
04/04/2024
" የቼልሲ እና ዩናይትድ ትልቅ ጨዋታ አይደለም " ፖል ሜርሰን
የቀድሞ የመድፈኞቹ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ፖል ሜርሰን የዛሬው የቼልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ ትልቅ ጨዋታ አለመሆኑን ገልጿል።
ከዚህ በፊት የማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቅ እንደነበር የገለፀው ፖል ሜርሰን " ጨዋታው በአሁኑ ሰዓት ትልቅ ጨዋታ እንኳን አይደለም " በማለት ተናግሯል።
" ከሁለቱ አንዱ ቡድን ከብሬንትፎርድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ከባድ ፈተና ገጥሞት ነበር ሌላኛው ደግሞ አስር ተጨዋቾች የያዘው በርንሌይን ተቆጣጥሮ መጫወት አልቻለም።"
n.e