Mestawot Media

Mestawot Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mestawot Media, Media/News Company, Addis Abeba, Addis Ababa.

የአሜሪካን ተጫዋቾች ያረፉበት የ16 ቢሊየን ዶላር ሆቴል ።...............በፊፋ ህግ መሰረት ፡ የአለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ አልፎ ፡ ወደ አዘጋጇ ሀገር የሚሄደው የእግር ኳስ ቡድን ...
23/11/2022

የአሜሪካን ተጫዋቾች ያረፉበት የ16 ቢሊየን ዶላር ሆቴል ።...............
በፊፋ ህግ መሰረት ፡ የአለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ አልፎ ፡ ወደ አዘጋጇ ሀገር የሚሄደው የእግር ኳስ ቡድን ፡ ጠቅላላ የሆቴልና የኢንሹራንስ ወጭ የሚሸፈነው ፡ በየተሳታፊው ሀገር የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካኝነት ነው ። እናም ተሳታፊው ሀገር ፡ አቅሙ የሚችለውን ሆቴል መርጦ ፡ መያዝ ይችላል ። ስለ
ሆነም የዚህ አይነት ውድድሮች ሲካሄዱ ተሳታፊ ሀገራት ያላቸውን የኢኮኖሚ አቅም ያሳዩበታል ። በኢኮኖሚ ያልዳብረው ሀገር ቡድን ይዟት የመጣውን ዶላር ለማብቃቃት ፡ ዋጋው ውድ ያልሆነ ሆቴል ሲመርጥ ፡ እንደ አሜሪካን ያሉ ሀብታም ሀገራት ደግሞ ፡ እጅግ ውድ የተባለውን ሆቴል መርጠው ተጫዋቾቻቸው በምቾት እንዲያሳልፉ ያደርጋሉ ።.................

በኳታር የአለም ዋንጫም የተከሰተው ይኼው ነው ። ሀብታም ሀገራት ትላልቅና ፡ ለአንድ ሌሊት በሺህ የሚቆጠር ዶላር የሚያስወጣ ሆቴል ይይዛሉ ፡ እንደካሜሩን አይነት ኢኮኖሚያቸው ያልዳበረ ሀገራት ደግሞ ፡ በአንድ ለሊት ከሰባት መቶ ዶላር በላይ በማይጠይቁ እንደ Banyan Tree አይነት መለስተኛ ሆቴሎች ላይ አርፈው ፡ በውድድሩ እስከሚቆዩበት ቀን ድረስ በዛ ያሳልፋሉ ።......................

ሀገር በኢኮኖሚ ልቃ ፡ ሀብታም እስካልሆነች ፡ ለአለም ዋንጫም ሄድክ ለስብሰባ ፡ ሁሌም ቅናሽ ያለበትን ትፈልጋለህ ። ምክንያቱም አላደክማ ።
የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ፡ ወደኳታር የገባው ፡ ውድድሩ ከመጀመሩ ከአስር ቀናት በፊት ነበር ። እናም ኳታር ኣንደደረሰ ፡ በቀጥታ ያመራው ፡ ሰው ሰራሽ ደሴት ላይ በተሰራው ፡ ለመገንባት 15 ቢሊየን በፈጀው The Pearl Doha ወይም Marsa Malaz Kempinski Hotel በሚባለው እጅግ የተቀናጣ ሆቴል ነበር ።.....................

ልክ በሆቴሉ ሲደርሱ ለአሜሪካኖች እንኳን አስደናቂ የሆነውን ስለዚህ ሆቴል ፡ የመሃል ተከላካዩ ብሬንደን አሮንሰን ሲናገር ፡ ይህ የማይታመን ነው ። በዚህ ሆቴል የማየው ሁሉ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መስተንጎዶና አገልግሎት ነው ። በማለት ያረፉበትን ሆቴን አድንቋል ።

ሌላው የቡድኑ አባል የሆነው የጆርጅ ዊሀ ልጅ ቲሞቲ ዊሃ ፡ በየክፍላችን ትላልቅ የቲቪ ስክሪኖች ያሉበት ፡ ትላልቅ አልጋዎችና ፡ የሚታየው ነገር ሁሉ በሚያስደንቅ በቃላት ለመግለፅ የሚያስቸግር የቅንጦት ሆቴል ውስጥ አርፈናል ፡ ሲል ተናግሯል ።

የቡድኑ አሰልጣኝም ፡ በዚህ የአለም ዋንጫ ቶሎ መሰናበት አንፈልግም ፡ መቆየት እንዳለብን ወስነን ነው የመጣነው እናም ይህን ለማድረግ ከሚያስፈልጉት ነገሮች አንዱ የተጫዋቾቻችንን ምቾት መጠበቅ ነው ። ለዚህም ነው እዚህ ያረፍነው በማለት ከተናገረ በኋላ ለተጫዋቾቹ ባስተላለፈው መልእክት ሻንጣችሁን ክፈቱ ፡ መፅሃፎቻችሁን ሼልፎች ላይ ደርድሩ ፡ ልብሳችሁን በቁምሳጥኑ ውስጥ አኑሩና ፈታ በሉ ፡ ሲል ተናግሯል ።.......................................
እናም የአሜሪካ ተጫዋቾች ፡ በያዙት ሁሉም ክፍሎች ውስጥ ሆነው ሰው ሰራሹን ደሴት ማየት ይችላሉ ፡ በያንዳንዱ ክፍል በተገጠመው ልዩ የቡና ማሽን ውድ ቡናቸውን በትልቅ ማግ ይይዙና ፡ ግድግዳው ላይ በተለጠፈው ግዙፍ የቴሌቪዥን ስክሪን ስፖርታዊ ክንውኖችን ወይም አስገራሚ ፍጥነት ባለው ኢንተርኔት የኔትፍሌክስ ፊልሞችን ማየት ። ወይም በሆቴሉ ውስጥ ባሉት ሰባት የተለያዩ ትላልቅ ሬስቶራንቶች በመሄድ ፡ ከአለም ዙሪያ የተሰበሰቡትን የምግብ ሜኑዎች ላይ የፈለጉትን ሀገር ምግብ መርጠው በአለም አቀፍ ደረጃ ውድ ተከፋይ በሆኑ ሼፎች የሚዘጋጀውን ምግብ ማጣጣም ይችላሉ ።

በሆቴሉ ውስጥ ባለው ትልቅ ሀይቅ በዘመናዊ የቅንጦት ጀልባ እየተንሸራሸሩ ይህን ካልፈለጉም በመዋኘትና የሜዳ ቴኒስ በመጫወት ጊዜያቸውን ማሳለፍ ይችላሉ ።.................
በመጨረሻም የአሜሪካን የእግር ኳስ ቡድን. ..በዚህ እጅግ ግዙፍና የራሱ የሆነ ሰው ሰራሽ ደሴት ባለው ሆቴል ፡ ከውድድድሩ እስከቆየበት ጊዜ ለያንዳንዳንዱ ተጫዋች ለአንድ ለሊት 16,500 ዶላር ይከፍላል ።

Wasihune Tesfaye

ኳታር ስለምታስተናግደው 22ኛው የዓለም ዋንጫ  ዝግጅት አስገራሚ እውነታዎች ፡-• የዓለም ዋንጫውን ካዘጋጁ አገራት ኳታር በጣም ትንሿ አገር ያደርጋታል።• በአረብ ሃገር የተዘጋጀ የመጀመሪያው...
19/11/2022

ኳታር ስለምታስተናግደው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዝግጅት አስገራሚ እውነታዎች ፡-

• የዓለም ዋንጫውን ካዘጋጁ አገራት ኳታር በጣም ትንሿ አገር ያደርጋታል።

• በአረብ ሃገር የተዘጋጀ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ነው።

• በዓለም ዋንጫው ታሪክ ኳታር ካወጣችው ወጪ አንፃር እጅግ ውዱ የዓለም ዋንጫ ያደርገዋል።

• ኳታር ለዓለም ዋንጫው በአጠቃላይ 220 ቢሊዮን ዩሮ በማውጣት ላለፉት 35 ዓመታት የተካሄዱ ተመሳሳይ7 የዓለም ዋንጫ ዝግጅቶች ከወጣው ወጪ ጋር ተቀራራቢ መሆኑ አነጋጋሪ ነው ።

• ለዓለም ዋንጫው ሙቀትን የሚያቀዘቅዝ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው 6 ቅንጡ ስቴዲየሞችን ገንብታ ዝግጁ አድርጋለች።

• ከዓለም ዋንጫው በኋላ የሚፈርሰው ከ974 ከንቴይነሮች የተገነባው ስታዲዬም 40ሺ ተመልካች በመያዝ በዓይነቱ ለየት ያለ ክስተት ሆኗል።

• ለዓለም ዋንጫው 3.2 ሚሊዮን ትኬቶች ተዘጋጅተዋል።

• 5 ሚሊየን ታዳሚዎች የዓለም ዋንጫን ለመታደም ኳታር ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል

• የኳታሩ ዓለም ዋንጫ የመጀመሪያው በበጋ የሚከናወን የዓለም ዋንጫ ነው።

• በእግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑ የአየር ሁኔታ ማስተካከያ የተገጠመላቸው ስቴድየሞች (air-conditioned stadiums) ኳታር ለዚህ ዓለም ዋንጫ አዘጋጅታለች።

• በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ዳኞች ዋና ዳኛ ሆነው በኳታር የዓለም ዋንጫ የምንመለከት ይሆናል።

• አፍሪካን የሚወክሉት 5ቱም ቡድኖች ለመጀመሪያ ጊዜ በአገራቸው አሰልጣኞች ይመራሉ ።

• በዚህ የዓለም ዋንጫ የሚሳተፈው በእድሜ ትንሹ ተጫዋች የጀርመኑ የሱፋ ሙኮኮ ሲሆን በእድሜ ትልቁ ደሞ የሜክሲኮው አልፌርዶ ታላቬራ ነው።

የዩክሬይኗ ርዕሰ ከተማ ኪየቭ በሰው አልባ በራሪ አካል ድሮን ተመታች፡፡ኪየቭ የተመታችው በኢራን ስሪቱ ካማካዚ ድሮን እንደሆነ ዩሮ ኒውስ ፅፏል፡፡በድሮን ጥቃቱ በኪየቭ በርካታ ፍንዳታዎች ተሰ...
17/10/2022

የዩክሬይኗ ርዕሰ ከተማ ኪየቭ በሰው አልባ
በራሪ አካል ድሮን ተመታች፡፡

ኪየቭ የተመታችው በኢራን ስሪቱ ካማካዚ ድሮን እንደሆነ ዩሮ ኒውስ ፅፏል፡፡

በድሮን ጥቃቱ በኪየቭ በርካታ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል ተብሏል፡፡

በጥቃቱ ማዕከላዊው የከተማዋ ክፍል በደፈናው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ተናግረዋል፡፡

ኪየቭ ሰሞኑንም በሩሲያ ተደጋጋሚ ከባድ የሚሳየል ጥቃት እንደተፈፀመባት ዘገባው አስታውሷል፡፡

ኪየቭ የሩሲያ ጦር ዒላማ ስትሆን ከብዙ ወራት ወዲህ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ሰበር መረጃመንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አየር ማረፊያዎችን እንደሚቆጣጠር አስታወቀ።የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነት ለማስጠበቅ ሲል፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ ...
17/10/2022

ሰበር መረጃ

መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አየር ማረፊያዎችን እንደሚቆጣጠር አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነት ለማስጠበቅ ሲል፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ አየር ማረፊያዎችንና በክልሉ የሚገኙ የፈዴራል መንግስት ተቋማትን እንደሚቆጣጠር አስታወቀ።

መንግስት ይህንን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደው ፣በህወሓት ኃይል ተደጋጋሚ ጥቃት ብቻ ሳይሆን ይህ ኃይል ከውጭ ኃይሎች ጋር በመሆን የአገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ እንደሆነ የመንግስት ኮሚንኬሼን አገልግሎት በዛሬው ዕለት ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።

ይህንን እርምጃ መውሰድ የኢትዮጵያን የአየር ክልል ማስከበርና የአገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነት አደጋ ላይ እንዳይወደቅ ማድረግ አስፈላጊ ነው የሚለው መግለጫው ፣ ለትግራይ ክልል ህዝብ አስፈላጊው የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርስም ጠቃሚ መሆኑን አክሎ ገልጿል።

አለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም IMF ባወጣው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ የዘንድሮው ኢኮኖሚያዊ እድገት 3.8 % ሆኖ ተመዝግቧል ። ይህ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት የእንግሊዝን የኢኮኖሚ እድገት የ...
14/10/2022

አለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም IMF ባወጣው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ የዘንድሮው ኢኮኖሚያዊ እድገት 3.8 % ሆኖ ተመዝግቧል ።

ይህ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት የእንግሊዝን የኢኮኖሚ እድገት የሚበልጥ ሲሆን ከአውስትራሊያ ጋር ደግሞ እኩል ደረጃ የሚያስቀምጣት ነው ። በዘንድሮው የኢኮኖሚ እድገት ኢትዮጵያ ያስመዘገበቺው የኢኮኖሚ ከ ቡድን 20 ሀገራት ሲነፃፀር የሚበልጧት አምስት ሀገራት ብቻ ናቸው ።

የኢትዮጵያ አመታዊ የኢኮኖሚ እድገት ከ ቻይና ፣ እንግሊዝ ፣ ፈረንሳይና ብራዚልን ከመሳሰሉ በሰፊው ያድጋሉ ተብለው ከተጠበቁ ሀገራት የበለጠ ሆኖ ተመዝግቧል ።

በተለይ ደግሞ ሶስት አመታትን ሙሉ በማያቋርጥ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሀገራችን በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ሆና ይህንን ማስመዝገቧ የሚያስደንቅ ነው ማለት ይቻላል ።

ገና ጦርነትን ከጀመሩ ጥቂት ወራት ብቻ የሆናቸው ዩክሬይንና ሩሲያ ኢኮኖሚያዊ እድገታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ተኮማትሮ ኔጌቲቭ ውስጥ ገብተው ሳለ ከፍተኛ የሉአላዊነት ትግል እና የሀገርን ህልውና የማስቀጠል ጦርነት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ከነ ቻይና የበለጠ ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስመዝገቧ የሚያስደስት ነገር ነው ።

እንደ IMF ትንበያ ከሆነ ኢትዮጵያ በመጪው አመት ከዚህ የበለጠ እድገት ታስመዘግባለች ። በተለይም ደግሞ ይህንን ጦርነት በአጭር ጊዜ መደምደምና ጠላቶቻችንን ማስወገድ ከተቻለ የኢትዮጵያ እድገት ወደ ሁለት ድጅት አሀዝ የማያድግበት ምክንያት የለም !

09/10/2022

#መከላከያ በህወሓት ላይ የመጨረሻ የተባለለትን ምት ለማሳረፍ የመንግስትን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ነው ተባለ!!!

@በጅግጅጋ ከተማ መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ ያለው የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከህወሓት በኃላ ስለትግራይ ሁኔታ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሏል።

@የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በባለሙያዎች እየተመሩ ክልሉ በሰራዊቱ ኮማንድ ፖስት ይተዳደር የሚልና እንደዚህ ቀደሙ በሲቪል ጊዜያዊ አስተዳደር ስር ትሁን የሚሉ ሁለት አማራጮች ለውሳኔ ቀርበዋል።

@የኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቪስ ከምንጮቼ አገኘሁት ብሎ ባጋራው መረጃ መሰረት ከሰሞኑ ከትግራይ ተውላጆች ጋር ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።

@በብልፅግና ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ የሚመሩና የትግራይ ተወላጆች የተካተቱባቸው የመልሶ ግንባታ እንዲሁም የሰብዓዊ ድጋፍ አሰራጭ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ወደ ስራ ገብተዋል።

@ወደፊት እየገሰገሰ ያለው የኢፌድሪ የመከላከያ ሰራዊት መንግስት ውሳኔ ካሳለፈ መቐለን ጨምሮ ትግራይን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር የሚያስችለውን ጥቃት ሊጀምር ይችላል።
Fasil Yenealem

የፌደራል መንግስት መግለጫ!!በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሰላም ንግግር ከሀገር ሉዓላዊነትና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓት አንፃር መታረም የሚገባቸው ጉዳዮችን ስለማሳወቅ!!የሰላም ንግግሩ የ...
07/10/2022

የፌደራል መንግስት መግለጫ!!

በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሰላም ንግግር ከሀገር ሉዓላዊነትና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓት አንፃር መታረም የሚገባቸው ጉዳዮችን ስለማሳወቅ!!

የሰላም ንግግሩ የሚካሄደው በሉዓላዊት ኢትዮጵያ ውስጥ በዴሞከራሲያዊ መንገድ በተመረጠ መንግሥትና በአንድ ዐማጺ ቡድን መካከል እንጂ፣ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል አስመስሎ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።

“የትግራይ መንግሥት (Government of Tigray) ፣ (State of Tigray)" ፤ "የትግራይ የውጭ ግንኙነት (Tigray External Service) የሚባል አገላለጽ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚፃረር ነው።

በሌላ በኩል “የትግራይ አስተዳደር” ወይም “የትግራይ ክልል መንግሥት" የሚባል አገላለጽም በሕገ መንግሥቱ መሠረት በሕጋዊ መንገድ በትግራይ ክልል ውስጥ የተመረጠ አካል ባለመኖሩ ተቀባይነት የለውም።

በመሆኑም ማንኛውም አካል ከላይ የተገጹትን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፤ የግዛት አንድነትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት የሚጥሱ አገላለጾችን ከመጠቀም ሊታቀብ ይገባል።

ግብፅና ወዳጆቿን ያስደነገጠው ጉብኝት! 🇪🇹 🇰🇪የዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ የጀመረዉ ጉብኝት በግብጽ እና በፈረሶቿ ዘንድ ከበድ መደናገጥን ፈጥሯል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሆነች ግብፅ ብዙ ...
06/10/2022

ግብፅና ወዳጆቿን ያስደነገጠው ጉብኝት! 🇪🇹 🇰🇪

የዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ የጀመረዉ ጉብኝት በግብጽ እና በፈረሶቿ ዘንድ ከበድ መደናገጥን ፈጥሯል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሆነች ግብፅ ብዙ ግዜ በኬንያ የጦር ሰፈር ሰርታ ፈረሶቿን አስታጥቃ ወደ ኢትዮጵያ እየላከች ኢትዮጵያ የማተራመስ ህልሟ በአቢቹ ዲፕሎማሲያዊ ስራ የቀን ቅዠት ሆኖ ቀርቷል።

ስለዚህ ግብጽ እና ፈረሶቿ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቋል። ከስፍራቸው በደረሰን መረጃ ሶማሊያ እና ጂቡቲ ከእጃችን በአብይ ወጥቷል። አልሸባብ ከኢትዮጵያ በደረሰው ጥቃት እየተዳከመ ስለሆነ ከእሱ ጋር የመስራት እቅዳችን እየተመናመነ ነው። አበቃን፤ተከበናል፤ አለቀልን በማለት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቋል።

መረጃ በፍጥነት ለማግኘት እዚህ👇ግቡ
https://t.me/mestawotmedia

የጥላቶቻችንን ማንነት በደንብ ነው የተረዳነው። አሁን የመጨረሻ መጀመሪያ ትግል ላይ ነን። አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን ነዳጅ ከቻይና ቀምቸ እኔ አለማለሁ አይነት ተማፅኖ ለአዲስ አበባ እያቀረበ...
06/10/2022

የጥላቶቻችንን ማንነት በደንብ ነው የተረዳነው። አሁን የመጨረሻ መጀመሪያ ትግል ላይ ነን።

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን ነዳጅ ከቻይና ቀምቸ እኔ አለማለሁ አይነት ተማፅኖ ለአዲስ አበባ እያቀረበች ነው። አሜሪካ ጋር የሚኖረን የነዳጅ ስምምነት የለም። ህወሓት የኢትዮጵያን መንግስት አሸንፎ የነዳጅ ስምምነቱን ለአሜሪካ የሚሰጥላት መስሏት ነበር ስትረዳው የነበረችው አሁን ግን እንደማይቻል አምናለች።

ድርድር የሚባል አለ አዎ አለ ግን የመደራደሪያ ነጥቡ ነው ፍሬ ነገሩ። ህወሓት ኢትዮጵያ መሬት ውስጥ ያለ አሸባሪ ነው። በኢትዮጵያ ህግ ይጠየቃል በኢትዮጵያ መንግስት ለህግ ይቀርባል ስለዚህ የኛን ህገ እንጅ የነሱን ፍላጎት አናከብርም ።

በሱሌማን አብደላ

የ12 ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከቀናት በኋላ እንደሚሰጥ ይታወቃል።  የጊዜ ሰሌዳው በ2 ዙር እንደሚከተለው ነው።1, በመጀመሪያ ዙር _ሶሻል ሳይንስ2, በሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስየሁለቱም...
01/10/2022

የ12 ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከቀናት በኋላ እንደሚሰጥ ይታወቃል። የጊዜ ሰሌዳው በ2 ዙር እንደሚከተለው ነው።
1, በመጀመሪያ ዙር _ሶሻል ሳይንስ
2, በሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ
የሁለቱም ዙር በሚከተለው ምስል ተቀምጧል።

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mestawot Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share