙሉ ጨረቃ ጥርት ብላ ስትታይ ነው።

“ኢቴ ቶሆ”

የጮዬ ማስቃላ አራት ሳምንት ሲቀረው ባሕላዊ መሪው ከፋንጎ ድቡሻ በዓሉ ስለመድረሱ አዋጅ ያስነግራል ፤ ይህም “ኢቴ ቶሆ” ይባላል።

በዚህ አዋጅ ነጋሪው የሰባቱን ደሬዎች ስም እየጠራ ማስቃላ ደርሷል ይላል።

ቅመም ፣ ቅቤ ፣ ልብስ ፣ ወተት . . . ግዙ የተጣላችሁ ታረቁ እያለም መልዕክቱን ያስተላልፋል።

“ሶፌ”

በዚህ ዕለት ዓመቱን ሙሉ ያገቡ ሙሽሮች ፣ ግዳይ የጣሉ ጀግኖች ፣ አራስ ሴቶች ፣ አዲስ ባሕላዊ ሹመት የተቀበሉ ሁሉ ዕውቅና የሚያገኙበት እና ከማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉበት ሥርዓት ነው።

“ካሎ ዲሾ”

ዕለተ አርብ “ካሎ ዲሾ” ይባላል ፤ ከብቶች እስከ ማስቃላ ተጠብቆ የቆየ ለምለም የግጦሽ ሣር እንዲግጡ ይፈቀዳል። ቅዳሜ እርድ ነው። ዕሑድ /Tama keso/ ደመራ ይደመራል።

ዕለተ ዕሑድ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ነዋሪዎች ከሕጻን እስከ አዋቂ ችቦ በመያዝ ወደ ፋንጎ ይተማሉ።

በየመንገዱ ከቤት ለኩሰው ባወጡት ችቦ አንዱ አንዱን እየነካ “ዮ ዮ ማስቃላ”እየተባባሉ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ፋንጎ አደባባይ ሲደርሱ ችቧቸውን ያከማቹና ወደ ቤት ይመለሳሉ።

“ጉጌኖ”

ጉጌኖ የማስቃላ ችቦ በወጣ በሳምንቱ ዕሁድ የሚከናወን የሽኝት ሥነ ስርዓት ነው።

ከማለዳ እስከ ስድስት ሰዓት ሲበላ ሲጠጣ ይዋልና ልክ ሰባት ሠዓት ላይ በአራቱም አቅጣጫ የበዓሉ ሰዓት መድረሱን የሚያበስር "ዛዬ" ይነፋል።

በዚህ ጊዜ በሰባቱም ቀበሌዎች ያሉ “ሀለቃዎች” እና “ሁዱጋዎች”ከሰጎን ላባ የሚዘጋጅ " ጉቼ" በየሀብት መጠናቸው ቁጥር ልክ በእንሰት ኮባ ላይ ሰክተው በጭንቅላታቸው ላይ አስረው የሐገር ሽማግሌዎች በቡድን በቡድን ሆነው በአራት አቅጣጫ ወደ ፋንጎ አደባባይ በመምጣት ኡደት ያደርጋሉ።

መሸት ሲል ከየአካባቢው የመጣ ችቦ ይደመርና በ”ጮዬ ኤቃ” አማካይነት ደመራው ይለኮሳል።

ደመራው ሲቀጣጠል ወጣቶች እሳቱን እየዞሩ ባሕላዊ ጨዋታ ይጫወታሉ።

በመጨረሻም በ”ፋንጎ ድቡሻ” ማሳረጊያ ምርቃት በአባቶች ይደረጋል።

ሁሉም ይነሱና “ዮ ዮ ማስቃላ” በማለት ጉጌኖ !ጉጌኖ ! እያሉ ወደ ፋንጎ ይመለሱና የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል።"

24/12/2024

❝ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ መምሪያ ቁጥር_❲77/2017] ተብለው ልጠቀስ ይችላል።❞
****************************,***********
✡️❝4.የተፈፃሚነት ወሰን ላይ ይህ መምሪያ፥❞....................
👉በመሆኑ ይህንን መረጃ በየደረጃው ያሉ መ/ቤት የሰው ሀብቶች የመንግስት ሠራተኞች ያውቃሉ❓❓‼️

♐️❝ 2.በሙከራ ቅጥር ላይ የሚገኝ ሠራተኞች ወይም ግዜያዊ ወይም የኮንትራት ወይም የፕሮጀክት ሠሮተኞች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።❞‼️...............

♐️❝ 9. በቢሮው ተመዝነው ደረጃ በወጣለት ወይም በቋሚ የሥራ መደብ ላይ በመመሪያው ተከትለው የተቀጠረ ግዜያዊ ወይም ኮንትራት ሠራተኛ ወይም በሚመከተው አካል በተፈቀደ የፕሮጀክት ደመወዝ ወይም ልዩ የደመወዝ ስኬል የተቀጠረ ግዜያዊ ወይም የኮንትራት ሠራተኛ የደመወዝ ማስተካኪያ ተጠቃሚ ይሆናል❞‼️

♐️❝ 10. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 9 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ በቋሚ ሆነ በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች በፐብሊክ ሰርቢስ በተፈቀደ መደብ ላይ የተቀጠሩ ስሆን ብቻ ተፈፃሚ ይሆና።❞‼️

👉 ⚠️
♐️❝ ማንኛውም የመንግስት መሥሪያ ቤት ኃላፊ የኑሮ ውድነት ማካከሻ ክፊያ በሚፈጽምበት ግዜ የዚህን መምሪያ ድንጋጌዎች በመተላለፍ ወይም በመቃረን ሁኔታ ተግባር ላይ አግባብ ባለው ሕግ ተጠያቂ ይሆናል።❞‼️

መረጃ የሀገር ሀብት ነው 🙏‼️

Via ZuuZuulla Kamma Kaarana

15/12/2024

Address

To Arbaminch
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gaammo Media House/ጋሞ ሚዲያ ሐወስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gaammo Media House/ጋሞ ሚዲያ ሐወስ:

Share