Wegen Media - ወገን ሚዲያ

Wegen Media - ወገን ሚዲያ Wegen Media is an independent source of news, information, and entertainment about Ethiopia and Horn

31/10/2024

" እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው ! " - አበባው ደሳለው (ዶ/ር)

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ ምንድነው ?

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦

" በባለፈው ዓመት መጨረሻ የበጀት ዓመቱ መዝጊያ ሰኔ 28 ወቅት ያነሳናቸው በርካታ ከህዝብ ጥያቄዎች ነበሩ።

ነገር ግን እነዛ ጥያቄዎች ስላልተመለሱ ከዛ ብዙም ለየት ያለ ጥያቄ አይደለም የምንጠይቀው ምክንያቱም ችግሮቹ እየተባባሱ ስለመጡ።

በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ የንጻሃን ግድያ፣ ህጋወጥ ጅምላ እስር ፣ እገታ ፣ ጾታዊ ጥቃት ፣ መፈናቀል ፣ ከፍተኛ ከኑሮ ውድነት ፣ አግባብ ያልሆነ የቤቶች ፈረሳ ያኔም ነበረ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

በአሁን ሰዓት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ብሶት አለ። በተለይ በአማራ ክልል ያለው ችግር ደግሞ አጠቃላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል እንዲሆን ያደረገ ነው።

በአማራ ክልል የመንግስት ኃይሎች ፀጥታውን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር ነበር ዘመቻ የጀመሩት ነገር ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ እንጂ ችግሩ ይበልጥ እየከፋ ሄደ እንጂ እየተሻሻለ አይደለም።

አሁንም ንጹሃን ዜጎች በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየሞቱ ነው ፣ ሲቪል ተቋማት የሆኑ ጤና ጣቢያዎች ፣ ትምህርት ቤቶች እየወደሙ ነው።

በአዲስ አበባ ፣ በአማራ ክልል እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው።

የኛ የምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልል ምክር ቤቶች አባላት ሳይቀሩ ከአንድ አመት በላይ ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ያለ ፍርድ እየተመላለሱ ነው ያሉት። ፍርድ ሳያገኙ ከአንድ ዓመት በላይ አስቆጥረዋል። ከዚህም የሚብሱ አሉ። ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች ለሁለት ዓመት ያክል ያለ ፍርድ የተቀመጡ አሉ በወይኒ ቤቶች።

ከፍተኛ የኑሮ ውድነቱን ስናይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አድርገናል፣ የብር የመግዛት አቅምን አዳክመን ኢኮኖሚው እንዲንሰራራ እናድረጋለን በሚል የተለያዩ ድጎማዎችን ተደርገዋል የደመወዝ ጭማሪ እስካሁን መንግስት ሰራተኛው ክሲ ውስጥ አልገባም ኑሮ ውድነቱ ግን እጅግ በጣም አሻቅቧል።

በኮሪደር ልማት ሰበብ በብዙ ሺዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ፈርሰው የተለያየ አቤቱታ በተለያየ መገናኛ ብዙሃን ዜጎች እያሰሙ ነው በተለይ አዲስ አበባ ችግሩ በጣም የገዘፈ ነው።

በአጠቃላይ እነዚህን ችግሮች ስናይ ከሰላምና ፀጥታው ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው።

ቅድሚያ የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ብንፈታው ሌሎች ችግሮችን አብረን እናስወግዳለን። እዛ ላይ ማተኮር አለብን።

🔵 መንግስት የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ለመፍታት እየሄደ ያለው አካሄድ እስካሁን ወታደራዊ ነው ፤ ፖለቲካዊ አካሄድ ለምን አልደፈረም ? ለምንድነው ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ የደከመው ?

🔵 ለእውነተኛ ድርድርና ውይይት በይፋ ጥሪ አቅርቦ ችግሩን ለምንድነው ለመፍታት የማይጠጋው ?

🔵 የሰላም መፍትሄ አካል አንዱ የጅምላ እስር ፣ የጅምላ ግድያ ማቆም ነው። ይሄ መቼ ነው የሚቆመው?

🔵 የኢኮሮሚ ችግሩን ለመፍታት ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት አለባቸው ያን ላለፉት በርካታ ዓመታት ማድረግ አልተቻለም ዜጎች በነጻነት እና በሰላም ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ መንግስት የሚያስችለው መቼ ነው ? "

ጋዜጠኛ ምኒልክ ፈንታሁን ፋኖን ተቀላቀለ!በኢትዮዽያ ቴሌቪዥን የዓባይ 365 የቴሌቪዥን ዝግጅት አዘጋጁ ጋዜጠኛ ምኒልክ ፋንታሁን የአማራ ፋኖ በወሎን ተቀላቅሏል።ጋዜጠኛ ምኒልክ ፈንታሁን  የአ...
08/10/2024

ጋዜጠኛ ምኒልክ ፈንታሁን ፋኖን ተቀላቀለ!

በኢትዮዽያ ቴሌቪዥን የዓባይ 365 የቴሌቪዥን ዝግጅት አዘጋጁ ጋዜጠኛ ምኒልክ ፋንታሁን የአማራ ፋኖ በወሎን ተቀላቅሏል።

ጋዜጠኛ ምኒልክ ፈንታሁን የአማራ ፋኖ በወሎ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውለታል።

Mulugeta Anberber

መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ.ም                   (ዘመቻ መቶ ተራሮች 3ኛ ቀን)የአርበኛ ዘመነ ካሴ ዕለቱ መልዕክት____________________________ለውድ አማራውያን ዲ...
05/10/2024

መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ.ም
(ዘመቻ መቶ ተራሮች 3ኛ ቀን)
የአርበኛ ዘመነ ካሴ ዕለቱ መልዕክት
____________________________

ለውድ አማራውያን ዲያስፓራዎች!

በምትኖሩበት የዓለም ጥግ ሁሉ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን!

ትግሉ በምትከታተሉት አኳሁአን በየቀኑ እየጋለ፣ በየቀኑ ቁመናውን እያስተካከለ፣ የጠላትን ካምፕ እያፈረሰ፣ የህዝቡን እና የፋኖውን ወኔና ተስፋ በየምእራፍ እያደሰ ወደፊት በመጓዝ ላይ ነው። የዲያስፓራው የቀደመ ድጋፍም እንደቀጠለ ነው። ያም ሆኖ የበለጠ የተቀናጀ፣ መልክ ያለው፣ ሰፊ፣ ጥልቅና ገንቢ ድጋፋችሁ የሚያስፈልግበት ወሳኝ የትግሉ የእድገት ደረጃ ላይ በመሆናችን ለማሳሰብ ያክል ብቻ ይህን አጭር ወንድማዊ መልክት ልኪያለሁ።

ወገኖቼ፤
በፊት የነበሩ ጊዚያቶችን ቀንሰን ብንተዋቸው እንኳን ባለፉት 17 ወራት ውስጥ ዓለም አቀፍ ትኩረት የሳቡ እና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ያሳሰቡ፣ የተቆጠሩ መልእክቶች የተላለፉባቸው ስንት ሰልፎች ተካሄዱ?
በመላው ዓለም ስንት የአማራ የዲያስፓራ ማህበራት አሉ?ከዚህ አኳያ ምን ያህል ሰልፎችን አስተባበሩ?

የአማራን ህዝብ ሰቆቃ እና እልቂት ያሳዩ፣ የዘር ፍጂት የወለደውን የአማራን ህዝብ ትግል መነሻና መድረሻ የሚያስገነዝቡ ስንት የጥናት ወረቀቶች ተሰሩ? ለስንት መድረኮችስ ቀረቡ?

የስንት ሚዲያዎችን በር አንኳኩተን የአማራን ህዝብ ሰቆቃና ትግሉን ነገርን? አስረዳን? ስንቶች ሚዲያዎች ትኩረት እንዲሰጡ አደረግን?

በየቦታው፣ በየጓዳው፣ በየኪሱ ለትግሉ ምን ያክል ገንዘብ ተሰበሰበ? ምን ያክሉስ በትክክል መሬት ላይ ደረሰ? ምን ያክል ለማን ደረሰ?

እነዚህን ጥያቄዎች በጊዜ የለንም መንፈስ ቁጭ ብሎ ማሰላሰልና በፍጥነት ትክክለኛ መልስ መስጠት ያስፈልጋል።
የምናውቀው እና የምናደንቀው ልፋትና ድካም ቢኖርም ዲያስፓራው ካለው ሁሉን አቀፍ ሰፊ አቅም አኳያ ግን ብዙ መነጋገር ይኖርብናል። ለቤት ግንባታ የተሰበሰበ “ነገር” የመንደር እንቅፋት እየሆነ አስቸግሯልና።ዝምብሎ መታመስ ይበዛል።

አንዳንዱ በውጭ የሚኖር አክቲቪስት የራሱ ብርጌድ ወይንም ሻለቃ መሪ አለው ወይንም እንዲኖረው ይሞክራል። በቀን በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ የስልክ ጥሪዎች መሬት ላይ ወዳለ ፋኖ ስልክ ይደረጋሉ። ብዙ ነገር ይወራል። ለበጎና ከ በጎ ኢንቴንሽን የተወራው እንኳን ከትግሉ ውስብስብነት አኳያ መሬት ላይ ብዙ ችግር ይፈጥራል።

እኔ ወንድማችሁ በዚህ ወሳኝ የትግላችን ምእራፍ ውስጥ እሳት ላይ ቆሜ አንድ ልመና ቀመስ ነገር ልንገራችሁ:- ብትችሉ መሬት ላይ ያለውን ትግል በሙሉ እምነት መሬት ላይ ላለው ታጋይ ተውት። ይህ ማለት ትግሉ አይመለከታችሁም ማለት አይደለም። ከመመልከት አልፎ የትግሉ ባለቤት ናችሁ። የሁላችንም ትግል ስለሆነም ነው ይህን የምፅፈው። ነገር ግን አይኖች ሁሉ፣ ቀልቦች ሁሉ፣ ስልኮች ሁሉ፣ ዋትሳፓች ሁሉ— ሁሉም ነገር ሁሉ መሬት ላይ ሆኗል። በመሆኑም ጊዚያችን ያለቦታው እየባከነ በየጊዜው በዲያስፓራው አቅም መሰራት የሚችል ስራ ሳይሰራ ይቀራል።

ሚናችን እንለይ፣ እንወቅ እና በዛ ልክ እንስራ። ግንኙነታችን ተቋማዊ እና መርህ ላይ የቆመ ይሁን። ግቡንና መድረሻ መንገዱን የለዬ ፣ የተቀናጀ ፣ ገንቢ ጥረት ከተደረገ ዲያስፓራ “አዲስ” ሀገር መፍጠር እንደሚችል አለም ብዙ አብነቶች አሏት። የታሪክ ንባባችን ችግር ከሌለበት በስተቀር በጣም ብዙ አማራ ዲያስፓራ የሚኖርባት አሜሪካ ራሷ በእንግሊዝ ዲያስፓራ ነው “የተፈጠረችው”። አስራ ሶስቱ የመጀመሪያ ኮሎኒዎች የተመሰረቱት በዚህ መልኩ ነው።
የአሁኗ እስራኤል የዲያስፓራ ውላጂ ናት።

የዲያስፓራ እንቅስቃሴ መልክ ሲኖረው ሀገር ሁሉ ፈጥሯል።

በያላችሁበት በስርዓት ውጡና የህዝባችን እልቂት ለአለም ንገሩ። የትግላችን ፍትሀዊነት በአለም ፊት መስክሩ። ውጡ! ጎዳናዎችን በሰልፍ አጥለቅልቁ። ጎዳናዎችና አደባባዮች ላይ ውላችሁ እደሩ፤ ሰንብቱ። የአብይ አህመድ ቡድን በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ፍጂት ለሰው ልጆች ሁሉ አሳውቁ።

በየዘርፉ ለህዝባችሁ የሚበጁ ጥናቶችን ስሩ። ምሁራዊ አቅሞች እዚህ ላይ ይረባረቡ።
መከራችን አውቀው ቢተኙ እንኳን ለአለም መሪዎች እና ሚዲያዎች ንገሩ። ዛሬ አማራን የበላ እሳት ነገ ሁሉንም እንደሚያቃጥል ዘርዝሩ። ታላቁ የአማራ ህዝብ እንደበግ እየታረደ መኖር አንገፍግፎት በቃኝ ብሎ መነሳቱን ሁሉም ይወቅ።
ለዚህ ሁሉ ጥረት መስመር አንድ የጋራ ተቋም ፍጠሩ፥ ምከሩ።

በዚህ ወሳኝ ወቅት ትግሉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ይፈልጋል። በተለይ የገንዘብ ድጋፍ። ለኛ የሚጠቅመን ለትግሉም የሚበጀው የተኛውን ተራራ መቆጣጠር እንዳለብን፣ መቼ እና የት መከላከልና ማጥቃት እንዳለብን እንድትመክሩን ሳይሆን በአንድ ቋት ሀሳብ ሰብስባችሁ፣ በአንድ ቋት ገንዘብ ሰብስባችሁ ካንድ ቋት ሀሳብም፣ ገንዘብም እንድታግዙን እንጂ ጀነራሎቻችን ሆናችሁ በስልክ እንድታዙን አይደለም።

ይህን ትግል ከሊቅ እስከ ደቂቅ በመንፈስና ሀላፊነት በመሸከም ረገድ እኩል ድርሻ አለን። በነፍስ ወከፍ ጀነራሎች ሆነን አዘን ግን ወደ ገደል እንጂ ወደ ድል አንመራውም። ለንደን ወይንም ካናዳ ቶሮንቶ የሚኖር አማራ ስልካችን ላይ ደውሎ “ሰኞ ጠዋት ባህርዳርን አጥቁ፣ ለዚህም ታንክና መትረጊስ በፍጥነት ታጠቁ” እንዲለን አንሻም ተገቢም አይደለም። እገዛ ማለት ይህም አይደለም።

አለም አቀፍ የጥናት መድረኮች ከትንሽ እስከ ትልቅ በአማራ ጉዳዮች ይጥለቅለቁ።
ዲያስፓራው ውስጥ ግዙፍ አቅም አለ፣ ጥናት ይስራ፣ ይፃፍ። ይወቅ፤ ያሳውቅ። ቋሚ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረኮች ይኑሩ። ግብግቡ ሀገር ሽጦ ኪሱን ከሚሞላ ቀጣፊ ቡድን ጋር በመሆኑ ለትግሉ ቋሚ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል። እናም በፍጥነት ስሩበት። ለዚህ ቅዱስ አላማ የአማራ ማህበራት በአንድ ይንቀሳቀሱ።

በዚህ ረገድ መሬት ላይ ያለው ጉዳይ መልክ መያዙ አይቀርም። በአጭር ማሳሰቢያ ተፅፎ የማያልቅ ብዙ ጉዳይ አለ። በጊዜው እንመክርበታለን።
ፈጣሪያችን ሁሉንም ይጠብቅ።

ድል ለአማራ ህዝብ!
[ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!]
አዲስ ትውልድ፤ አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ!

ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!የልማት ተነሺ ተብሎ ሰዎች ድንገት ቤታቸው ሲፈርስ ስለገጠማቸው ጉዳት ብዙ የሚያሳዝኑ ታሪኮች ሲነገሩ ሰምቻለሁ። ነገሩ ቢያሳዝነኝም፣ የስሚ ስሚ አ...
14/09/2024

ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!

የልማት ተነሺ ተብሎ ሰዎች ድንገት ቤታቸው ሲፈርስ ስለገጠማቸው ጉዳት ብዙ የሚያሳዝኑ ታሪኮች ሲነገሩ ሰምቻለሁ። ነገሩ ቢያሳዝነኝም፣ የስሚ ስሚ አይቼ ሳልመረምር አስተያየት ብሰጥ ሚዛናዊ አልሆን ይሆናል፣ እሳሳት ይሆናል በሚል ከማዘን በስተቀር ምንም አላልኩም ነበር፣ አሁን ግን ለልማት ድንገት መፍረስ የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት።

የማወራው ስለአንድ ሰው ታሪክ ነው፣ ተቆጥሮ ህዝብ ስለሚባለው፣ ሀገር በማቅናት ውስጥ ማህበረሰብ በመስራት ውስጥ አስተዋጽኦ ስላለው አንድ ሰው ነው።

የህይወት ታሪኩ እንዲህ ነው ...

ገና ጎረምሳ እያለ ከተወለደበት ገጠር ወጥቶ 250 ኪሎሜትር በእግሩ ተጉዞ አዲስ አበባ ገባ። አዲስ አበባ የግለሰቦች ንግድ ቤት ተቀጥሮ ከጽዳት አንስቶ የተለያዩ ስራዎችን ሰርቶ ከራሱ አልፎ ወላጆቹን ቤተሰቡን ረድቶ፣ ትዳር መስርቶ፣ ልጆች አፍርቶ፣ የግል ንግድ ከፍቶ ሲኖር ቆይቶ የዛሬ 60 ዓመት አካባቢ ከፈረንሳይ ኢምባሲ ወረድ ብሎ ከሃይዌዩ ድልድይ ስር የግንብ ግድግዳ ላይ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” የሚለው ጽሁፍ በደማቁ በቀይ ቀለም ከተጻፈበት ፊትለፊት ወደ ቤላ በሚወስደው ቀኝ መታጠፊያ መንገድ ላይ መሬት ገዝቶ ቆንጆ ቤት ሰርቶ ኑሮውን መሰረተ።

12 ልጆችን አሳድጎ፣ አስተምሮ ለወግ ለመዓረግ አበቃ፣ የልጅ ልጅ አየ። አሁን የ 94 ዓመት አዛውንት ነው። ጠንካራ፣ ደግ፣ ሰራተኛ፣ ተጫዋች፣ ቀልድ አዋቂ፣ ሰው ሁሉ የሚወደው፣ ሰውን ሁሉ የሚወድ፣ ሃይማኖቱን አክባሪ እምነቱን አጥባቂ ነው። የግቢ አትክልት ይወዳል፣ ግቢው በወይን፣ በአቩካዶ፣ በኮክ፣ በአፕል፣ በቡና ዛፍ የተሞላ የሚያምር ግቢ ነው። የአትክልት ፍቅሩ ለራሱ ቤት ብቻም አይደለም፤ ሰፈር ውስጥ እየዞረ በሰው ቤት በዘመድ ቤትም ችግኝ ከቤቱ እየወሰደ ይተክላል።

ይህ ጠንካራ ሰው በቅርቡ በህመም አልጋ ላይ ዋለ ፥ “በቂ ኖሬያለሁ ሆስፒታል እንዳትወስዱኝ በኖርኩበት ባረጀሁበት ቤት አስከሬኔ ይውጣ” አለ። ልጆቹ ቃሉን አከበሩለት ቤቱ ውስጥ እንዳለ ሀኪም እያየው በልጆቹ፣ በልጅ ልጆቹ በቤተዘመድ በጎረቤት ተከቦ እንዲያስታመሙት አደረጉ። ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የ አዲስ ዓመት ዋዜማ በሰፈሩ አንድ ዜና ተሰማ፣ ከወረዳ የመጡ ሰዎች እየዞሩ ለልማት እየመዘገቡ ነው የሚል።

የአዲስ ዓመት በዓል ማግስት መስከረም 2 መጥተው በ20 ቀን ውስጥ ቤታችሁ ለልማት ሊፈርስ ስለሆነ ለመስከረም 3 ጠዋት ለስበሰባ ኑ የሚል መልእክት በቃል ብቻ ተነገረ። እንዲህ ያለ ዱብ እዳ ሲሰማ ለህግ ጉዳይ መዋሉ ቢቀር እንኳን ህልም ይሆን እንዴ ብሎ ድጋሚ አይቶ ለማረጋገጥ የሚያስችል ብጣቂ ወረቀት አልተሰጠም፣ ልክ እንደ ክፉ መርዶ ነጋሪ በር አንኳኩተው በቃል ትዕዛዝ ሰጥተው ሄዱ።

መስከረም 3 በስብሰባው ላይ ስልክም ሆነ ማንኛውም ድምጽ እና ምስል መቅጃ ይዞ መግባት ባልተፈቀደበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢዎቹ ቤታችሁ ለልማት ይፈርሳል የሚለው መርዶ ተነገራቸው።

ለምን?

ለጫካ ፕሮጀክት ልማት።

መቼ?

እስከ መስከረም 20።

ተሰብሳቢው ደነገጠ “ልጆቻችንን ትምህርት ቤት አስመዝገበናል፣ ዩኒፎርም አሰፍተናል፣ የደከመ ታማሚ ቤታችን ስላለ ጊዜው አይበቃንም፣ የእለት ጉርሴ ከቤት ኪራይ የማገኘው ብቻ ነው፣ ምን ልሁን? የሚሉ አዛውንቶች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ጮኸው አልቅሰው ተናገሩ። ሁለት ሳምንት አላችሁ ተባሉ።

ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃል??

በየቤቱ ያለ እቅድ ፥ ያለ ኑሮ... ለቅሶ፣ ጽኑ ታማሚ፣ ሰርግ፣ አራስ፣ የደረሰች ነፍሰጡር....ቤቱ ይቁጠረው ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃል? ምንድነው ጥድፍድፉ? ልማት ታስቦ እንደሆነም እኮ በረጅም ጊዜ እቅድ ላይ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ሊቀመጥ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ሰው ነው።

ነዋሪው እንዴት ይነሳ? ወዴት ይሂድ የሚለው እንጂ ትግበራ ከተጀመረ በኋላ በመጨረሻው ሰዓት ለነዋሪው በቀናት ውስጥ ትነሳለህ ብሎ በቃል መንገር እንዴት? ሰው ያነሰ ቅድሚያ ነው የሚሰጠው? ልማቱ ለሰው ነው አይደል??

ይህ ቤተሰብ የመራ፣ ሀገር ያቀና፣ ስንቱን ያስተማረ፣ የዳረ፣ አስታሞ በክብር የቀበረ፣ የተጣላን አስታራቂ የሐገር ሽማግሌ፣ አልጋ የያዘ መንቀሳቀስ፣ መንቃት የማይችል፣ ፈጣሪው ጋ እስኪሄድ ቀኑን የሚጠብቅ አረጋዊ እስከ መስከረም 20 ይነሳ ቤቱ ይፈርሳል ተባለ።

እንዴት ይሄድ? የት ይሂድ? በኖረበት ሰፈር ባቋቋምው እድር፣ በሚወደው አብሮ በኖረው የሰፈር ሰው ላይሸኝ? የሀገር ትርጉም ሲነገር “አባት የሞተ እንደሁ በሀገር ይለቀሳል” አልተባለም ነበር እንዴ? እና ለአባት የሚለቅሰበት፣ ለቅሶ የሚቀመጡበት ሀገር የለም??

ልማት ማንም አይጠላም ፣ ማማር ፣ መታደስ ማንም አይጠላም። የሰው ልጅን ግራ ሲያጋባ ለድንገተኛ ስጋት ሲዳርግ፣ ሰው ሁሉ የኔስ ተራ መቼ ይሆን እያለ በጭንቀት እንዲኖር ሲገደድ፣ ክብርን ሲነካ፣ ሰውነትን ሲያፈርስ ግን አዎን ልማት ይጠላል!!

ይሄን ጽሁፍ የምታዩ የልማት ደጋፊ ነን ባዮች ኮመንት ላይ መጥታችሁ፣ "እና ሃገር አይልማ? ሀገር ሲለማ አይናችሁ የሚቀላ፣ የልማት አደናቃፊዎች" ትሉ ይሆናል። እውነቱ ግን የልማት አደናቃፊ እናንተ ናችሁ።

እንደግፈዋለን የምትሉት ልማት በሰዎች እንዲጠላ፣ ሰው እንዲያለቅስበት፣ የምትታትሩ ዛሬን እና ሆዳችሁን ብቻ የምታዩ፣ ከሆዳችሁ ውጪ ሌላ ነገር የመደገፍ አቅም የሌላችሁ ሰባራ ሸንበቆዎች የልማት ጠላቶቹ ናችሁ።

ድንገት እንደ ሱናሜ አደጋ ቤታችሁ የፈረሰባችሁ ወገኖቼ፡ እስቲ ተናገሩት እንዴት ሆናችሁ? እንዴት አለፋችሁት?

እስቲ እውነተኛ ታሪካችሁን፣ ስሜታችሁን፣ ትኩስ ትዝታችሁን አጋሩን ታሪክ ይጻፍ ለሚመለከተው አካልም ሰውን ሳያፈርስ፣ ቤት አላልኩም ሰውን ሳያፈርስ ሰዉም ተቀብሎት ሊሰራ እንደሚችል ትክክለኛ ጥቆማ እና ድጋፍ ይሁነው።

✍️ Azeb Worku

21/04/2024

ቀሲስ በላይ መኮነን ፈጸሙት የተባለው እና በእስር ቁጥጥር የዋሉበት ዝርዝር መረጃ!

ቀሲስ በላይ መኮንን ከሰሞኑ "ተሳትፈዉበታል" በተባለው የማጭበርበር ድርጊት የተነሳ የአፍሪካ ህብረት የዉጪ ምንዛሬ የሚያስቀምጥበትን የባንክ ሂሳብ ከኢትዮጵያ ዉጪ ለማድረግ እንዳሰበ ተሰማ

ህብረቱ ለሶስተኛ ጊዜ በሀሰተኛ ሰነድ ልጭበረበር ነበር ያለ ሲሆን "ታማኝ" በተባሉ ሰዎች የተፈጸመው ሙከራ ወደፊት "በባለስልጣናት ላለመሞከሩ ማረጋገጫ ስለሌለኝ ነዉም" ብሏል

ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል መባላቸውን ዳጉ ጆርናል ተከታታይ መረጃዎችን አድርሷል። ይህንኑ ተከትሎ ቀሲስ በላይ የተጠረጠሩበት ድርጊት መነጋገሪያ ሆኖ የቆየ ሲሆን ዘ ሪፖርተር ደግሞ አዲስ መረጃ አጋርቷል።

ቀሲስ በላይ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመገኘት ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከህብረቱ የሂሳብ ቁጥር ለግንባታ እና ሌሎች ስራዎች ክፍያ በሚል 6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

ስማቸዉ ያልተጠቀሰ የዘ ሪፖርተር ምንጭ ታድያ ይህንን ድርጊት ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የዉጪ ምንዛሬ የሚያስቀምጥበትን የባንክ ሂሳብ ከኢትዮጵያ ዉጪ ለማድረግ እንዳሰበ ተናግረዋል። ህብረቱ ለሶስተኛ ጊዜ በተጭበረበረ ሰነድ ከባንክ ሂሳቡ ሊወጣ የነበረ ገንዘብን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ያስታወቀ ቢሆንም "እምነትና እዉቅና" ባላቸዉ ሰዎች የተፈጸመዉ ተግባር ወደፊት በባለስልጣናት ለላመሞከሩ መተማመኛ የለኝም በማለቱ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ያለዉ ቅርንጫፉ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት የተከፈተ ሲሆን በዋነኛነት የአፍሪካ ሒሳቦችን በተለይ ለማስተዳደር ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሪ ክምችት ያላቸዉ አካውንቶችን በማካተት ቁጥጥር ያደርጋል።

ቀሲስ በላይ በወቅቱ ሀሰተኛ የህብረቱ ማህተም ያረፈባቸዉን ወረቀቶች በመያዝ ለግንባታ እና የማሽነሪዎች አቅርቦት በሚል ክፍያዉን መጠየቃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ክፍያዉ ከመፈጸሙ በፊት ወደ ህብረቱ የስልክ ጥሪ ያደረጉት የባንኩ ሰራኞች የክፍያዉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሲሞክሩ የህብረቱ የፋይናንስ ክፍል የማያዉቀዉ መሆኑን እና ክፍያዉ እንዲታገድ ህብረቱ መጠየቁ መረጃዉ ይደርሳቸዋል።

ህብረቱ ይህንን ተከትሎም ግለሰቡ እንዲያዙለት ጠይቆ ቀሲስ በላይ በህብረቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ በፌዴራል ፖሊስ ተላልፈው መሰጠታቸዉ ይታወሳል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የፋይናንሺያል አስተዳደር ዲቪዥን ኃላፊ ማዳሊስቶ ሙኡሶ ሎሌም ወዲያውኑ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል እና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ክፍል ደብዳቤ ጽፈዋል ብሏል ዘገባዉ። ኃላፊዉ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ከአፍሪካ ህብረት ሒሳብ ወደ አራት ግለሰቦች ሒሳብ እንዲዘዋወር የጠየቁ ሰነዶች ሁሉም ፎርጂድ ናቸው ብለዋል በጻፉት ደብዳቤ።

ከዚህ ክስተት በኋላ የህብረቱ እና የባንኩ ሰራተኞች ለፖሊስ ቃላቸዉን መስጠታቸው በዘገባዉ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ እንደተናገሩት "በመሠረቱ ጥሬ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ብቻ ሊሰጥ አይችልም ። ለማጭበርበር የሞከረዉም ግለሰብ መጥቶ መጠኑን በጥሬ ገንዘብ ሲጠይቅ ይህን እንኳን አያውቅም ነበር ማለታቸዉን ነዉ።

አክለዉም " ግለሰቡ እዚህ አገር የዶላር አካውንት ከሌለው ገንዘቡ ቢተላለፍም እንኳ የትም ሊደርስ አይችልም። አጭበርባሪዎች በየቀኑ ወደ ባንካችን ይመጣሉ። ባንክ ስለምንሰራ የተለመደ ነው። እኛ ግን ሁልጊዜ ከመሳካታቸው በፊት እናጣራለን። ለፍርድም እየወሰድናቸው ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን ሒሳቦች የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ያንንን እያደረግን ነው። የአፍሪካ ህብረትም እስካሁን ድረስ ቀጥተኛ ቅሬታ አላቀረበብንም" ሲሉ አቶ አቤ ተናግረዋል።

"ማጭበርበር ሲያጋጥም ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው" ያሉት ስማቸው ያልተጠቀሱት የዜና ወኪሉ የአፍሪካ ህብረት ምንጭ" አሁን ማጭበርበሩ በተከበሩ ሰዎች እየተሞከረ ስለሆነ ተጨንቀናል" ብለዋል። ይህ ድርጊት "ባለስልጣናት አንድ ቀን ተመሳሳይ ነገር ላለማድረጋቸዉ ምንም አይነት ዋስትና የለንም" ያሉም ሲሆን "እምነት እያጣን ነው" ብለዋል።

ባለስልጣኑ አክለዉም በዚህ የተነሳ "ኢትዮጵያ ውስጥ ለደሞዝ አነስተኛ መጠን ያለው ፎሬክስ(የዉጪ ምንዛሪ ) ለመያዝ ወስነናል ፤ የድርጅቱን ገንዘብ ከኢትዮጵያ ውጭ ማቆየት እንድናስብ ያስገድደናል" ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣን መናገራቸውን ተናግረዋል።

VOA Amharic

20/04/2024


1) በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ከጥር 3-መጋቢት 23/2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ 1200 የሚጠጉ ሚሊሻዎች በፋኖ ኃይሎች ተገድለዋል። መረጃው ከክልሉ ሚሊሺያ ጽ/ቤት የተገኘ ነው።

2) ከየካቲት 18 እስከ ሚያዚያ 8/2016 ባለው ጊዜ 3214 አድማ ብተና አባላት ጠፍተዋል።

ከእነዚህ ውስጥ 74% የሚሆኑት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የጠፉ ናቸው!

3) መከላከያ አንድ ግምገማ አስቀምጧል። የማራ አድማ ብተና አባላት የቡድን መሣሪያ ካላስረከቡ አደጋ አለው። በግልጽ የፋኖን መንገድ የሚከተሉት በርካታ ናቸው። ፋኖው አደረጃጀቱ አንድ አለመሆን እንጅ አንድ ከሆነ ግልገል ፋኖው(አድማ ብተናው) ፋኖን ከመቀላቀል አይመለስም ተብሏል።

በአድማ ብተናው የታጠቀውን የቡድን መሣሪያ በፍጥነት ማስረከብ አለበት የሚል አቅጣጫ ተቀምጧል።

ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም

© beletekassa

15/04/2024

ሰበር የድል ዜና!!!!
ፋኖ ኩታበርን ተቆጣጠረ

በሻለቃ ደምሌ ጣፋጭ የሚመራው የልጅ እያሱ ክፍለ ጦር በሰለሞን አሊ እና ዮሴፍ አስማረ የሚመራው የአማራ ፋኖ ልዩ ኮማንዶ በጋራ በመሆን በተሰራ ልዩ operation በአሁኑ ሰአት ከሌሊቱ 7 ጀምሮ በተጀመረ ድንገተኛ ኦፕሬሽን በተሰራ ስራ የደሴ መዳረሻ የሆነችሁን እና ከደሴ ከተማ በ28 km ርቀት ላይ የምትገኘውን የኩታበርን ከተማ ተቆጣጥረናል።ጉዟችን በተጠናና በተደራጀ መልኩ ወደ ፊት የምንጓዝ ይሆናል።

በአዲስ ስራ በአዲስ ድል በአዲስ ስነልቦና ታድሰን እየመጣን ነው።

11/04/2024

እየተካሄደ ባለው ከባድ ውጊያ ሀገር አቋራጩ መንገድ ተዘጋ።

በከባድ ውጊያ ምክንያት የባህርዳር - ጎንደር ዋና መንገድ ተዘግቶ ዋለ።

እንፍራንዝ ፣ ቁልቋል በርና ጣና ገዳም አካባቢዎች እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ተከትሎ ሁለቱን የአማራ ክልል ትላልቅ ከተሞች ባህርዳርን እና ጎንደርን የሚያገናኘው መንገድ ተዘግቷል፡፡
በዚህ መንገድ ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡም ነው የተነገረው፡፡
ውጊያው ዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን ፣ የፋኖ ሃይሎች ከደንቢያና ከበለሳ አቅጣጫ ወደ እንፍራንዝ ከተማ በመግባት ውጊያ ከፍተዋል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 70% የሚደርሰዉ ቆጣቢ አማራ ነዉ።አብዛኛዉ ኦሮሞ አዋሽ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክና ኦሮሚያ ኮኦፕሬቲቭና ሲንቄ ባንክ ነዉ የሚቆጥበዉ። የንግድ ባንክ 70% ወሳኝ ...
16/03/2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 70% የሚደርሰዉ ቆጣቢ አማራ ነዉ።
አብዛኛዉ ኦሮሞ አዋሽ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክና ኦሮሚያ ኮኦፕሬቲቭና ሲንቄ ባንክ ነዉ የሚቆጥበዉ። የንግድ ባንክ 70% ወሳኝ የአመራር ቦታ የተያዘዉ ግን በኦሮሞዎች ነዉ።
አማራዉ ለሀገራዊ ተቋም ባለዉ ቀናኢ አመለካከት አብዛኛዉ ገንዘብ የሚያስቀምጠዉ ንግድ ባንክ ነዉ። ነገር ግን የንግድ ባንክን ገንዘብ እንደፈለገ እየተጠቀመበት ያለዉ ደግሞ በተቃራኒው የኦሮሞዉ ሀይል ነዉ።

አብይ አሕመድ የኦሮሞ ፖለቲካ የሚያግዘዉ ባለሀብት አልፈጠረም በሚል ሰበብ ባጫ ጊናና አቤ ሳኖ የባንኩን ተቀማጭ ገንዘብ ለኦሮሞዉ እያወጡ ዘሩት ።
ባለሀብት በመፍጠር ሰበብ የብድር ስርዓትን ያልተከተሉ በመቶ ቢሊየኖች የሚቆጠር ብር ለኦሮሞ ባለሀብት ተብየዎች ረጭተዋል
። ባንኩ ውስጥ ለባለጊዜዎቹ ጉዳይ ከሚያስፈጽሙ ሰዎች መካከል አንዱ
አቶ ደረጀ ፉፋ ይባላል።
ሰለእዚህ ሰውዬ ጉዳይ ከሶስት ሳምንት በፊት መረጃ ደርሶኝ በስራ ጫና ውጥረት ውስጥ ስለነበርኩ ዘንግቸዋለሁ ።
መረጃው ይሄንን ይመስል ነበር 👇👇👇

ደረጀ ፉፋ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤክዘኪዩቲቭ ቫይስ ፕሬዚደንት ነዉ። የባጫ ምክትል ነበር። አሁንም የአቤ ሳኖ ምክትል ነዉ። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል የነሽመልስ ገንዘብ አቀባባይ ነዉ። ከነሽመልስ በሚደርሰዉ ትዕዛዝ መሰረት የአማራ ባለሀብቶችን አካዉንት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይበረብራል። ለአማራ ባለሀብቶች ብድር እንዳይሰጥ ይከለክላል። ዋናዉ መስሪያ ቤት ላይ ያለዉን ወሳኝ ቦታዎች አማራ እንዳይደርስበት አድርጓል። አሁን ደግሞ አዲስ አበባ ዉስጥ ያሉ ሁሉም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲስትሪክት ዳይሬክተሮች ኦሮሞ ብቻ እንዲሆኑ በተሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረት እሱን ለማስፈፀም መመሪያ አስተላልፏል(አብዛኛው ተፈጻሚ ሁኗል)። አሁን ደግሞ አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ከሚገኙ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ዉስጥ 53 የአማራ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችን አስነስቷል። 53ቱ ስራ አስኪያጆች ተገደዉ ረፍት እንዲሞሉ ታዘዋል።

በ53ቱ እንዲነሱ በተደረጉ አማሮች ምትክ ደግሞ ኦሮሚያ ክልል ካሉ ዲስትሪክቶች ኦሮሞኛ ተናጋሪ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችን አምጥቶ እንዲተኩ መመሪያ አስተላልፏል።

ወደ ትናንቱ ዘረፋ ስናመራ

አንደኛ ሲስተሙ እንደሚሰበር ለሚፈልጉት አካል ቀድመዉ መረጃ አስተላልፈዋል።

ግለሰቦች በራሳቸዉ ሞባይልና በኤቲኤም ካንቀሳቀሱት ዉጭ በባንኩ ኮርባንኪንግ ሲስተም በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ አንቀሳቅሰዋል።

አብይና ጀሌዎቹ ፖለቲካዉን የሚደግፍ ሶሻል ግሩፕ መፍጠር አላማቸዉ ስለሆነ ዘረፋዉ የዚሁ አካል ነዉ። ኢኮኖሚዉን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነዉ (Economic capture leads to state capture) ይባላል። የኦሮሞ ብልፅግና በብሔራዊ ተቋማት ላይ እያደረገ ያለዉ አይን ያወጣ ዘረፋ የዚሁ እሳቤ አካል ነዉ።

ንግድ ባንክ ሁለት ሶስተኛ ቆጣቢዉ አማራ ነዉ። ቢዘረፍ የአማራዉ ሀብት ስለሆነ ችግር የለም ከሚል መነሻ ዘረፋዉን ፈጽመውታል። ባናቱም የንግድ ባንክን ደንበኛ ወደ አዋሽ ባንክ፣ ኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ፣ ሲንቄ ባንክና ሌሎች ኦሮሚያን ቤዝ ወዳደረጉ ባንኮች እንዲዞር ይፈለጋል።

ይህ ዘረፋ ከመከሰቱ ከጥቂት ቀናት በፊት ከላይ እንደተጠቀሰው ዋና መስሪያ ቤትና አዲስ አበባ ያሉ 53 አማራ የንግድ ባንክ ማኔጀሮችን የግዴታ ፈቃድ(Forced leave) እንዲወስዱ በማድረግ ከስራ አንስቷል። ዘረፋዉ በብዛት የተፈፀመዉ በኦሮሚያ አካባቢ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህ የተደረገዉ የእዚሁ ዘረፋ አንድ አካል ስለሆነ ነዉ። እናም ነጥቦችን ስናገናኝ በብልጽግና ሰዎች የተመራ ነው።

Woldesilassie

ሰበር ዜና!የአማራ ፋኖ ቀደምት ላሊበላ ከተማን ሲቆጣጠር የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ ዛሬ  መርሳ ከተማን ገቢ አድርጎ፤ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።
13/03/2024

ሰበር ዜና!
የአማራ ፋኖ ቀደምት ላሊበላ ከተማን ሲቆጣጠር

የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ ዛሬ መርሳ ከተማን ገቢ አድርጎ፤ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።

ሰበር ዜና/Breaking News! የአሜሪካን መንግስት በዝቋላ ገዳም የሀይማኖት አባቶችን ግድያ አውግዞ መግለጫ አውጥቷል:: በሲቪልያን ላይ የቀጠለው ግድያ በሀይማኖት አባቶች ላይ መስፋፋቱ ...
04/03/2024

ሰበር ዜና/Breaking News!

የአሜሪካን መንግስት በዝቋላ ገዳም የሀይማኖት አባቶችን ግድያ አውግዞ መግለጫ አውጥቷል:: በሲቪልያን ላይ የቀጠለው ግድያ በሀይማኖት አባቶች ላይ መስፋፋቱ በጥልቅ እንዳሳሰበው የአሜሪካን መንግስት በኤምባሲው አማካይነት መግለጫ ሰጥቷል::

The U.S. embassy in addisababa condemn the killing of monks at Ziquala Monastery. The embassy condemns killing of religious leaders and civilians faithful as well as the indiscriminate killing of civilians.

በአማራ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ1.8 ሚሊየን ሕዝብ በላይ ለችግር መዳረጉ ተሰማከ380 ሺህ በላይ ሕጻናትና እናቶች ለከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ክልሉ አስታውቋልበአንዳንድ...
17/02/2024

በአማራ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ1.8 ሚሊየን ሕዝብ በላይ ለችግር መዳረጉ ተሰማ

ከ380 ሺህ በላይ ሕጻናትና እናቶች ለከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ክልሉ አስታውቋል

በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች በተከሰተ ድርቅ በርካቶች ለችግር መዳረጋቸውና ሌሎች ደግሞ ለመፈናቀል ተገድደዋል። የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን እንደሚያመለክተው በአማራ ክልል በአጠቃላይ በ43 ወረዳዎችና 429 ቀበሌዎች በተከሰተው ድርቅ አንድ ሚሊዮን 800 ሺህ ህዝብ ጉዳት ደርሶበታል፣ ከ900 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቀያቸውን ለቅቀው ተፈናቅለዋል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው በሰሜን ጎንደር ዞን ጃንአሞራ ወረዳ «ዋሰን» በተባለ ቀበሌ የሚገኙ አንድ ተፈናቃይ ያለውን የእርዳታ አቅርቦት በተመለከተ ሲናገሩ፤ «ስለ ድርቁ ምን ብየ ላውራህ፣ የምትላስ የምትቀመስ፣ ምንም፣ ምንም፣ ምንም ነገር የለንም፣ ሌላው ቀርቶ “እግዚአብሔር የፈጠረውን ውሀ፣ እግዚአብሔር አነሳብን” ውሀ እንኳ ሳይቀር፣ እርዳታ የሚባል ነገር የለም፣ የለንም» ነው ያሉት።

ሌላው በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ በሚገኝ የተፈናቃዮች መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃይም በተመሳሳይ በቂ እርዳታ እንደማይደርሳቸው ነው የሚናገሩት። «እርዳታ እየቀረበ አይደለም፣ ህዝባችን እዚህ መጥቷል፣ ከ16 እስከ 17 ሺህ እንሆናለን፣ ህዝቡ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ተበትኗል፣ ምንጮች ደርቋል፣ ተፈናቃዩ ሁለትና ሶስት ወራት እዚህ ተቀምጦ ምንም ነገር የለም፣ «ጎኑን የሚዳስስ» እርዳታ እየመጣ አይደለም፣ መላ ቅጡ የጠፋው ጊዜ ነው።» ሲሉ ገልጠዋል።

የጃንአሞራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸጋው ተሰማ የውሀ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል። ምንም እንኳ ክልሉ የውሀ ቦቴ ቢያቀርብም የመንገድ ችግር እንደልብ አላሠራንም ብለዋል። የምግብ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ አሁን የተሻለ አቅርቦት እንዳለ ነው የተናገሩት።

በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ተቋም የድንገተኛ ስርዓተ ምግብ ቅኝትና ምላሽ ባለሙያ አቶ ኃይሉ አያሌው በድርቁ በዋናነት የተጠቁት ሕጻናትና አጥቢ እናቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።

«ድርቁ ያስከተለው ችግር በጤናና ስርዓተ ምግብ ላይ ስናስብ፣ ለምግብ እጥረት ከሚጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል ከ5 ዓመት በታች ሕጻናት፣ አጥቢና ነፍሰ ጡር እናቶች ናቸው። ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች አጠቃላይ በተደረገ ልየታ 23,060 ሕጻናት ከፍተኛ አጣዳፊ የምግብ እጥረት ያለባቸው ሆነዋል፣ 230,314ቱ ደግም መካከለኛ አጣዳፊ የምግብ እጥረት ያለባቸው ሆነው ተገኝተዋል።»

አጣዳፊ የምግብ እጥረት ካለባቸው 23 ሺህ ሕጻናት መካከል ግማሹ ያክሉ ብቻ የአልሚ ምግብ እርዳታ ያገኙ ሲሆን መካከለኛ የምግብ እጥረት ካለባቸው 230,314 ሕጻናት መካከል ደግሞ እርዳታ ያገኙት 34 ሺህ ያክሉ ብቻ ናቸው ብለዋል።

መካከለኛ የአጣዳፊ ምግብ እርዳታ ያሻቸዋል ተብለው ከተለዩ 62,426 እናቶች መካከል ደግሞ እስካሁን 15 ሺህ እናቶች ድጋፍ እንደተደረገላቸው አመልክተዋል። ተረጂዎችን በተሟላ ሁኔታ ማገዝ ያልተቻለው በዋናነት የግብዓት እጥረት በመኖሩ ነው ያሉት አቶ ኃይሉ መንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ረጂ ድርጅቶችና ተቋማት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

Address

Bole Sub City
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wegen Media - ወገን ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wegen Media - ወገን ሚዲያ:

Share