
01/09/2025
አቤት አጨካከን...😥🙄😥
==========================
በትናንትናው ዕለት በ25/12/2017 ዓም ከጅቡቲ ነዳጂ ጭነው
ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር እና በሰሜን ወሎ ከደብረ ዘቢጥ ጋይንት ባለው የመንገድ ክፍል እገታ ዝርፊያን በመፍራት በእጀባ እየሄዱ ባሉበት መኪኖቹ በጥይት ኮምፒተራቸው ሴንሰር በመመታቱ ቁመው ነበር በቆሙበት እንዱ በቀን እንዱ ከመሸ በድምሩ 2 ነዳጂ የጫኑ መኪኖች መቃጠላቸውን መልዕክት ደርሶናል።
2ቱ ተሽከርካሪዎች ጨጨሆ ተብሎ በሚጠራው የመቄት እና የላይጋይንት ወረዳዎች በሆነ ቦታ ላይ መቃጠላቸውን አድርሰውናል። 3ኛ መኪና ነዳጁ እየፈሰሰ እንዳለም ነግረውናል።
በእጀባ የሚደረግ ጉዞ እንዲህ ንብረን ከውድመት ሹፌሮችን ከሞት ካላስጣለ መንገዱን ባለመጠቀም በአዲስ አበባ ዙሮ መምጣት ምርጫ ሊያደርግ ይገባል ከጅቡቲ የምትመጡ ሹፌሮች ባለንብረቶች።
ካሁን በፊት በዚህ የመንገድ ክፍል ጋይንት ወጣ ብሎ ቦቴዎች በጥይት ተመተው ነዳጅ መደፋቱ ይታወቃል።
የደረሰው የንብረት ውድመት 40,000,000 (አርባ ሚሊየን )ብር የሚገመት ሲሆን ይህ የግለሰቦች ሀብት ለህዝብ ግልጋሎት የመጣ ነዳጂ ነው።
ፍትህ ለአሽከርካሪዎች 😥🙇♀️😥