Maleda / ማለዳ 24

Maleda / ማለዳ 24 share like

10/04/2022
23/10/2020

We want to a person who manage our page
For any question - inbox

'ኮሮና ቫይረስ ጠፍቷል፤ ውጡና ጨፍሩ' - ፖል ማኮንዳ(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)የታንዛኒያው ነባር ፖለቲከኛ 'የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጠፍቷል' ማለታቸውን ተከትሎ ከሃገሬው ሰው ወቀሳ እየ...
23/05/2020

'ኮሮና ቫይረስ ጠፍቷል፤ ውጡና ጨፍሩ' - ፖል ማኮንዳ

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የታንዛኒያው ነባር ፖለቲከኛ 'የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጠፍቷል' ማለታቸውን ተከትሎ ከሃገሬው ሰው ወቀሳ እየዘነበባቸው ነው። ፖለቲከኛው ይባስ ብለው ታንዛኒያውያን እሁድ ዕለት ወደ አደባባይ ወጥታችሁ የኮሮና ቫይረስ መጥፋትን አክብሩ ብለዋል።

የዳሬሳላም ኮሚሽነር ፖል ማኮንዳ የታንዛኒያ ዜጎች አዲስ ልብስ ገዝተው ደስታቸውን ቢገልፁ በበሽታው ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ይደግፋሉ ብለዋል።

ታንዛኒያ ወስጥ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስለመጥፋቱ ምንም የለም። የታንዛኒያ ጤና ሚኒስቴር ስለ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መግለጫ ከሰጠ አንድ (1) ወር አልፎታል።

ፈጣሪ ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን።

👍በየእለቱ የሚወጡ አዳዲስ እና ትኩስ መረጃዎች ለማግኘት ፔጃችንን LIKE ያድርጉ።

📩አስተያየትም ቢፅፉልን ይደርሰናል

📤SHARE ማድረጎን አይዘንጉ።
#ማለዳ24

 #በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር  #429 ደረሰ።ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3645 የላብራቶሪ ምርመራ  #30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላ...
22/05/2020

#በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር #429 ደረሰ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3645 የላብራቶሪ ምርመራ #30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር #429 ደርሷል፡፡

ፈጣሪ ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን።

👍በየእለቱ የሚወጡ አዳዲስ እና ትኩስ መረጃዎች ለማግኘት ፔጃችንን LIKE ያድርጉ።

📩አስተያየትም ቢፅፉልን ይደርሰናል

📤SHARE ማድረጎን አይዘንጉ።
#ማለዳ24

21/05/2020
ተጨማሪ 3 ሰዎች በ ቫይረሱ መያዛቸው ተረጋገጠ። በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,861 ላቦራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች ...
08/05/2020

ተጨማሪ 3 ሰዎች በ ቫይረሱ መያዛቸው ተረጋገጠ።



በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,861 ላቦራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ዘጠና አራት (194) ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከ23-33 ዓመት የሆኑ ይገኙበታል። የሁሉም ታማሚዎች የመኖሪያ ቦታ አዲስ አበባ ነው።

ፈጣሪ ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን።

👍በየእለቱ የሚወጡ አዳዲስ እና ትኩስ መረጃዎች ለማግኘት ፔጃችንን LIKE ያድርጉ።

📩አስተያየትም ቢፅፉልን ይደርሰናል

📤SHARE ማድረጎን አይዘንጉ።
#ማለዳ24

የሞባይል ባትሪን እድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮችአንዳንድ ጊዜ ከበሽታ ባልተናነሰ በእለት ተእለት ኑሯችን ጤና የሚነሱን አይነት ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የእለት ተዕለት...
08/05/2020

የሞባይል ባትሪን እድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች
አንዳንድ ጊዜ ከበሽታ ባልተናነሰ በእለት ተእለት ኑሯችን ጤና የሚነሱን አይነት ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የእለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የሚጎረብጡ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛዎቻችንን ከሚጎረብጡ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሞባይል ባትሪ ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ፣ በዚህ ዙሪያ ለሳይቴክ ደንበኞች መላ የሚሆን ነገር አናቀርብላቸውም ብለን አሰብን… ምን ትላላችሁ?
ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ የተሰሩት ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) ሲሆን ይሄም ባትሪ በአግባቡ ካለመጠቀም መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ ይደክማል፤ ያረጃል፡፡ ይሄም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡ የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው ሲሆን ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ የሚያስግሩባቸውን ምክንያች እና ባትሪን በተሻለ መጠቀም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች እንደሚከተለው እንጠቁማችኋለን፡፡
የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች፡-
1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀም
ትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡
2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡
3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደር
በምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡
4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት
ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡
5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ
የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
6. 2 ደቂቃ ቢያቆይዎት ነው፤ ነገር ግን ይሄን መረጃ ሼር ብታደርጉት የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማቸዋል፡፡
አሁኑኑ ሼር አድርጉት፡፡

ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ እንዴት ማስተካከል ይቻላል?በተለያዩ አጋጣሚዎች ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ ሊገባ ይችላል፣ ይህ ሁኔታ ሲፈጠር ከመደናገጥ ይልቅ ቀላል የሆኑ አካሄዶችን በመከተልስልክዎ. እንዳ...
08/05/2020

ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ እንዴት ማስተካከል ይቻላል?

በተለያዩ አጋጣሚዎች ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ ሊገባ ይችላል፣ ይህ ሁኔታ ሲፈጠር ከመደናገጥ ይልቅ ቀላል የሆኑ አካሄዶችን በመከተል
ስልክዎ. እንዳይበላሽ ማድረግ ይችላሉ፡፡

ከሁሉም በፊት ስልክዎን በፍጥነት ከዉሀ ዉስጥ ማዉጣት ይኖርቦታል፡፡

ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ በቆየ ቁጥር ዉሀ ወደ ስልክዎ ዋና ክፍሎች ዉስጥ የመግባት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡

ሊከተሉዎቸዉ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን እንመልከት፡

በፍጹም ሊያደርጉዎቸዉ የማይገቡ ነገሮች

• ስልክዎን እንዳያበሩት

ስልክዎ ላይ የሚገኙትን ቁልፎች አይንኩ

•ስልክዎን አያወዛዉዙት ወይም ስልክዎ ከሌሎች ነገሮች ጋር አያጋጩት

•የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች አይንቀሉ፡፡

ስልክዎ የዉሀ ብልሽት
አመላካች(Liquid Damage Indicator(LDI)) ተገጥሞለታል፣

የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች የሚከፍቱት ከሆነ ይህ የዉሀ ብልሽት
አመላካች አክቲቭ(Active) ይሆናል፡፡

ይህ ደግሞ ከስልኩ አምራች
ድርጅት የሚሰጠዉን Warranty ያሳጣዎታል፡፡

በትንፋሽዎ ዉሀዉን ለማድረቅ አይሞክሩ፣

ምክንያቱም ስልክዎ
ላይ በሚተነፍሱበት ጊዜ ዉሀ ወደ ዉስጠኛዉ የስልክዎ ክፍል ዉስጥ ሊገባ ስለሚችል ነዉ፡፡

ስልክዎን በማንኛዉም አይነት. የሙቀት መሳሪያ ለማድረቅ አይሞክሩ፡፡

ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ ከብልሽት የሚከላከሉባቸዉ አካሄዶች
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

1) ስልክዎን ከዉሀ ዉስጥ ሲያወጡት እየበራ ከሆነ ያጥፋት እና
ቀጥ አድርገዉ ይያዙት፡፡
2) የስልክዎን ከቨር በመክፈት ባትሪ፣ሲም ካርድ እና ሚሞሪ
ካርዱን ያዉጡ፡፡

3) ደረቅ ጨርቅ ወይም ማድረቂያ በመጠቀም ስልክዎን ያድርቁ፡፡
ዉሀ ወደ ሌላ የስልክ ክፍሎች እንዳይተላለፍ ይጠንቀቁ፡፡

4) በጐድጓዳ ሰሀን ላይ ያልተቀቀለ ሩዝ ይጨምሩ እና ስልክዎን
ሩዝ ዉስጥ ይክተቱት፡፡ ሩዝ ዉሀን የመምጠጥ አቅሙ በጣም ከፍተኛ
ስለሆነ አብዛኛዉን ጊዜ ስማርት ስልኮችን እና ታብሌቶችን ለማድረቅ
ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡

5) ስልክዎ በሩዝ ዉስጥ ለአንድ ወይም ሁለት ቀን እንዲቆይ
ያድርጉ፡፡ በእነዚህ ቀናቶች ዉስጥ ስልክዎን ለማብራት
እንዳይሞክሩ፡፡

6) ከጥቂት ቀናቶች በሗላ ስልክዎን ከሩዝ ዉስጥ ያዉጡ እና
ባትሪዉን አስገብተዉ ያብሩት፡፡
ስልክዎ አሁንም ካልበራ ባትሪዉን ቻርጅ ያድርጉት፣

ቻርጅ ተደርጎም
የማይበራ ከሆነ ባትሪዉ ብልሽት አጋጥሞታል ማለት ነዉ፡፡

ባትሪ
ይቀይሩለት ወይም ወደ ስልክ ሰሪዎች ይዉሰዱት፡፡

⚽ስፖርት ⚽♻️የዝውውር ዜናዎች♻️◉ባርሴሎና የኮሮና ቫይረስ ባደረሰው ቀውስ ኢኮኖሚያቸው ትክክል ስላልሆነ የላውታሮ ማርቲኔዝ ዝውውር ላይ እክል ሊገጥማቸው ይችላል ተብሏል ለዝውውሩ ግን ገንዘ...
22/04/2020

⚽ስፖርት ⚽

♻️የዝውውር ዜናዎች♻️

◉ባርሴሎና የኮሮና ቫይረስ ባደረሰው ቀውስ ኢኮኖሚያቸው ትክክል ስላልሆነ የላውታሮ ማርቲኔዝ ዝውውር ላይ እክል ሊገጥማቸው ይችላል ተብሏል ለዝውውሩ ግን ገንዘብ እና ተጫዋቾች የመስጠት ፍላጎት አላቸው

◉ማውሪዚዬ ሳሪ ጆርጊኒሆን ከቼልሲ የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው እና በክረምቱ የመጀመሪያ ታርጌታቸው እሱ ነው

◉ማንቸስተር ዬናይትድ የጄደን ሳንቾን ዝውውር እየመራ እንደሆነ እና ለተጫዋቾቹ አማላይ ገንዘብ እና ታሪካዊውን 7 ቁጥር ማሊያ አዘጋጅተው የክረምቱን ዝውውር እየጠበቁ ይገኛል

◉ላምፓርድ የክረምቱ የመጀመሪያ ዕቅዶቹ የሌስተር ሲቲው ቤን ቺዌል እና የኤሲሚላኑ ተከላካይ ሮማኞሊ እንደሆነ ስካይ ስፖርት አስነብቧል

◉የቶማስ ፓርቴ ዝውውር በአርሰናል አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ዕድሉ ሰፊ ነው ተብሏል በክረምቱ የርቴታ የመጀመሪያ ፈራሚ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል መድፈኞቹ ለዝውውር 50 ሚሊየን ፓውንድ ያወጣሉ

◉ሮድርጌዝ,ቤል,ናቾ,ዲያዝ,ቫስኪዩዝ,ኦርዲዚዬላ እና አውሪሊዬ በዚህ ክረምት ከሪያል ማድሪድ የሚሰናበቱ ተጫዋቾች ናቸው

◉ሊሮይ ሳኔ በዚህ ክረምት ወደ ባየር ሙኒክ የመዘዋወር ዕድሉ 90% ፐርሰንት ነው ሲቲዎችም ከአሁኑ የእሱን ተተኪ እያፈላለጉ ነው

◉ቀያዬቹ ሴጣኖች የሃሪ ኬንን ዝውውር በዚህ ክረምት ሊያሳኩት እንደማይችሉ አምነዋል መሉ ትኩረታቸው ሳንቾ ላይ ነው

◉ቲሞ ዋርነርን ወደ ሊቨርፑል እንዲመጣ ዩርገን ክሎፕ አሳምነውታል ተብሏል የእሱ ሊቨርፑል መምጣት ደሞ ፌርሚኖ ወደ ቀድሞ የ10 ቁጥር ቦታው መጫወት ይጀምራል ማለት ነው

◉አርሰናል በዚህ ክረምት በርከት ያሉ ተጫዋቾችን እንደሚያሰናብት እና ቡድኑን እንደ አዲስ እንደሚገነባው አርቴታ አሳውቋል።

 በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1073 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግ...
22/04/2020



በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1073 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 116 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ቦታው በአፋል ክልል ገዋኔ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 2 - የ54 ዓመት አሜሪካዊ (በትውልድ ኢትዮጵያዊ) ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አምስት (5) ሰዎች (4 ከአዲስ አበባና 1 ከድሬዳዋ) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሃያ አንድ (21) ደርሷል።

24

ግብጽ ለአሜሪካ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ላከች!ፕሬዝዳንት አብዱልፋታህ አልሲሲ ለአሜሪካ የህክምና ቁሳቁሶች እንዲላክ በወሰኑት ውሳኔ መሰረት ሀገሪቱ በጦር አውሮፕላን ቁሳቁሶችን መላኳ ተዘግቧል...
22/04/2020

ግብጽ ለአሜሪካ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ላከች!

ፕሬዝዳንት አብዱልፋታህ አልሲሲ ለአሜሪካ የህክምና ቁሳቁሶች እንዲላክ በወሰኑት ውሳኔ መሰረት ሀገሪቱ በጦር አውሮፕላን ቁሳቁሶችን መላኳ ተዘግቧል

 በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
22/04/2020



በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ስልክ network📶 አልሰራ የሚልበት ሁለት አይነት ምከንያቶች ብቻ ናቸዉ ።1. hardware problem2. Software problemየ hardware ችግር መሆኑን ማወቂያ ምልክቶች👇✅ n...
21/04/2020

ስልክ network📶 አልሰራ የሚልበት ሁለት አይነት ምከንያቶች ብቻ ናቸዉ ።
1. hardware problem
2. Software problem

የ hardware ችግር መሆኑን ማወቂያ ምልክቶች👇

✅ no sim-card(sim እያለዉ)
✅ insert sim-card(sim እያለዉ)
✅ no service (sim እያለዉ)

⬆️ስልኮ ከላይ የተዘረዘሩትን የሚል ከሆነ የhardware ችግር ስለሆነ ለ ጠጋኝ ማሳየት ግዴታ ነዉ።

⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

የ software ችግር መሆኑን ማወቂያ ምልክቶች👇
✅ Emergency
✅ network locked
✅ unknown sim
✅ invalid sim
✅ invalid imei
✅ incomplete imei

⬆️ስልኮ ከላይ የተዘረዘሩትን የሚል ከሆነ የsoftware ችግር ስለሆነ imei repair በማድረግ ይስተካከላል።

like 👍
👥 share ማድረጎን አይርሱ

 ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሚያዚያ 10 ቀን 2012 ዓ/ም ይወጣ የነበረው የትንሳኤ ሎተሪ ዕጣ የተራዘመበት ምክንያት በኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ሳቢያ ሎተሪው ባለመሸጡ መሆኑን ገልጿል። የዕጣ መ...
21/04/2020



ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሚያዚያ 10 ቀን 2012 ዓ/ም ይወጣ የነበረው የትንሳኤ ሎተሪ ዕጣ የተራዘመበት ምክንያት በኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ሳቢያ ሎተሪው ባለመሸጡ መሆኑን ገልጿል። የዕጣ መውጫ ቀኑን በቅርቡ አሳውቃለሁ ብሏል፡፡
like 24

21/04/2020



በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 745 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 114 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ42 ዓመት ቻይናዊ የመኖሪያ ቦታው ሰበታ ዞን ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 2 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በስራው ባህሪ ለበሽታው ተጋላጭነት ያለው።

ታማሚ 3 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ ከሳዑዲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

አጫጭር መረጃዎች ፦- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ42,000 በላይ ሆኗል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከ790,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።- በደቡብ ኮሪያ 9 ሰዎች በ...
21/04/2020

አጫጭር መረጃዎች ፦

- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ42,000 በላይ ሆኗል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከ790,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

- በደቡብ ኮሪያ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተሰምቷል። አምስቱ (5) ከውጭ ሀገር የገቡ ናቸው።

- ባለፉት 24 ሰዓት በቻይና 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አራቱ (4) ከውጭ ሀገር የገቡ ናቸው።

- በናይጄሪያ የሟቾች ቁጥር 22 ሲደርስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ665 በልጧል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Maleda / ማለዳ 24 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share