
12/01/2025
የቢቸግር "ነገር"!!
(🙉🤪🤓)
የቴዎድሮስ ፀጋዬ (ርዕዮት ሚዲያ) ፖለቲካል ኢጎ በጣም ይሸክካል። ያስጠላልም። ሰው-ይታዘበኛልም የለም?🤓🤔 ቴዎድሮስ የሚባለው በሚያሰራጨው ፕሮግራም ላይ ጃዋርን አቅርቦ ቃለመጠይቅ አደረገለት።
ጥሩ ሊባል የሚችል ክሪቲካል ነጥቦች የተነሱበት ቃለመጠይቅ ነው።
ከዚያ ጃዋር በመጨረሻዋ የባከነች ሰዓት ጠብቆ ነጥብ በቴዎድሮስ የቀደሙ አቋሞች ላይ ያደረበትን ቅሬታና ወደፊት እንዲታረም ተስፋ አንደሚያደርግ ገለፀ። ማለትም በፔናሊቲ መለያያ ምት ላይ በቴዲ ላይ ነጥብ አስቆጠረበት🤓🤩!
ጃዋር ያንን ሲለው ቴዎድሮስን አንዘረዘረው። ያለምንም ማስተባበያ በቀጥታ "አንተም እኮ እንዲህ እንዲህ ነህ፣ አታቅርበው ስባል ነው ያቀረብኩህ፣ ምናምን ..." ወደማለት ገባ።
በሎጂክ ይሄን ዓይነቱን የቴዎድሮስን የመሠለ ምላሽ "ፋላሲ" እንለዋለን። - ሃሳብን ባልተገባ መልኩ አንተምኮ እንዲህ ነህ ብሎ ማንሸዋረር (Ad-hominem fallacy ወይም Tu-quoqui ይባላል)።
እሺ ይሁን ሰው ነው። ሰዎች ናቸው። ሁሌ ከኢጎአችን ጋር ነው የምንዞረው። በራሱ ቤት መጥቶ ሲነድፈው፣ ዘራፍ ብሎ ተነሳ። ነገሩ በጣም አስቂኝ ቢሆንም፣ ok ይሁንለት። ይሁንላቸው። ፕሮፌሽናል ኔትወርኮች አይደሉም። የመሠላቸውን ቢሉስ ቢዘባርቁስ ማን ጠያቂ አላቸው? በገዛ ራሳቸው ሱቅ?.. ብዬ ትዝብቴንና ገረሜታዬን ከድኜ ዩትዩቤን ዘጋሁ።
ያ ሲገርመኝ፣ እና በመጨረሻው የቃለመጠይቅ ሰዓት ያየሁት አንካ ሠላንቲያ ያደነቅኩትን የጠያቂ ብስለት ወደ ህፃንነት ተርታ ላወርደው ሲዳዳኝ፣ ዛሬ ደሞ ዩትዩብ ጎትቶ አመጣልኝ።
ዩትዩቡ ደሞ ካለበት ዓመሉ፣ አንዴ ተሳስተህ እንኳ የሆነ ቻናል ከከፈትክ፣ በማግስቱ፣ ወሩን ሙሉ ያንኑ እየደጋገመ ያመጣብሃል። መልሶ አመጣብኝ የቴዎድሮስን "ርዕዮት"።
"የጃዋርን ቃለመጠይቅ አስመልክቶ በተመልካቾች የተሰጠ ግብረመልስ" የሚል ርዕስ ሳይ አሳቀኝ። ወይ ጃዋር? ትናንት ምግብ ሆኖ ተበልቶ፣ ዛሬ ደሞ መረቅ ሆኖ መጣ? አሳቀኝ።
በዛሬው ስነ ጃዋር ዝግጅት ላይ፣ ቴዎድሮስ ፀጋዬ አሉላ ሠለሞን ከሚባለው ሰው ጋር ስለ ጃዋር ቃለመጠይቅ ማውራት ጀመረ። አሉላም ስለ ጃዋር ኢንተርቪው የተባሉ ነጥቦችን እያነሳ፣ ከህወኀታዊ ሊባል ከሚችል አንግል እየተቸና አያደነቀ ሃሳቡንና አቋሙን ገለፀ።
ቴዎድሮስ ፀጋዬ ግን አሁንም በጃዋር ነገር አልረካም። በመጨረሻ ሰዓት ላይ ጃዋር የነከሰው እሰካሁን እየለበለበው ይመስላል።
ደሞ ጃዋር የህወኀቶቹን እነ ጌታቸው አሰፋንም "አውሬ" እያለ ሲገልፃቸው ነበር በቃለመጠይቁ። እና ይሄ ሁሉ ቁጭት ተጠራቅሞ፣ ገና በጃዋር ላይ ነጥብ ማስቆጠር አለብኝ ብሎ ወስኗል መሠለኝ ቴዎድሮስ ፀጋዬ🤪😀😃።
እና የአሉላን ቃለመጠይቅ ሲጨርስ ቴዎድሮስ ምን ቢል ጥሩ ነው? "እኔ ጃዋርን በራሴ ሚዲያ ጠያቂ ሆኜ ጋብዤ፣ ይሉኝታና ስነምግባር ይዞኝ በግልፅ ያላወጣሁት ስለጃዋር ያለኝ የግሌ አቋምና አስተያየት ስላለኝ፣ በሌላ አውራምባ ታይምስ በተባለ ሚዲያ በተጠያቂነት ቀርቤ ስለጃዋር ልክልኩን እናገራለሁ፣ እና ታዳሚዎቼ ነገ በዚያ ሚዲያ ላይ ስለጃዋር ስናገር አዳምጡኝ፣ ጠብቁኝ!" 😃😃😀🤪🤪!
አስበኸዋል? የሲኤንኤን የዜና አንከር ትራምፕን አቅርቦት ትራምፕ ነጥብ አስቆጥሮ ከተለየው በኋላ፣ "ነጥብ ተቆጥሮብኛልና ነገ ከጠያቂነት ወደ ተጠያቂነት ራሴን ለውጬ፣ በኤቢሲ ኒውስ ላይ ትራምፕን ሳብጠለጥለው ኑና ስሙኝ"😀 ሲል?
ወይ የቪኦኤ ጋዜጠኛ ተነስቶ፣ ትናንት የጋበዝኩት እንግዳ አቋም ቪኦኤ ከሚያንፀባርቀው የአሜሪካ መንግሥት አቋም ጋር ስለተጋጨብኝ፣ ነገ በዶቸቨለ ራዲዮ ላይ ተጋባዥ ሆኜ ቀርቤ የእንግዳዬን ጉድ ሳፍረጠርጥ ኑ ስሙኝ🤪😀 ሲል አስበው እስቲ??
እነዚህ የግለሰብ ሚዲያዎች (ማለትም የፓርቲ ዝንባሌ ያላቸው ግለሰባዊ ልሳኖች) ግን አንዳንዴ እንዲህ ውርድድድድድድ ይሉብኛል!
ከሙያው ጋር አይተዋወቁም። ግን ሙያተኛ ሆነው ጉብ ብለው ታገኛቸዋለህ። አሉ ብለህ ስታደንቃቸው፣ ተመልሰው ተራ መንደርተኛ ሆነው ታገኛቸዋለህ። የአህያ ሥጋ ይሆኑብሃል። አልጋ ሲሉት አመድ!😃🤪 (ደንበኛ አመዳሞች!😀🤩🤩)
ድሮስ ጆሮ ሰጥተህ አዳምጥ ብሎ ማን አስገደደኝ? ባላለፉበት ባላልፍስ? እንዲህ ዓይነቱን የወረደ የመንደርተኛ ነገር መች እሰማ ነበር? ማን አዳምጥስ አለኝ? በገዛ ጆሮዬ!🤪🙄 ይበለኝ!!😀🤩😳😳 እንድትል ያደርጉሃል።
የቢቸግር ነገር! የቢቸግር ነው ብዙው ነገራችን! We are far behind! እና ይሄን ማሰብ ራሱ ይሸክካል! አንዱ ካንዱ የሚሻልበትን ነገር ያሳጡሃል! አንዱ ከሚኮንነው ሌላው የተሻለ የሞራል ልዕልና የለውም! ይሄም ያው፣ ያም ያው! አሊታ ኪሊታ😀😃!!
አይለምደኝም!
(ግን አያርመኝም!😳😀🤪🤓)
አላህ ይሁነኝ!🙏🏿
🌿❤️