
30/08/2025
የተመድን 80 ዓመታት ያስቆጠሩ እሴቶች ለማደስ ጊዜው አሁን ነው - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባዔ 2025 ላይ ለመሳተፍ ቻይና ተገኝተዋል።
አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ዛሬ በቲያንጂን ከተማ ውይይት አድርገዋል።
በወቅቱም ተመድ በዓለም አቀፍ የአስተዳደር መዋቅሩ ላይ አስቸኳይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ጉቴሬዝ ገልጸዋል።
በድርጅቱ ከ80 ዓመታት በፊት የተቀመጡ የመጀመሪያዎቹን እሴቶች ለማደስም ጊዜው አሁን ነው ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል።
ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው፤ ቻይና ሁልጊዜም የተመድ አስተማማኝ አጋር ሆና እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
ከድርጅቱ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር እና ድርጅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ሚና ለመደገፍ ፕሬዚዳንቱ ቃል ገብተዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ