
16/03/2025
ጉረባእ ኢስላማዊ ድርጅት ከቡራዩ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት እና ከሸገር ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ሊግ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት "አህለን ረመዳን" የተሰኘ የዳዕዋ ኮንፈረንስ ተካሄደ!
ጉረባእ ኢስላማዊ ድርጅት ከቡራዩ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት እና ከሸገር ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ሊግ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት "አህለን ረመዳን" የተሰኘ የዳዕዋ ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በቡራዩ ትልቁ ስታዲዮም ተካሂዷል።
በመርኀ ግብሩ ላይ የሸገር ከተማ መጅሊስ አመራሮች፣ የቡራዩ ክፍለ ከተማ መጅሊስ አመራሮች ዱዓቶች፣ ኡስታዞች እና ቃሪዎች እንዲሁም በርካታ የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ ተገኝቷል። በዝግጅቱ ላይ የተገኙ ኡለማኦችና ዱአቶች በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ ዳዕዋዎችን አቅርበዋል።
ጉረባእ ኢስላማዊ ድርጅት ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር ይህንን መሰል ዝግጅት ሲያዘጋጅ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ድርጅቱን በማጠናከር መሰል ስራዎችን በስፋት እንዲሰራ ማስቻል የህዝበ ሙስሊም ድርሻ ሊሆን ይገባል ተብሏል።