Cynoox Technology

Cynoox Technology Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Cynoox Technology, Social Media Agency, Addis ababa, Addis Ababa.

09/05/2025

10 Best Free Websites to Learn English
Link On comment
👇👇👇

በጉራጌ ዞን የመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች አካባቢ ግጭት መረጋጋቱን ፖሊስ አስታወቀየሰላማዊ ሰዎችን ግድያ ተከትሎ፣ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች አካባቢ፣ ዳግም የተቀስቀሰ...
05/08/2023

በጉራጌ ዞን የመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች አካባቢ ግጭት መረጋጋቱን ፖሊስ አስታወቀ

የሰላማዊ ሰዎችን ግድያ ተከትሎ፣ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች አካባቢ፣ ዳግም የተቀስቀሰውን የጸጥታ ሁከት እና ግጭት፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ ፖሊስ ማረጋጋቱን፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ዓለማየሁ ማሞ ለVOA ገልፇል።

በምሥራቅ መስቃን፣ ሰሜን ዲዳ በምትባል ቀበሌ፣ ወደ ገበያ በማቅናት ላይ የነበሩ ሰባት ሰዎች እንደተገደሉ፣ ፖሊስ ማረጋገጡን ገልጸዋል።

ነዋሪዎች፣ አካባቢው እንደተረጋጋ እና ወደ አንጻራዊ ሰላም እንደተመለሰ ተናግረው፣ ዳሩ ግን ወንጀለኞቹ ባለመያዛቸው፣ የደኅንነት ስጋት እንደሚሰማቸው ተናግረዋል።

ከሰኔ 25 ቀን እስካለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ፣ 20 ሰዎች እንደተገደሉ፣ የምሥራቅ መስቃን ወረዳ ፖሊስ፣ ለአሜሪካ ድምፅ መግለጹ አይዘነጋም።

ሁለት የዎላይታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቡት ክስ ላይ ብልፅግና ፓርቲ ፍርድ ቤት ባለመቅረቡ በሌለበት የክስ ሂደቱ ይቀጥል ተባለ! የዎላይታ ህዝብ ጥያቄ ክልልነት እንጂ ክላስተር አይደም ህገ ...
05/08/2023

ሁለት የዎላይታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቡት ክስ ላይ ብልፅግና ፓርቲ ፍርድ ቤት ባለመቅረቡ በሌለበት የክስ ሂደቱ ይቀጥል ተባለ!

የዎላይታ ህዝብ ጥያቄ ክልልነት እንጂ ክላስተር አይደም ህገ መንግስቱ ተጥሷል በማለት ህዝበ ውሳኔውን በመቋወም ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር እና የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ሰኔ 8/2015 ዓም የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤትን ጨምሮ ስምንት ተቋማት ላይ ክስ መስርቶ እንደነበር ይታወሳል።

ፍርድ ቤት ሐምሌ 7/2015 በዋለው ችሎት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ሐምሌ 24/2015 ከብልፅግና ፓርቲ ውጪ ሌሎች 7 ተቋማት መልሳቸውን አቅርበው ዛሬ የመቃወሚያ ክርክር ለማድረግ ቀጠሮ ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ብልፅግና ፓርቲ ምላሽም አልሰጠም ፍርድ ቤት ሊቀርብ አልቻለም ሌላው የደቡብ ክልል ምክር እና የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ፍርድ ቤት ባለመቅረባቸው ፍርድ ቤቱ ሁለት ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለቀጣይ ቀጠሮ መስጠቱን ገልፇል።

ውሳኔዎቹ ብልፅግና ፓርቲ ፍርድ ቤት ተጠርቶ ባለመቅረቡ የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አክብሮ መገኘት ባለመቻሉ በሌለበት ክሱ እንዲቀጥል እና ውሳኔ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ ተላልፏል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት እና የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት መልሳቸውን ያቀረቡ ቢሆንም ተገኝተው ባለመከራከራቸው የመከራከር መብታቸው ተነፍጎ ሂደቱ እንዲቀጥል ውሳኔ መተላለፉን የፓርቲዎቹ ተወካዮች ገልፇል።

ፍርድ ቤት ጥቅምት 2/2016 ዓም ፍሬ ነገር ክርክር ለማድረግ ቀጠሮ መስጠቱን የፓርቲዎቹ ተወካዮች ገልፇል።

ያለመከሰስ መብት ያለውን የህዝብ እንደራሴ አቶ ክርስቲያን ታደለን ፌደራል ፖሊስ  አስሮታል።
05/08/2023

ያለመከሰስ መብት ያለውን የህዝብ እንደራሴ አቶ ክርስቲያን ታደለን ፌደራል ፖሊስ አስሮታል።

የአዲስ አበባ የምክር ቤት አባል የሆኑትን ዶክተር ካሳ ተሻገርን በሌሊት ፖሊሶች ቤቱ ድረስ መጥተው አስረውታል❗❗
05/08/2023

የአዲስ አበባ የምክር ቤት አባል የሆኑትን ዶክተር ካሳ ተሻገርን በሌሊት ፖሊሶች ቤቱ ድረስ መጥተው አስረውታል❗❗

 ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ " አማራ ክልል " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።አመሻሹን ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ እንዲሁም የ...
04/08/2023



ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ " አማራ ክልል " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

አመሻሹን ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና ተከለከሉ ተግባራት ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።

በዚህም ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬከተር ጄነራል የሚመራ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ መቋቋሙ ተገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ አባላት፣ መዋቅር እና አደረጃጀት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።

የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ጠቅላይ ዕዙ ተጠሪነት ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆንም ተገልጿል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎችና የተከለከሉ ተግባራት ምንድናቸው ?

- ማንኛውም ሰው በአዋጁ መሰረት የሚወጡ መመሪያዎችን፣ የሚሰጡ ትዕዛዞች እና የሚተላለፉ ውሳኔዎችን የመተግበር እና የማከበር ግዴታ አለበት ተብሏል።

- የአስቸኳይ ጊዜ ጠ/መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ #የሚቃረን ፣ #የሚቃወም እና በክልሉ የአመጽ እንቅስቃሴን የሚያበረታታ ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር፣ እንዲሁም የፀጥታ መደፍረሱን የሚያባብስ ንግግር፣ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ቅስቀሳ በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጭት የተከለከለ መሆኑ ተመላክቷል።

- በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ለታጣቂ ቡድኖች የገንዝብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

- ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንዲሁ ተከልክሏል።

- ከአስቸኳይ ጊዜ ጠ/መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተመላክቷል።

(ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ከላይ ያንብቡ)

"ፈተናው  ከስርቆትና ከኩረጃ ነጻ ሆኖ ተጠናቋል" ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ  የ2015 ዓ.ም የ12...
04/08/2023

"ፈተናው ከስርቆትና ከኩረጃ ነጻ ሆኖ ተጠናቋል" ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከማንኛውም ፈተና ስርቆትና ኩረጃ ነጻ በሆነ መልኩ ተጠናቋል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን እና ተማሪዎችም ፈተናውን በሰላማዊና በተረጋጋ ሁኔታ መውሰዳቸውን ገልፀዋል።

በአጠቃላይ 840 ሺ 859 የማህበራዊ ሳይንስና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በ2 ሺ 785 የፈተና ጣቢያዎች ተፈትነዋል።

ከሀምሌ 19 እስከ ሀምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር በተሰጠው ፈተና ከ30ሺ 438 የሚበልጡ ፈተና አስፈጻሚዎች መሰማራታቸውንም አመላክተዋል፡፡

በህግ ጥላ ስር ላሉ 515 ተፈታኞችና በኢትዮጵያ ለሚማሩና በውጭ አገር ለሚኖሩ ተፈታኞች ከነሀሴ 23 እስከ 26 ድረስ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጣቸው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በፈተናው በጉዞ ሂደት ያጋጠመ ቀላል የትራፊክ አደጋ፣ በህመም ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶችን ወደ ፈተና ጣቢያ ይዞ መግባት በመሞከር ችግሮች ማጋጠማቸዉን ገለጸው ከዚህ ባሻገር በፈተና ሂደት የጎላ ችግር አለማጋጠሙንም ጠቁመዋል።

በጎንደር ዩኒቨርስቲ 3 ካምፓሶች ትናንት ባጋጠመ ችግር 16 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን ሳይፈተኑ መቅረታቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ በቀጣይ በሚመቻች መርሀ ግብር የሚፈተኑ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

 #ሰበርየኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴ፣  ጎንደር እና ላሊበላ የሚያደርገው የቅዳሜ እና እሁድ በረራዎች የተሰረዙ መሆኑን አሳውቋል።ወደተጠቀሱት አካባቢዎች ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞቹ ...
04/08/2023

#ሰበር

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴ፣ ጎንደር እና ላሊበላ የሚያደርገው የቅዳሜ እና እሁድ በረራዎች የተሰረዙ መሆኑን አሳውቋል።

ወደተጠቀሱት አካባቢዎች ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞቹ በረራዎቹ እንደተመለሱ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ግጭት ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ተጫዋቾች ዮሴፍ ታረቀኝ እና ብርሃኑ በቀለ ብሔራዊ ቡድኑ በአሜሪካ እያደረገ በሚገኘው ዝግጅት ወቅት የ...
04/08/2023

የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ግጭት ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ተጫዋቾች ዮሴፍ ታረቀኝ እና ብርሃኑ በቀለ ብሔራዊ ቡድኑ በአሜሪካ እያደረገ በሚገኘው ዝግጅት ወቅት የእርስበርስ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ተጨዋቾቹ የዲሲፕሊን ጉድለት በማሳየታቸው ምክንያት ከጉያናው የወዳጅነት ጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ የተደረጉ ሲሆን ሐሙስ ሐምሌ 27/2015 በአሜሪካ ከሚገኘው ቡድን ተነጥለው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ውሳኔ ተላልፎ ሀገር ቤት መድረሳቸው ይፋ ሆኗል።

ግልጽ ደብዳቤ!ለክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድለተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔለክቡር አቶ ቴዎድሮስ ም...
04/08/2023

ግልጽ ደብዳቤ!
ለክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
ለተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ
ለክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፦ አስቸኳይ አገር አድን ውይይት እንዲደረግ በድጋሚ ስለመጠየቅ፣

እናት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባወጣነው የጋራ መግለጫ በአገራችን እየተስተዋለ ያለውን ውስብስብ ችግር ለመፍታትና የአገራችንን ህልውና ለመታደግ አስቸኳይ የአገር አድን እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ያደረግን ሲሆን ይህንኑ የሚገልጽ ደብዳቤ በአድራሻ ማስገባታችን ይታወሳል። በዚህም መግለጫ እና ደብዳቤ የሰላሳ ሁለት ዓመታት እኩይ ዘር ፍሬ ለሆነውና ዛሬ ላይ አገራችን ለተደቀነባት ሁለንተናዊ ችግር ብቸኛ መፍትሄሔ በምትመሩት መንግሥት፣ ነፍጥ አንስተዉ ዉጊያ ላይ በሚገኙ ኃይሎች እና ሕጋዊ እውቅና ኖሯቸው በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አስቸኳይ የአገር አድን ውይይት ማድረግ መሆኑን በመግለጽ ይኸው አገር አድን ውይይት አንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ እንዲጀመር መጠየቃችን ይታወሳል። ይሁን እንጂ ጥያቄያችንን ካቀረብን ከሶስት ሳምንታት በላይ የተቆጠረ ቢሆንም አገርን ከከፋው አደጋ ለመታደግ ያለመውን ማሳሰቢያችንን ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ይልቁን እልህና ፉክክር የተላበሰ በሚመስል መልኩ ግጭቱ እየሰፋ መጥቶ መላው የአማራ ክልል ወደ ጦር አውድማነት እየተለወጠ መሆኑን እየተመለከትን ነው። በዚህ ጦርነት መሣሪያ ያልታጠቁ ንጹሐን ዜጎችም ሕይወት እያለፈ መሆኑን፤ ብሔራዊ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎችም ላይ በዚሁ ምክንያት መተጓጎል እንደደረሰባቸው ለመረዳት ችለናል።

አገር ትምህርት መውሰድ ያለባት ከሌላ ሳይሆን የአንድ ሚሊየን ልጆቿን ህይወት ከቀጠፈው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሊሆን እንደሚገባ በማመን አገራችን ላይ ላንዣበበው የከፋ አደጋ ብቸኛ መፍትሄ አስቸኳይ ሁሉን አቀፍ ውይይት መሆኑን ዛሬም አጽንኦት ሰጥተን በደጋሚ ልናሳስብና ዛሬ ነገ ሳይባል መንግሥት ራሱን ዝግጁ አድርጎ በገለልተኛ አገር ውይይት እንዲጀመር አጥብቀን እንጠይቃለን። መንግሥት ድጋሚ ያቀረብነውንና ለአገር ባጠቃላይ እንዲሁም በሥልጣን ላይ ላለው መንግሥት መውጫ መንገድ ሆኖ ሊያገለገል የሚችለውን ይህን የአገር አድን ውይይት ሃሳብ ቸል በማለት በሚወስደው የኃይል እርምጃ እና ይህን ተከትሎ ለሚደርሰው ጉዳት ሙሉ ተጠያቂነት እንደሚወስድ አጽንኦት ሰጥተን እናሳስባለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ የዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ

የሸኔ ታጣቂዎች በጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተገለጸበደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ዋና መቀመጫ በሆነችው ቡኢ ከተማ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት...
04/08/2023

የሸኔ ታጣቂዎች በጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተገለጸ

በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ዋና መቀመጫ በሆነችው ቡኢ ከተማ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” በሚል በአሸባሪነት የተፈረጀው ኃይል፤ በከተማው በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የተፈጸሙት በረቡዕ ሐምሌ 26/2015 ሌሊት አምስት ሰዓት ገደማ መሆኑን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ፤ ጥቃቱ በፖሊስ ጣቢያው የታሰሩ ከ30 በላይ የሽብር ቡድኑን አባላት ለማስፈታት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የታጣቂ ቡድኑ አባላት ወደ ከተማው የገቡት በሞተር ሳይክልና በባጃጅ ተሸከርካሪዎች መሆኑን ጠቅሰውም፤ ከፖሊስ ጣቢያው ጠባቂ ፖሊሶች ጋር ለአንድ ሰዓት ያህል የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

አርቲስት አብርሃም ወልዴ እና ባለቤቱ ወ/ሮ ማክዳ ኃ/ሚካኤል 1.9 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ!!አርቲስት አብርሃም ወልዴ እና ባለቤቱ ወ/ሮ ማክዳ ኃ/ሚካኤል በጋብቻቸው ወቅት በጎፈንድሚ እና...
04/08/2023

አርቲስት አብርሃም ወልዴ እና ባለቤቱ ወ/ሮ ማክዳ ኃ/ሚካኤል 1.9 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ!!

አርቲስት አብርሃም ወልዴ እና ባለቤቱ ወ/ሮ ማክዳ ኃ/ሚካኤል በጋብቻቸው ወቅት በጎፈንድሚ እና በሀገር ውስጥ ባንኮች ያሰባሰቡትን ገንዘብ ለ4 አካባቢዎች ድጋፍ አደረጉ።

👉 ሰቆጣ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አንድ ሚሊዮን ብር
👉 ደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች 400,000 ብር
👉 በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለሚገኘው ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት 250,000 ብር
👉 ፊቼ ሰላሌ ለሚገኘው ፍቅር የተቀናጀ የማህበረሰብ የልማት ድርጅት 250,000 ብር ድጋፍ አድርጓል።

ከዚህ ቀደም ለመቄዶኒያ የ300ሺ ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ድጋፉ እስካሁን የቆየው በጎፈንድሚ የተሰበሰበው ገንዘብ ለአሸባሪ ነው በማለት ሰዎች ሪፖርት ስላደረጉ ገንዘቡን ለማስለቀቅ ረጅም ጊዜ እንደወሰደ አርቲስት አብርሃም ወልዴ ተናግሯል።

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Cynoox Technology posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Cynoox Technology:

Shortcuts

Share