02/09/2025
የስልጣን ጥማት ማርከሻ እና እድሜ መግዣነት ታስቦ የተገነቡ፤ ራዕይ የማጣት ማሳያ እና ትጉም አልባ ናቸዉ።
ትናንትና የብልጽግና ፓርቲ ቢሮዎች በሁሉም ወረዳዎች ተገንብቶ መጠናቀቁን እየተነገረ ይገኛል። ይህንኑ ስንመረምር የምናገኘዉ አንድ ምስጥር ይገለጥልናል። እሱም የስልጣን ጥማት ማርከሻ እና እድሜ መግዣነት ታስቦ የተገነቡ ራዕይ የማጣት ማሳያ መሆኑ።
ይህንን ስባል አንዳንድ የዋህ ማህበረሰባችን ክፍል ልማትን እንደምንቃወም አድርጎ ለማቅረብ እንደሚሞክር እንረዳለን፤ ዳሩ ግን እንዲህ ያለዉ ፋይዳቢስ ስራ ልማት እንደአይደል ለማሳየት ነገሩን በምክንያት እንመልከት። ግንባታዎች የተከናወኑት በሁሉም ወረዳዎች አስገዳጅ መዋጮ መሆኑ በሌላ በኩል ነገሩን በአሉታዊ እንዲነሳ ያደርገዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ይሁን ብለን መልካም ነዉ ብንል እንኳን ነገሩ አዎንታዊ የማይሆንበት አንድ ምክንያት ግን አለ።
እሱም ሲዳማ ክልል ነባር ወረዳዎች በስተቀር 1998 ዓ.ም የተመሠረቱ ወረዳዎችን ጨምሮ በቅርቡ 2011 ዓ.ም የተመሰረቱ አብዛኞቹ አንድ ወይም ሁለት በስተቀር ከሀያ የሚልቁ ሰክተር መስሪያቤት የራሳቸዉ ቢሮ የላቸዉም። ለዚህም በአመት ከፍተኛ ገንዘብ ለቢሮ ክራይ ያወጣሉ። ይህ ደግሞ የወረዳዎቹ ኢኮኖሚ ብሎም ህዝቡን በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳ ይገኛል።
በሌላ በኩል ፓርቲው ከዚህ ቀደም በወረዳ አስተዳደር ህንጻዎች ዉስጥ ሶስት ክፍል ዉስጥ የሚኖሩ ህዝባዊ አገልግሎት እምብዛም የሆነ፣ ከስሩ ሌላ ሰራተኞች የሌሉት፤ በአንጻሩ ምንም አይነት የቢሮ ክራይ የማይወጣባቸዉ መሆኑን ይታወቃል።
ከዚህ ባሻገር አሁን የብልጽግና ፓርቲ ቢሮ ገንብቶ እያስመረቁ ያሉት አንዳንድ ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ አንድም የራሳቸውን ቢሮ ገንብቶ የማያውቁ የወረዳ አስተዳደር ቢሮ ጭምር የሌላቸ ናቸዉ። ለአብነት ሙሉ በሙሉ ወይም በአብዛኛው ቢሮ የለላቸዉ ወረዳዎች ስንፈልግ በትንሹ የሚከተሉትን እናገኛለን፦ ጭሮኔ፣ ቡራ፣ ዳኤላ፣ ሻፋሞ፣ ሆኮ፣ ቡርሳ፣ ቦና፣ ቦካሶ ወንሾ እና ወዘተ ናቸዉ።
እነዚህ ወረዳዎች በከፍል ከዛሬ አስራ ዘጠኝ አመታት በፊት የተመሰረቱ፤ ሌሎቹ ደግሞ ከዛሬ ስምንት አመታት በፊት የተቆረቆሩ ወረዳዎች ሆኖ ቢሮ ሳይኖራቸዉ ክራይ እየከፈሉ እየኖሩ፤ ትናንት የተፈጠረውን ብልጽግና ቢሮ ለመገንባት ህዝብን አስተባብረን (አስገድዶ፣ አስሮ፣ ገርፎና አሰቃይቶ) ህንጻ አስገነባን ስባል ነገሩ ትርጉም የሚያጣዉ እዝህ ላይ ነዉ።
በሌላ በኩል እነዚህ ግንባታዎች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የሌላቸዉ ከመሆኑም ባለፈ፤ ይህ ሁሉ ለአንድ ፓርቲ ህንጻ በየወረዳው ገንብቶ መክፈት፤ በአንጻሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተከራይቶ እንኳ የሚከፍቱት ቢሮዎች መስበር፣ ፓይፔላ መስረቅ፣ አባላትን ማሰር፣ ማሳደድ፣ ባለበት አንድ ፓርቲ ብቻ ይህንን ያህል ማስፋፋት ዬትም አያደርስም። እነዚ ስራዎች ትርጉም የሚያጡበት ሌላኛው ምክንያት ይህ ነዉ።
ስጠቃለል በአራት ምክንያት እነዚህ የቢሮ ግንባታዎች ትርጉም የሚያጡበት ይሆናሉ፦
1, በህዝባ ትብብር የተገነቡ መሆናቸውን ብነገርም እዉነታዉ ግን ተቃራኒ ሆኖ እናገኛለን። ለመዋጮ ግለሰቦችን፣ ሰራተኞችን፣ አርሶአደሮችን፣ ማስገደድ፣ ማሰር፣ ማስፈራራት እና ማሰቃየት የታከለበት በመሆኑ፤
2, ቢሮዎች እየተገነቡ ያሉት ወረዳዎች ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡበት አንድም የራሳቸዉ ቢሮ የሌላቸው በመሆኑ፤
3, እነዚህ ግንባታዎች ኢኮኖሚያዊ እና ህዝባዊ አገልግሎት ፋይዳ የለላቸዉ ከመሆኑም ባሻገር በስዉር የክልሉ ባለስልጣናት የማዕከላዊ መንግሰስት ልብ ለመማረክ እና ለብልጽግና ታማን አገልጋዮች መሆናቸዉን ብቻ ያሳዩበት በመሆኑ፤
4, ሌሎች ተቃማዊ ፓርቲዎች አንድም ቢሮ በወረዳዎችም ሆነ ሀዋሳ ከተማ መክፈት እንዳይችሉ ተደርጎ የዲሞክራሲ መህዳር የተዘጋበት በመሆኑ፤ ትርጉም የሌላቸው እና ራዕይ የማጣት ማሳያ መሆኑን ያስገነዝባሉ።
ሉዋ ሚዲያ