
27/02/2024
♦ እናቶች እና አዛውንቶች በስብሰባ ላይ ተማጽኖ አቅርበዋል ፤ ሆኖም ግን ዶሮ ማነቂያ ሰፈር ሙሉ ለሙሉ ሊፈርስ ነው !
በተለምዶ አጠራር ዶሮ ማነቂያ እየተባለ የሚጠራው እንደሚፈር በዛሬው ዕለት የአካባቢው ነዋሪዎች በወረዳ 5 የሰብሰባ አዳራሽ ተጠርተው ፤ ዶሮ ማነቂያ አካባቢ ሙሉ በሙሉ በአስቸኳይ እንደሚፈርስ ለነዋሪዎቹ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል ።
የዶሮ ማነቂያ ሰፈር ነዋሪዎች ፤እናቶች እና አዛውንቶች በስብስ ላይ ተማጽኖ አቅርበዋል ፤ እባካችሁን በችኮላ የንግድ እና የመኖሪያ ቤታችን አታፍርሱብን ፣ እኛ ልማት አንጠላም ፣ በአካባቢው የዕለት ጉርሳችን በተለያየ ሥራ ተሰማርተን እየሰራን ኑራችንን እየገፋን ነው ያለነው። ግዜ ስጡን እንመካከር እትብታችን ከተቀበረበት ዝም ብላችሁ አታፈናቅሉን ፣ ድህነት ወንጀል አይደለም ፣ለከተማ ገፅታ ሲባል እኛን አድራሻ አታሳጡን ፤ እኛ ድሆችን በማዕከለ መልኩ ከተማውን ማስዋብ ትችላላችሁ ፤ እባካችሁን ሕይወታችን አተመሰቃቅሉ በማለት ነዋሪዎች ተማጽኖ አቅርበዋል።
ከቀናቶች በፊት ፤ ማህበራዊ ፍትህ አመጣለሁ የሚለው "ኢዜማ" የፓርቲውም ከፍተኛ የመንግስት ሹመኛ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ፤ ለከተማ ገፅታ ሲባል ድሆች በፍቃደኝነት ለቀው ወደ ሌላ ይዛወሩ የሚል የአለቆቻቸውን ሐሣብ አስቀድሞ ማቅረባቸው የሚዘነጋ አይደለም ።
የአዲስ አበባ ተወላጅ እና ነዋሪ ወደየትም ሳይዘዋወሩ ፤ የአዲስ አበባን የከተማውን ገጽታ መገንባት አይቻልም ወይ ?! ድሃን ከአዲስ አበባ የማፅዳት ዘመቻ ማብቂያው የት ሰፈር ነው ?! ማነው ባለሳምንት ?!
ይድነቃቸው ከበደ