Amhara Reporter

Amhara Reporter Amhara Reporter

RIP
11/12/2022

RIP

09/12/2022

የኦሮሞ ቄሮ የልማት እንጂ የአድማ አጀንዳ የለወም!

የተለያየ አፍራሽ ፍላጎትና የፖለቲካ አጀንዳ ባላቸው የኦሮሞ ህዝብ ጠላቶች የቄሮ መግለጫ ተብሎ እየተሰራጨ የሚገኘው የአድማና የአመፅ ጥሪ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ በሁሉም አካባቢ የምንገኝ ወጣቶች ልንረዳ ይገባል።

ማንኛውም አካል ሃሳቡንና ፍላጎትን በሰላማዊ መንገድ ለማስተላለፍ የሚችልበት ሰፊ እድል የተፈጠረበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። ጥያቄዎች የሉም አይባልም፣ የትኛውም አካል ጥያቄና ቅሬታ ሊኖረው ይችላል። ሆኖም ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ የምናቀርብበት እድል በተሰጠበት በዚህ ወቅት ግለሰቦችን፣ ህዝብና እና ሀገርን በሚጎዳ የአድማ እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለራስም ኪሳራ ነው።

ይህንን የአድማና የአመፅ ቅስቀሳ እያደረጉ የሚገኙት ከፍተኛ ገንዘብ ከተለያዩ ስውር እጆች የተቀበሉ የሸኔ ልሳኖችና ሀገር አፍራሾች ናቸው። ሸኔ ደግሞ ለኦሮሞ ህዝብ የሚጠቅም ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ ጠላት መሆኑን ከማንም በላይ ባለፉት አመታት የኦሮሞ ህዝብ ጠንቅቆ አውቆታል። ልጁ የመንግስት ሰራተኛ ነው ብሎ ሽማግሌ አባትን በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገድለውን ሸኔ የኦሮሞ ህዝብ ጠላቱ እንደሆነ ማንም ነጋሪ አያሻውም። ከማንም በላይ በሸኔ የተቃጠለው፣ የተለበለበው፣ የረገፈውና ህይወቱ ስቃይ የሆነበት የኦሮሞ ህዝብ ነው።

የኦሮሞ ልጅ ነኝ የሚል ማንኛውም ቄሮ የዚህን የኦሮሞ ጠላት የሆነ አካል አጀንዳ ፈፅሞ ሊቀበል አይችልም። ሸኔ ከጥፋትና ከስቃይ ውጭ ለህዝቡ የሚፈይደው አንዳች ነገር የሌለው ከንቱ ቡድን መሆኑን እያወቅን ከዚህ የጥፋት መል ዕከተኛ ቡድን አጀንዳ ጋር ከቆምን እኛ የኦሮሞ ልጆች ከየትኛውም አካል በላይ ለኦሮሞና ለኦሮሚያ ጠላት መሆናችንን ማወቅ አለብን። ከሸኔ የጥፋት አጀንዳ አንዲት ዘለላ ስንዴ፣ አንዲት ጠብታ ውሃ ይገኛል?

ለኦሮሞና ለኦሮሚያ አሁን የሚያስፈልገን አድማ ሳይሆን ልማት ነው፣ ግጭት ሳይሆን ሰላም ነው፣ መለያየት ሳይሆን አብሮ መሆን ነው! ይህ ነው የሚያስፈልገን። እስከመቼ የማንም ስራ አጥና በትክክለኛ መንገድ ኑሮውን ማሸነፍ የማይችል ከንቱ መጠቀሚያ እንሆናል?

ለሸኔ የጥፋት አጀንዳ ጊዜ የለንም!
የኦሮሞ ቄሮ የኦሮሞ ህዝብ የልማት አጀንዳ አለው!

09/12/2022

ሸኔ የግብፅ መልዕክተኛና አጀንዳ አስፈፃሚ ነው!

የሰሜኑ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ያወቀችው ግብፅ ሙሉ ትኩረቷንና ግንኙነቷን ከሸኔ ጋር አድርጋለች!

የኢትዮጵያን የልማትና የማደግ አጀንዳን ለማደናቀፍ የማትፈነቅለው ድንጋይ የሌላት ግብፅ አሁን ሙሉ ትኩረቷን በሸኔ ላይ በማድረግ ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ እያደረገች እንደሆነ ታውቋል። ከዚህ ቀደም ከህወሃት ጋር በተደረገው ጦርነት ሀገር እንዳትረጋጋ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረገችው ግብፅ የሰሜኑ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እየተፈታ መሆኑን በመገንዘቧ አሁን ሙሉ አቋምን እና ተስፋዋን በሸኔ ላይ አድርጋ እየሰራች ነው።
ለዚህም ለሸኔ የፋይናንስ ድጋፍና አጀንዳዎችን በቀጥታ እየሰጠች ሲሆን ህዝብን ከህዝብ የማጋጨትና ሀገር እንዳትረጋጋ የማድረግ ተል ዕኮዋን ሸኔ እያስፈፀመላት እንደሚገኝ ታውቋል። የዚሁ ተል ዕኮ አካል የሆነው የአመፅና የአድማ ጥሪ ከማታ ጀምሮ በሸኔ ልሳኖችና አቀንቃኞች እየተነዛ እንደሚገኝ መገንዘብ ተችሏል።

ለዚህ ነው ሸኔ ፀረ-ህዝብ፣ ፀረ-ሀገር ነው የምንለው። ሸኔ የራሱ የሆነ አጀንዳ የለወም። አጀንዳዎችን የሚሸጡለት የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው። ሀገር ተረጋጋታ እንዳትበለፅ፣ ህዳሴ ግድብን ሙሉ ለሙሉ እንዳታጠናቅቅ፣ ከውጭ ተረጅነት ለመውጣት የያዘችው እቅድ እንዳይሳካ የኢትዮጵያ ጠላቶች በውስጥ ካሉ የእናት ጡት ነካሾች ጋር በመተባበር እየሰሩ ይገኛል።

ሸኔ ደግሞ የዚህ አጀንዳ ግንባር ቀደም አስፈፃሚ ነው። ስለዚህ ከሸኔ አጀንዳ ጋር መተባበር ከግብፅ ጋር መተባበር ነው!

09/12/2022

ሰበር ዜና
ከ20 በላይ ቁልፍ የሸኔ አመራሮች እርምጃ ተወስዶባቸዋል

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ይንቀሳቀሱ በነበሩ የሸኔ የሽብር ቡድን አባላት ላይ በተከናወነው ተከታታይ ኦፕሬሽን ከ20 በላይ ቁልፍ አመራሮች መገደላቸው ታውቋል፡፡

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ሰሞኑን በተከታታይ ያከናወኑትን ኦፕሬሽን በተመለከተ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ የሸኔ አባላት ላይ በተጠና መንገድ በተወሰዱ እርምጃዎች የሽብር ቡድን ዋና አዛዥ ኩምሳ ድሪባ ወይንም መሮ በመባል ከሚታወቀው ግለሰብ ጋር በቅርበት የሚንቀሳቀሱ አምስት ቁልፍ የሽብር ቡድኑ መሪዎችን ጨምሮ በተለያዩ ዞኖች ታጣቂ ቡድኑን የሚያስተባብሩ ከ20 በላይ አመራሮች ተገድለዋል፡፡

የመሮ የቅርብ ሰዎች የነበሩት መንጫስ፣ ሚካኤል ተርፋ ወይም ገዳ፣ ወንዴ፣ ጉቱና ገሜ የተባሉ አመራሮች በተወሰደው እርምጃ መገደላቸውን የሚያመለክቱት የመረጃ ምንጮች፤ ይህንን ተከትሎ በቅርቡ በተቃጣበት ጥቃት የመቁሰል አደጋ ደርሶበት የነበረው ዋና አዛዡ መሮ ከሕመሙ ሳያገግም በቄለም ወለጋ ዞን ወደ አሳቻ ስፍራ በመሸሽ ለመደበቅ ሙከራ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

በሸኔ ቁልፍ አመራሮች ላይ የተወሰደው እርምጃ በቡድኑ የኃይል አዛዦችና ታጣቂዎች ዘንድ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥና የስነልቦና ቀውስ እንዳሳደረም እየተገለጸ ይገኛል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ተገኝተዋል፡፡

ቡድኑ እየደረሰበት ባለው ከባድ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራዎች በእውር ድንብር ንፁሐንን ለማጥቃት መሞከሩ አንዱ ማሳያ ነው፤ ይሁንና የመንግሥት የጸጥታ አካላት እግር በእግር እየተከተሉ በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃ ሸኔ መፈናፈኛ ማጣቱ እየተገለጸ ይገኛል፡፡ ወደ ሽሽት የገቡት ታጣቂዎች በኅብረተሰቡ ላይ ዘረፋና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለመፈጸም ያደረጉት ጥረትም የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በጋራ ባከናወኑት ስምሪት ከሽፏል፡፡

የሸኔ አመራሮችን መገደል ተከትሎ የቡድኑ አንዳንድ አዋጊዎች ወደ ጎረቤት ሀገራት ለመሸሽ ቢያስቡም በጎረቤት ሀገራት ተሸሽገው የሚገኙ የሸኔ ሴል አባላት ታድነው እንዲያዙና ለመንግሥት ተላልፈው እንዲሰጡ ከስምምነት በመደረሱና በከበባ ውስጥ በመግባታቸው ሥጋት ውስጥ መውደቃቸው ታውቋል፡፡

አመራሮቹና ታጣቂዎቹ በቀጣይ የትግል ስልታችን ዙሪያ ምክክር ማድረግ ያስፈልጋል ውጊያውን እናቁም ወይም እጅ እንስጥ የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን፤ ይህን ተከትሎም መጠራጠር፣ ክፍፍል፣ አለመተማመንም በከፍተኛ ደረጃ መፈጠሩንና አለመግባባቱም መሣሪያ እስከ መማዘዝ ወዳደረስ ግጭት ማምራቱ እየተገለጸ ይገኛል፡፡

በመንግሥትና በሕዝብ ተቋማት ላይ ዝርፊያና ውድመት እያደረሰ የሚገኘው እንዲሁም ንፁሐንን በማገት ዘረፋና ግድያ እየፈፀመ ያለው የሸኔ የሽብር ቡድን እንዲከሰም በፌደራል እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላት ተከታታይና የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ መላው የኦሮሚያ ሕዝብም የቡድኑን አረመኔያዊና ኢሰብአዊ ድርጊቶች በማጋለጥና ጥቆማ በመስጠት ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጎን መቆሙ ታውቋል፡፡

31/10/2022

‹‹ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው›› - ዕብሪት ሲወጥራቸው
‹‹ሽምግልናߴኮ ባህላዊ እሴታችን ነው፤ ኧረ አስታርቁን›› - መከላከያ ሲደቁሳቸው

የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አመራሮች ጉዳይ ግራ አጋቢ ሆኗል፡፡ ለቀቅ ሲያደርጓቸው ፉከራና ቀረርቷቸው አይጣል ነው፡፡ ኒውክሌር የታጠቁ፣ ከምሥራቅ አፍሪካ አልፈው በመላው ዓለም የኃይል ሚዛን አስጠባቂ የሆኑ ይመስላቸዋል፡፡ የመንደር ሽፍታ ቡድንነታቸውን ዘንግተው የዓለም ልዕለ ኃያል ሀገር እንደሆኑ ይሰማቸዋል፡፡ ለያዝ ለገናዥ በማስቸገር ልክ በሌለው ዕብሪት ተወጥረው እንደ ሰፈር ጎረምሳ . . . በበረት ውስጥ እንደገባ በጥባጭ ኮርማ ያደርጋቸዋል ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል ‹‹ትዕግስትም ልክ አለው!›› በማለት ወደ ህወሓት መንደር የገሰገሰ እንደሁ እነርሱን አያድርጋችሁ፡፡ ከፍርጠጣቸው እኩል ምንዳ የሚሰፈርላቸው የውጭ ዜጎችና የቡድኑ ደጋፊዎችን ያካተተው የፕሮፓጋንዳ ክንፋቸው ለቅሶና የለየለት ቅጥፈት የማኅበራዊ ሚድያውን ሜዳ ይቆጣጠረዋል፡፡ በዕብሪት ተነሳስተው ወረራ ሲፈጽሙ እራሳቸውን እንደ ጀግና ሲያወድሱ የነበሩት በሙሉ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያለጥርጣሬ የሚገዛውንና አንጀቱን የሚበላውን የጄኖሳይድ ተፈጸመብን አጀንዳ ይከፍታሉ፡፡ ንፁሐን ተገደሉ ከተሞች ወደሙ ይላሉ፡፡ ሰሞኑን‹‹የመከላከያ ኃይሎች ከተማውን በእሳት አቃጥሉ ብለዋል›› በሚል የሠሯት ግን ብዙም ያልተሸጠች ድራማ ለህወሓት የፕሮፓጋን ክንፍ ቅጥፈት ጥሩ ማሳያ ትሆናለች፡፡

ጭምቡሉን ያለ ሀፍረት አውልቆ የህወሓትን የበሬ ወለደ ቅጠፈት ማስተጋባት የጀመረው አብርሃ ደስታም ‹‹አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ እንደሚባለው›› ሰሞኑን አዲስ ፈራሚ በመሆን የሚረጨው የሐሰት መርዝ አስገራሚ ሆኗል፡፡ አብርሃ መከላከያ በራያ አካባቢ ንፁሐንን ገድሏል በሚል ያሰራጨው የበሬ ወለደ ወሬ ህወሓት የራያን ሕዝብ በብረት መዳፍ ቀጥቅጬ ካልገዛሁ በማለት ያደረሰውን ግፍ ለማስረሳት የተሰነዘረች የፈጠራ ክስ መሆና ነው ።

አሁን አሁን ነገሮች እየተቋጩ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ፍንጮች ይታያሉ፡፡ የአሸባሪ ቡድኑ መታደራዊ አመራር ታደሰ ወረደ ጥይት የሳተው ታጣቂ መስሎ በድንጋጤ ገርጥቶ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ሽሬ፣ አድዋ፣ አክሱምና ሌሎችም በርካታ ስፍራዎች በጥምር ጦሩ መያዛቸውን አምኗል፡፡ ከወደ ደቡብ አፍሪካ የሚመጡ መረጃች እንደሚጠቁሙት በዕብሪት ተወጥረው ‹‹ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው ፤ ጦርነቱ አልቋል ከማን ጋር ነው የምንደራደረው›› በማለት ሲፎክሩ የነበሩትም፤ ‹‹ሽምግልናߴኮ ባህላዊ እሴታችን ነው፤ ኧረ አስታርቁን›› በማለት የሰላም ውይይቱ ቀን ተራዝሞላቸዋል፡፡ ሆኖም የሰላም ውይይቱ ጊዜ ቢራዘምም የዕብሪተኞች ቀን ግን ማጠሩ አይቀርም።

ህወሓት ተስፋ ሲቆርጥ ውሸት ማቀናበር ያደገበት ልማዱ ነው።ህወሓት የሀገር መከላከያ  ሠራዊትን በትር መቋቋም ሲያቅተው የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋትን ተያይዞታል። የሐሰት ፊልሞችን እያቀና...
30/10/2022

ህወሓት ተስፋ ሲቆርጥ ውሸት ማቀናበር ያደገበት ልማዱ ነው።

ህወሓት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በትር መቋቋም ሲያቅተው የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋትን ተያይዞታል። የሐሰት ፊልሞችን እያቀናበረ የሐሰት ክሶችን መፈብረክ ቀጥሏል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የተላበሰው ዕሴት ሕዝባዊነት መሆኑን ዓለም ያውቀዋል። ይሄንንም እንኳን በሀገሩ እና በሕዝቡ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮው በተግባር አሳይቷል። ይሄንንም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሰላም ካስከበረላቸው ሕዝቦች የተሰጡት የምስክር ወረቀቶች እስከ ዘለዓለም ሲናገሩለት ይኖራሉ።

ህወሓትና ጋሻ ጃግሬዎቹ መጀመሪያ ተቋሙን ለማፍረስ ሞከሩ፤ አልተሳካም። ጥቅምት 24 ሌሊት በክህደት ወግተው ሊያጠፉት ተፍጨረጨሩ፤ አልተሳካም። ደጋግመው ጦር መዘዙበት፤ ሽንፈት አከናነባቸው። አሁን በመጨረሻ ወደ ቆርጦ ቀጥል አመላቸው ገቡ።

አንዳንድ የሠራዊታችን አባላት በተለያዩ ጊዜያት፣ ለተለያየ ዓላማዎች፣ የተናገሩትን ቆርጦ እየቀጠለ፣ የሠራዊቱን ስም በማጥፋት፣ ጉዞውን የሚገታ መስሎት፣ ህወሓት መከራ እያየ ነው።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከግንዘቤ እጥረትም ሆነ የጠላት መጠቀሚያ በመሆን ከዕሴቱ ውጭ የሆኑ መልክቶችን የሚያስተላልፉ አባላቱን በከፍተኛ የዲሲፒሊን ጥሰት ይቀጣል። ይሄንንም የሚያደርገው ራሱን እያረመና እያበቃ የመሄድ ነባር ሥርዓት ስላለው ነው። የተልዕኮው ዋና ግብ ሕዝብን ከጉዳት መጠበቅ ስለሆነም ነው።

ስለሆነም ሕዝባችን ከህወሓት የቆርጦ ቀጥል ሤራ እንዲጠነቀቅና በዓላማና በአቋም ከሠራዊቱ ጋር የጀመረውን ቅንጅት እንዲያጠናክር፣ የመከላከያ ሠራዊት ጥሪውን ያቀርባል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

የመጨረሻውን ጊዜ መደረሱን የሽብር ቡድኑ አመነሰሞኑን የጥምር ጦሩ በሁሉም አቅጣጫ በከፍተኛ ወኔ ወደ መቐለ መገስገሱን ተከትሎ ትግራይ ነጻ እንደሚሆነ በማመናቸው ምክኒያት የህዝቡን ከየፌደራል...
28/10/2022

የመጨረሻውን ጊዜ መደረሱን የሽብር ቡድኑ አመነ

ሰሞኑን የጥምር ጦሩ በሁሉም አቅጣጫ በከፍተኛ ወኔ ወደ መቐለ መገስገሱን ተከትሎ ትግራይ ነጻ እንደሚሆነ በማመናቸው ምክኒያት የህዝቡን ከየፌደራል መንግስቱን የሚቃቅሩ የሃሰት መረጃዎች ባላቸው እዝ ሰንሰለት ተጠቀመው ቤት ለቤትና በየሃይማት ተቋማቱ እያሰራጩ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማህበራዊ ሚዲያም ለማሰራጨት ካሰቧቸው አጀንዳዎች መካከል የትግራይ አሰተዳደር በምሰልኔ ሰለሚመራ እንዳተቀበሉት በማለት አይቀሬ ሽንፈቱን ህዝቡ እንዲከላከልለት በማሰተጋባት ላይይገኛል፡፡
የትግራይ ህዝብ ሆይ የዚህ ሴራ ሰለባ እንዳትሆን!

ኢትዮጵም ትግራይም ታሸንፋለች

28/10/2022

"እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" - ጭካኔ የተሞላበት የህወሓት ውሳኔ

ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የሰሜኗ ኮከብ የሆነችውን መቀሌ ከተማ በቅርብ ርቀት ከበባ ውስጥ ማስገባቱን ተከትሎ ከተማዋ በእጁ እንደማትቆይ የተረዳው አሸባሪው የእናት ጡት ነካሹና የወንበዴዎች ስብስብ የሆነው የህወሓት ቡድን በመቀሌ ከተማ በእስር ላይ የነበሩ በርካታ ዘራፊዎችን በመበተን ወደ በረሃ እግሬ እውጪኝ እያለ መሆኑ ታውቋል።

አሸባሪ ቡድኑ ከዚህ በፊትም በ2013 ዓ/ም መከላከያ መቀሌን ከበባ ውስጥ ሲያስገባ በተመሳሳይ ሁኔታ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በመልቀቅ በከተማው ስርዓት አልበኝነት እንዲሰፍን፣ ህዝቡ ያለው ቀሪ ንብረት እንዲዘረፍ እና በርካቶች በማጅራት መቺ ህይወታቸውን እንዲያጡ ማድረጉ ይታወሳል። ይህ የሽብር ቡድኑ ሴራ በዋናነት መከላከያ ሰራዊት ከተማ በማረጋጋት ስራ እንዲጠመድ ለማድረግ ታስቦ ቢሆንም አሳዛኙ ጉዳይ ቡድኑ ለህዝብ ደንታ የሌለው መሆኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑ ነው። የመቀሌ ህዝብ ይህን ሴራ በደንብ የተረዳው ሲሆን መደበቂያ ያለው የዘራፊዎች ሰለባ ላለመሆን ንብረቱን ይዞ ወደ ገጠር አካባቢዎች እየሸሸ እንደሚገኝ ታውቋል።

የሁለት ጁንታዎች ወግ ጁንታ 1 ፡-  ወዴት እየሄድክ ነው ? ጁንታ 2 ፡- ለድርድር ወደ ደቡብ አፍሪካ እየሄድኩ ነው፤ አንተስ  ? ጁንታ 1 ፡-  ዋይ ለእኔማ እድለ ቢስ ነኝ፡፡ አታይም እ...
25/10/2022

የሁለት ጁንታዎች ወግ

ጁንታ 1 ፡- ወዴት እየሄድክ ነው ?

ጁንታ 2 ፡- ለድርድር ወደ ደቡብ አፍሪካ እየሄድኩ ነው፤ አንተስ ?

ጁንታ 1 ፡- ዋይ ለእኔማ እድለ ቢስ ነኝ፡፡ አታይም እንዴ . . . ዙሪያችንን ተከበብን'ኮ፡፡ ወደ ተንቤን በረሐ እየገባን ነው፡፡

ጁንታ 2 ፡- አይዞን የትም ብንሆን እንደመስሳቸዋለን !

ጁንታ 1 ፡- ትቀልዳለህ እንዴ ! ? አንተማ ምን አለብህ ? ! በድርድር ስም ሄደህ በዛው ትቀራለህ፡፡ ይልቅስ እንደመስሳለን ስንል አሁን የራሳችን ያልነው ሕዝብ እንዳይደመስሰን ፍራ፡፡ ትግራዋይ አምርሯል፡፡ አመራሮች ወደ ተንቤን በረሐ የሚወርዱት ለእኛ ሳይሆን እራሳቸውን ለማዳን፤ ለጥቅማቸው ነው እያለ እያጉተመተመ ነው፡፡

ጁንታ 2 ፡- ታዲያ አስቀድምን እንደዚህ የሚሉትን ለምን አንደመስሳቸውም !

20/10/2022

Video from recently freed Alamata.

The GoE already delivering humanitarian aid to Alamata residents. More will come as ENDF control the whole Tigray and free it from the Terrorists.

Address

Gotera
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Reporter posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share