05/08/2025
በሬክተር 5.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ በኢራን መከሰቱ ተዘገበ።
ዛሬ ማለዳ ላይ የ5.4 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በደቡብ ምስራቅ ኢራን ተከሰተ፡፡
የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ እንደገለጸው የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር በ08፡36 ሲሆን፤ ጥልቀቱ በግምት 56.7 ኪ.ሜ (35.2 ማይል) ነው።
እስካሁን የመሬት መንቀጥቀጡ ስላደረሰው ጉዳት ከሀገሪቱ ባለስልጣናት የተሰጠ ማብራሪያ የለም።
ኢራን በሴስሚክ እንቅስቃሴ ባለበት ክልል ውስጥ የምትገኝ ሲሆን፤ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ብዙ አውዳሚ የመሬት መንቀጥቀጦችን ማስተናገዷ ይታወሳል።
በአገሪቱ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ እጅግ አሳዛኙ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በ2013 ነበር፡፡
በወቅቱም የ6.7 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ የባም ከተማን በመምታት ቢያንስ የ34 ሺህ ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል ሲል ያስታወሰዉ አናዶሉ ኤጀንሲ ነዉ።