Wollo Gerageru= ወሎ ገራገሩ

Wollo Gerageru= ወሎ ገራገሩ Wollo Wollo

68 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጀልባ መስጠም አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።" በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው " - ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM)በየመን...
04/08/2025

68 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጀልባ መስጠም አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።
" በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው " - ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM)

በየመን አብያን ግዛት ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በመስጠሟ ቢያንስ 68 ስደተኞች መሞታቸውንና 74 ስደተኞች ደግሞ የደረሱበት እንደማይታወቅ ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

በየመን የድርጅቱ ተወካይ አቤዱሳቶር ኢሶቭ ለአሶሼትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል " በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ #ኢትዮጵያውያን ናቸው " ብለዋል።

ኢሶቭ በሰጡት ቃል፤ ' ካንፋር ' በተባለ አካባቢ የ54 ስደተኞች አስክሬን በውቅያኖስ ዳር የተለያየ ቦታ ወድቆ መገኘቱን በሌላ ቦታ የተገኘ 14 አስክሬን ወደሆስፒታል መላኩን ተናግረዋል።

12 ሰዎች ደግሞ በህይወት መትረፋቸው ተመላክቷል።

እንደ ተወካዩ ገለፃ ኢትዮጵያውያኑ አደጋው የደረሰባቸው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው።

🥺..
01/08/2025

🥺..

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት በደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና ድጋፍ ሰጪ መሰረተ ልማቶችን አስመረቀ። የምርቃት ሥነ ስርዓቱ...
01/08/2025

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት በደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና ድጋፍ ሰጪ መሰረተ ልማቶችን አስመረቀ። የምርቃት ሥነ ስርዓቱ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በተገኙበትበደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።


ከ12 ሚልየን ዩሮ በላይ በፈጀ የፕሮጀክት ወጪ የተገነባው ይህ መሰረተ ልማት 3,500 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል፣ ቪአይፒ ተርሚናል፣ እንዲሁም ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ሕንፃዎችን እና መሰረተ ልማቶችን ያቀፈ ሲሆን ወደ ከተማዋ የሚጓዙ መንገደኞችን ምቾት ይበልጥ የሚያሳድግ ነው።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ተጫዋቾች ከቡድኑ ተነጥለው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደርጓል !!በብሔራዊ ቡድናችን የአሜሪካ ጉዞ ላይ በቡድን ስብስቡ ተካተው ወደ ስፍራው ያመሩት ዮሴፍ ታረቀ...
04/08/2023

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ተጫዋቾች ከቡድኑ ተነጥለው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደርጓል !!

በብሔራዊ ቡድናችን የአሜሪካ ጉዞ ላይ በቡድን ስብስቡ ተካተው ወደ ስፍራው ያመሩት ዮሴፍ ታረቀኝ እና ብርሃኑ በቀለ ከጉያና ጋር ከተደረገው ጨዋታ አስቀድሞ የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የዲሲፕሊን ጉድለት በማሳየታቸው ሁለቱም ተጫዋቾች ከጨዋታው ውጪ እንዲሆኑ የተደረጉ ሲሆን ሐሙስ ሐምሌ 27/2015 በአሜሪካ ከሚገኘው ቡድን ተነጥለው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ውሳኔ ተላልፎ ሀገር ቤት ደርሰዋል።

23/06/2023

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollo Gerageru= ወሎ ገራገሩ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share