
16/06/2025
አመራሩ ሕዝብን በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ለማገልገል መዘጋጀት አለበት - አቶ ሙስጠፌ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2017 በየደረጃው ያለ አመራር ሕዝብን በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀት አለበት አሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በአፍሪካ አመራር ልቀት አካዳሚ ለክልሉ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቅቋል።
አቶ ሙስጠፌ በዚህ ወቅት ÷ የለውጡን መልካም ጅምሮችና እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን የሚያስቀጥል ጠንካራ አመራር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አመራሩ ከምንም በላይ ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንዳለበት የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ ለዚህም በእውቀት የሚመራ ሙሉ ፍላጎትና ዝግጁነት ያለው አመራር ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡
በመሆኑም በየደረጃው ያለ አመራር ሕዝብን በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።
በሁሉም ዘርፎች አሁን ላይ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ እየታገዙ፣ በእውቀት የሚመሩና በብቃትና ክህሎት የሚሰጡ በመሆኑ ከጊዜው ጋር እውቀትንና ብቃትን ማሳደግ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
በክልሉ በሁሉም መስኮች አስደናቂ የልማት ሥራዎችና ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው÷ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና በትኩረት እንደሚሰራ ማስገንዘባቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!