Habesha Hulegeb Tube

Habesha Hulegeb Tube This page is aimed to Share the latest Ethiopian news, information's, and other related activities!

ይቅርታ‼️ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ "ያደኩበት ቤተክርስትያን ተገንብቶ በማለቁ የተሰማኝ ደስታን ለመግለፅ ሀላፊዎችን አስፈቅጄ ነው ጥይት የተኮስኩት በዚህም ያስከፋዋችሁ  ይቅርታ አድርጉልኝ"...
24/04/2024

ይቅርታ‼️
ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ "ያደኩበት ቤተክርስትያን ተገንብቶ በማለቁ የተሰማኝ ደስታን ለመግለፅ ሀላፊዎችን አስፈቅጄ ነው ጥይት የተኮስኩት በዚህም ያስከፋዋችሁ ይቅርታ አድርጉልኝ" ብሏል።

🙏ሼር  🙏ሼር 🙏ሼር ያድርጉ።እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ በጎፈንድሚ ከ 55,000 CAD ( የካናዳ ዶላር) በላይ ተሰብስቧል። አሁንም የሁላችንንም እርብርብ ስለሚጠይቅ እኛም የበኩላችንን እንወጣ ...
23/04/2024

🙏ሼር 🙏ሼር 🙏ሼር ያድርጉ።

እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ በጎፈንድሚ ከ 55,000 CAD ( የካናዳ ዶላር) በላይ ተሰብስቧል።

አሁንም የሁላችንንም እርብርብ ስለሚጠይቅ እኛም የበኩላችንን እንወጣ ።

🙏መርዳት ባንችል እንኳን ሼር በማድረግ መርዳት ለሚችሉ እናድርስ!!

👉 СВЕ 1000622473872
👉 Dashen Bank 5563671317021
👉 Abyssinia bank 91613069
👉 ኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ 1023500172828
👉 አዋሽ ባንክ 013471254339600

👉ትግስት ካሳ ቀፀላ

ስልክ
📞 0911868306
📞 0911137097

https://gofund.me/42557274

ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ተባለሕወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገ – ወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑን  ዋዜማ ...
23/04/2024

ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ተባለ

ሕወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገ – ወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑን ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች አሰባስቤ ሰራሁት ያለችዉ ዘገባ ያመለክታል። ከሁለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፈረመው ሕወሓት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን ብልፅግናን በመቀላቀል በሀገራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት መስማማቱን ቢገልፅም ፓርቲውን ለመቀላቀል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።

ከብልፅግና በፊት የነበረው ኢሕአዴግ እኩል የስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውክልና ያላቸው አራት ንዑስ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሆን ብልፅግና ግን አንድ ወጥ ፓርቲ ነው። የብልፅግና የፓርቲ ውክልና በህዝብ ብዛት የሚወሰን እንጂ እንደ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እኩል ውክልና አይኖራቸውም።

አሁንስ እየተደረገባቸው ባለው ድርድር ሕወሓት የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-ደንብ ተሻሽሎ በፓርቲ ውስጥ አባል ድርጅቶች እኩል የማዕከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ ውክልና እንዲኖራቸው ይፈልጋል።

ብልፅግና ግን ሕወሓት የተናጠል ህልውናውን አክስሞ ብልፅግናን እንዲቀላቀልና ውክልናውም በትግራይ ህዝብ ቁጥር ልክ የሚወሰን መሆኑን ይገልፃል።

የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር የጀመሩት ሲሆን ከሁለት ሳምንት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው በጉዳዩ ላይ በስፋት ተነጋግረዋል።

በሕወኋት በኩል ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው …አስፈላጊም አይደለም” ብለው የሚያምኑ አመራሮች ቢኖሩም ፣ ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው፣ በተለይም የትግራይን ፀጥታና ደህንነት ለመስጠበቅ ከብልፅግና ጋር አብሮ መቆም አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑም አሉ።

Via ዋዜማ

"በመዋሸቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ወጣት ሀብታሙሰሞኑን በቲክቶክ በተለቀቀ ቪዲዮ መነጋገሪያ የነበሩት የስራ ባልደረቦች በመካከላችን ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ጨዋታ ነው ብለዋል። አንዳዶች ጉዳ...
22/04/2024

"በመዋሸቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ወጣት ሀብታሙ

ሰሞኑን በቲክቶክ በተለቀቀ ቪዲዮ መነጋገሪያ የነበሩት የስራ ባልደረቦች በመካከላችን ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ጨዋታ ነው ብለዋል። አንዳዶች ጉዳዩን ወደ ሌላ ነገር ሲወስዱትም ተመልክተን ነበር።

ዛሬ ተስፋ ሚዲያ ሁለቱንም አገናኝቶ በመካከላቸው ግጭት እንደሌለ ተናግሯል። ሀብታሙ ሰዎች ገፋፍተው ገንዘብ ለማግኘት በመዋሸቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሏል።

👉 የነዚህን ሶስት እንቁዎች አይን ለማብራት እንረባረብ  #ሔራን እና  #ሶልያና የማየት ዕድል አላቸው፤ ያን ተስፋ እውን ለማድረግ 400 ሺህ ዶላር ያስፈልጋቸዋል።በመሆኑም የደጋግ ኢትዮጵያው...
22/04/2024

👉 የነዚህን ሶስት እንቁዎች አይን ለማብራት እንረባረብ

#ሔራን እና #ሶልያና የማየት ዕድል አላቸው፤ ያን ተስፋ እውን ለማድረግ 400 ሺህ ዶላር ያስፈልጋቸዋል።
በመሆኑም የደጋግ ኢትዮጵያውያንን እገዛ ይሻሉ።

🙏ሼር በማድረግ መርዳት ለሚችሉ እናድርስ!!

👉СВЕ 1000622473872
👉Dashen Bank 5563671317021
👉Abyssinia bank 91613069
👉ኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ 1023500172828
👉አዋሽ ባንክ 013471254339600

👉ትግስት ካሳ ቀፀላ

ስልክ
* 0911868306
* 0911137097

🙏ሼር በማድረግ መርዳት ለሚችሉ እናድርስ!!

ቲክቶከሯ ባደረገችው ነገር ተፀፅታ ይቅርታ ጠየቀች። በሀገራችን ከፍተኛ ተከታይ ካላቸው ቲክቶከሮች መካከል "ፊዮና" የምትባል ታዳጊ ለአንዲት ምስኪን እናት ስለሰጠችው 10,000 ብር ድጋፍ እ...
03/03/2024

ቲክቶከሯ ባደረገችው ነገር ተፀፅታ ይቅርታ ጠየቀች።

በሀገራችን ከፍተኛ ተከታይ ካላቸው ቲክቶከሮች መካከል "ፊዮና" የምትባል ታዳጊ ለአንዲት ምስኪን እናት ስለሰጠችው 10,000 ብር ድጋፍ እንዳደረገች ቀርፃ በቲክቶክ ትለቃለች።

ሌላ ቲክቶከር 1ሺ ብር ብቻ እንደሰጠች 9ሺ ብሩን ፊዮና መልሳ እንደወሰደች እናትየዋን ቀርፆ ይለቃል። ከዚህ በኋላ ነበር ታዳጊዋ ላይ ጫናው የበዛው ታዳጊዋ ፊዮና ምንም እንዳላጠፋች የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደሆነ ደጋግማ ብታስረዳም ዛሬ ግን የሰራውት ነገር ስህተት ነው ይቅርታ አድርጉልኝ ብላለች።

በዙሪክ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ****************ዛሬ ምሽት በተካሄደው የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡በወንዶች...
01/09/2023

በዙሪክ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ
****************
ዛሬ ምሽት በተካሄደው የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡
በወንዶች ምድብ በተካሄደው 5 ሺህ ሜትር የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ ርቀቱን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፣ ሰለሞን ባረጋ ደግሞ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
በምድቡ አሜሪካዊው ፊሸር ግራንት 3ኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል፡፡
በውድድሩ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ለሜቻ ግርማ አቋርጦ ወጥቷል፡፡

«ጥፋቴን አምኛለሁ፣ በድርጊቴ ተፀፅቻለሁ፣ በእኔም በቤተሰቤም ስም ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ!» «እኔ ኤዶም ንጉሱ በሆለታ በቤተክርስቲያን በቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለቀብር ሄጄ ስህተት...
30/08/2023

«ጥፋቴን አምኛለሁ፣ በድርጊቴ ተፀፅቻለሁ፣ በእኔም በቤተሰቤም ስም ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ!»

«እኔ ኤዶም ንጉሱ በሆለታ በቤተክርስቲያን በቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለቀብር ሄጄ ስህተት ስለፈፀምኩ፣ ያደረኩት ድርጊት በሀገር ውስጥ እና ውጪ የሚገኙ ኦርቶዶክሲያዊያንን ስላስቆጣ እኔም ጥፋቴን አምኛለሁ፣ በድርጊቴ ተፀፅቻለሁ፣ በእኔም በቤተሰቤም ስም ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ! የአካባቢው ነዋሪ፣ ደብሩ እና በሀገር ውስጥ እና ውጪ የምትገኙ ምዕምናን ይቅርታ እንድታደርጉልኝ በልዑል እግዚዓብሔር ስም እጠይቃለሁ» ስትል የይቅርታ ደብዳቤዋን አስገብታ በአውድምህረት ላይ የይቅርታ ደብዳቤዋ ለህዝቡ ተነቦ ይቅርታ ተደርጎላታል።

20/05/2023
ማናችንም ነገ ምን እንደምንሆን አናውቅም     ሀብት አያድነንም ፤ ውበት አያድነንም ፤ጉልበት አያድነንም ፤ ስልጣን አያድነንም ፤ ማንም አያድነንም ።*************************...
20/05/2023

ማናችንም ነገ ምን እንደምንሆን አናውቅም
ሀብት አያድነንም ፤ ውበት አያድነንም ፤ጉልበት አያድነንም ፤ ስልጣን አያድነንም ፤ ማንም አያድነንም ።
*******************************************************
ሳምራዊት እህታችን ለመኖር አገባች ፤ አግብታም ወለደች ። ትናንት ግን ከወራት ስቃይ በኋላ አረፈች ። " ገንዘብ እንደማያድን አየሁት " ይላሉ እናቷ ለኢዮሀ ሚዲያ እያለቀሱ ። ሀብት አያድንም ፤ ጉልበት አያድንም ፤ ስልጣን አያድንም ፤ ማንም አያድንም ። አምላክ ብቻ ያድናል ። በሳምራዊት መዳን ላይ የአምላክ ፈቃድ አልሆነም ። ቁምነገሩ እሱ አይደለም ። ለልጇ ፣ ለእናቷ ፣ ለባለቤቷና ለቅርብ ሰዎቿ ልብ መሰበር ካልሆነ ሳምራዊት በሞቷ እረፍት እንጂ ያጣችው የለም ።

ሀብት አያድንም ፤ ጉልበት አያድንም ፤ ስልጣን አያድንም ፤ ማንም አያድንም ። እኛ ከዚህ የምንወስደው ምንድነው ። በዚህ ዓለም ላይ የምንኖረው ለራሳችን ይሁን ለሌላ ግልጽ አይደለም ። መኖራችን ጥቅሙ ፣ መሞታችን ጉድለቱ የሚታየው በሌላው ለይ ነው ። ያ የመዳን ጉጉት አልሆነም ። እያንዳንዳችን እንደ ሳምራዊት ያለ ቀን ከፊታችን አለ ። ካንሰር ላይሆን ይችላል ። በተኛንበትም ፣ በእንቅልፋችን ውስጥ ሆነንም ሊሆን ይችላል ። የመሄጃችን ቀን ግን አለ ። ለእናቷም ፣ ለባለቤቷም ፣ ለልጇም ጭምር አለ ። የጊዜ ጉዳይ ነው ። ማንም ከዚያ አያስቀረንም ። ፀሎትም ፣ ጻድቅነትም እንኳ አያስቀረንም ።

ስራችን ይቀር ካልሆነ እኛ አንቀርም ። ከሌሎች ተምረን ራሳችንን የምንገልጽበት ሀሳባችንና ተግባራችን ብቻ በዚህ ዓለም ላይ ቋሚ ሆኖ ይቀራል ። ልጆቻችን ስማችንን የሚያስጠሩበት እድል እንኳን ጠባብና ጥቂት ነው ። እኛን ሰው የሚያደርገን በሰው ልጅ ልብ ውስጥ የተተከልንበት መጠን ነው ። የሚያስጠራን ያለን ሳይሆን ለዓለምና የሰው ልጆች የሰጠነው ነው ። " በምን ያህል መጠን ሰጥተናል ? " የሚለው ነው " በምን ያህል እንታሰባለን ? " የሚለውን የሚወስነው ። ሀብት አያድንም ፤ ጉልበት አያድንም ፤ ስልጣን አያድንም ፤ ማንም አያድንም ።

ውበት በወራትና ጥቂት አመታት ውስጥ እንዲህ ይረግፋል ። ይህቺ ውብ አበባ ምናልባትም በህልፈቷ ወቅት ከዚህ በላይም ከሰውነት ተራ ወጥታ ይሆናል ። በቃ ሰውነት ማለት እንዲህ ነው ። እኛ ማለት እንዲህ ነን ። ዋጋችን እንዲህ ነው ። መልካችን የሚመስለው ይህንን ነው ። ሳምራዊት ስታገባ ይህ ሁሉ መከራ ከፊቷ መምጣቱን አታውቅም ። አግብታ ስትወልድም ከምትወደውና ነሚወዳት ባለቤቷ ጋር ቤታቸው መሞቁንና መዋቡን እንጂ ከውልደቷ ማግስት ጀምሮ ስቃይና መከራን አልጠበቀችም ። እናቷም ፣ ባለቤቷም ሲናገሩ ትልቅ ስቃይ የሆነባቸው በቁም እያለች እሷንና ልጇን መነጠል ነበር ። በመጨረሻ ላይ የምትወደውንና የምትሳሳለትን ልጇን እንኳን ማቀፍ አልቻለችም ። አቅሟ ደክሟል ፤ ጉልበቷ ዝሏል ። በመጨረሻም ላይ ሄደች ። የዚህች ቆንጆ ሰውነት ከአፈር እንደመጣ ወደ አፈር ተመለሰ ። ማናችንም ከዚህ ቀን አናመልጥም ። ሀብት አያድነንም ፤ ውበት አያድነንም ፤ጉልበት አያድነንም ፤ ስልጣን አያድነንም ፤ ማንም አያድነንም ።
Via- Tewodros teklearegay

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ በሙሉ ነፍስ ይማር፣ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይስጥልን። እጅግ ልብ ሰባሪ ዜና ...
20/05/2023

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ በሙሉ ነፍስ ይማር፣ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይስጥልን።

እጅግ ልብ ሰባሪ ዜና ነው፣ ለሀገርም ትልቅ መጉደል ነው።
Elias Meseret

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habesha Hulegeb Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share