SHEWA Online

SHEWA Online ለእኩልነት፣ ለፍትሕና ለነፃነት

ስውሯ ማርያም! ለብዙ ምዕመናን ፈውስ እየሰጠች ያለችው ስውሯ ማሪያም ''ደብረ ብርሃን'' ጠባሴ ክፍለ ከተማ ትገኛለች። ለብዙዎቻችሁ ፈውስ ከለላ ትሁናችሁ🙏💚💛❤️
13/10/2024

ስውሯ ማርያም!

ለብዙ ምዕመናን ፈውስ እየሰጠች ያለችው ስውሯ ማሪያም ''ደብረ ብርሃን'' ጠባሴ ክፍለ ከተማ ትገኛለች። ለብዙዎቻችሁ ፈውስ ከለላ ትሁናችሁ🙏💚💛❤️

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዘመን መለወጫን በዓል አስመልክተው የእንኳን...
10/09/2024

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዘመን መለወጫን በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

የብፁዕነታቸውን ሙሉ መልእክት እነሆ!!!
***** ***** ***** ***** *****

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

"ምድር ሠናይት እንተ ዘልፈ ይሔውጻ እግዚአብሔር አምላክከ ፤ ወአዕይንቲሁ ለእግዚአብሔር አምላክከ ላዕሌሃ እምርእሰ ዓመት እስከ ማኅለቅተ ዓመት "

"አምላክህ እግዚአብሔር የሚጎበኛት አገር ናት ፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በርሷ ላይ ነው"ዘዳ ፲፩ ÷ ፲፪

የተወደዳችሁ እና የተከበራችሁ በቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ በመላው ዓለምም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር 2016 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን በሰላም እና በጤና አስፈጽሞ እንኳን ለ2017 ዓም ዘመነ ማቴዎስ በሰላም እና በጤና አደረሰን! አደረሳችሁ!!!

የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር ዘመንን በዘመን እየለወጠ ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ 5500 ዓመተ ኲነኔ 2017 ዓመተ ምሕረት በአጠቃላይ 7517 ዘመን ይሆናል ።

እስራኤል ዘሥጋ በግብፅ ባርነት በነበሩበት ዘመን ተወልዶ በፈርኦን ቤት የፈርኦን ልጅ መባልን በእምነት እንቢ በማለት ያደገው ክቡደ መዝራዕት ሙሴ ከ4 መቶ 30 የግብፅ ባርነት ዘመን በኋላ እስራኤላውያንን ነጻ ለማውጣት በግብፅ እና በግብፃውያን ላይ ዘጠኝ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሥረኛ ሞተ በኲርን አሥራ አደኛ ስጥመትን ፈጽሞ በርሱ መሪነት በመልአኩ ተራዳኢነት በእግዚአብሔር አሻጋሪነት ቀይ ባሕር ተከፍሎላቸው በደረቅ አልፈው ከሞት ወደሕይወት ከባርነት ወደነጻነት ከውርደት ወደ ክብር ተሸጋግረዋል ።

በመሆኑም የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ በጸናች የእግዚአብሔር እጅ እስራኤል ዘሥጋን ከግብፅ የባርነት ሕይወት ነጻ አውጥቶ ሊወርሷት ወደአለችው የአባቶቻቸው ርስት የተስፋይቱ ምድር ከነአን ለመግባት በሞአብ ሜዳ ላይ በጉዞ ለነበሩት ለእስራል አዲሱ ትውልድ የምትወርሷት የበረከት ምድር ከነዓን ዝናብ እንደማይዘንብባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም።

የቃል ኪዳን ምድር ከነዓን የዘሩባትን የምታበቅል የተከሉባትን የምታጸድቅ እግዚአብሔር የሚጎበኛት የእግዚአብሔር ዓይን በረድኤት የማይለያት መሆኑን በመግለጽ በውስጧ በሰላም ለመኖር የባርነት ቀንበራቸውን ሰብሮ መና ከሰማይ አውርዶ እየመገበ ውኃ ከዓለት ላይ አፍልቆ እያጠጣ ያሻገራቸውን የእግዚአብሔርን ሕግ እና ሥርዓት ጠብቀው እንዲኖሩ በአጽንኦት ሲመክራቸው እናስተውላለን።

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን አባቶቻችን በአጥንታቸው እና በደማቸው አጽንተው ያስረከቡን ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ስሟ በመጽሐፍ ቅዱስ ተደጋግሞ የተወሳ ልክ እንደተስፋይቱ ምድር ከነዓን 3 መቶ 65 ቀናት ስመ እግዚአብሔር የሚጠራባት ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጸምባት እግዚአብሔር ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ በምሕረት ሀገረ እግዚአብሔር በምሕረት ዓይኑ የሚመለከታት ፣ መዝበ ታሪክ ዓይኑ የሚመለከታት ሀገረ እግዚአብሔር ፣ መዝገበ ታሪክ ፣ የቅርስ ማዕከል እና የሰው ዘር መገኛ መሆኗን እናስታወሳለን።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለየ ሁኔታ ከውስጥና ከውጪ እየደረሰ ባለው ፈርጀብዙ የተፈጥሮ እና የሰው ሠራሽ ችግር ምክንያት በአራቱም ማዕዘን በጦርነት ድምፅ እየተናጠች የፈተናና የመከራ ማዕበል እያንገላታት ትገኛለች።

በዚሁ ችግር ምክንያት የተነሳ በርካታ ወገኖቻችን መተኪያ የሌላት ውድ ሕይወታቸውን እያጡ ሲሆን ለዘመናት የደከሙበት ሀብት ንብረታቸው እየጠፋ ይገኛል።

ከቤት ቀያቸው ተፈናቅለው ለቀን ሀሩር ለሌሊት ቁር ተጋልጠዋል ፤ ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ተለይተው የለጋነት እድሜያቸውን በከንቱ እያሳለፉት ይገኛሉ ፤ በአጠቃላይ በሀገራችን እየሆነ ያለውን ነገር ስንመለከት ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እንገነዘባለን።

በመሆኑም ከዘመነ ዮሐንስ ወደዘመነ ማቴዎስ ስንሸጋገር እስራኤል ዘሥጋ ከግብፅ ወደከነዓን ሲሻገሩ የግብፅን ትብት በግብፅ ቀብረው ከሞት ወደሕይወት ከባርነት ወደነጻነት እንደተሻገሩ እኛም እስራኤል ዘነፍስ ያረጀውን ሰውነት ገፍተን አዲሱን ሰውነት በመልበስ አሮጌውን የኃጢኣት ርሾ አስወግደን አዲስን የጽድቅ ርሾ ገንዘብ በማድረግ ጥላቻን አውልቀን ፍቅርን በመልበስ መለያየትን ተጸይፈን አንድነትን በመጎናጸፍ የክርስቶስ መልክ መገለጫ የሆነውን የሰውን ልጅ በሰውነቱ ብቻ በማክበር በአዲስ ልብ በአዲስ አስተሳሰብ በአዲስ መንፈስ ልንሻገር የሚገባ መሆኑን በአጽንኦት ማሳሰብ እንፈልጋለን ።

ዘመነ ክረምት አልፎ አዲሱ ዓመት ሲገባ መስከረም ሲጠባ የወንዝ ውኃዎች ይጠራሉ አበባዎች ይፈካሉ የእኛም ሕይወት በንስሓ ውኃ ሊጠራ በበጎ ነገር ሁሉ ሊፈካ በአዲሱ ዓመት አዲስ ማንነት ሊኖረን ያስፈልጋል።

በመጨረሻም የዘመን መለወጥ ለሰው ልጅ ሕይወት ትርጉሙ ከፍ ያለ በመሆኑ በሕይወታችን ተለውጠን ስለ ሀገራችን እና ስለሕዝባችን በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት በመጸለይ የሰላም ሰው ሆነን ለሰላም የልባችንን በር በመክፈት እጃችንን ለፍቅርና ለአንድነት በመዘርጋት በማረሚያ ቤት ፣ በሆስፒታል እና በተለያየ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በመጠየቅ ፣ ያለንን ለሌላቸው ወገኖቻችን በማካፈል በይቅርታ ልብ መጪውን አዲሱን ዓመት እንድንቀበለው በማለት መልእክታችንን እናስተላልፋለን ።

መጪው አዲሱ ዘመን ዘመነ ማቴዎስ ሞት እና ጦርነት የሚቆምበት የጥይት ጩኸት የማንሰማበት የሀገራችን ችግር የሚፈታበት የሰላም የፍቅር እና የበረከት ዘመን እንዲሆንልን መልካም ምኞታችንን በመጸለይ ጭምር እንገልጽላችኋለን ።

ቅዱስ እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!!!

አባ ቀሌምንጦስ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ!!!

ጳጒሜን ፭ ቀን ፲፫ ወር ፳፻ ፲፮ ዓም
ሺዋ ደብረ ብርሃን ኢትዮጵያ!!!

10/08/2024

በደብረ ብርሃን ከተማ ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት በጦር መሳሪያ የታገዘ ውንብድና እና ዝርፊያ እየፈፀሙ ይገኛሉ።

በከተማዋ በርካቶች የእጅ ስልኮቻቸውንና የያዙትን ገንዘብ ተዘርፈዋል። ይሄውም የዝርፊያ ውንብድና የሚፈፀመው በሽጉጥ በማስፈራራት እንደሆነ ጥቃት የደረሰባቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ዝርፊያው የሚፈፀመው አንዳንድ ጊዜ የመንግስት የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ጭምር እንደሆነ ይነገራል። በእነዚህ ዘራፊዎች ከቀላል ጥቃት እስከ ህይወት ማጣት የሚደርስ ጥቃት የተፈፀመባቸው ነዋሪዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል።

ሰበር ዜናበአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በጥይት ተመተው በዛሬው እለት ህይወታቸው እንዳለፈ ታውቋል።
05/07/2024

ሰበር ዜና

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በጥይት ተመተው በዛሬው እለት ህይወታቸው እንዳለፈ ታውቋል።

ሰበር ዜና! ጀነራል ተፈራ ማሞ በይፋ የአማራ ፋኖን ትግል ተቀላቀሉ! የኢትዮ 251 ሚዲያ ምንጮች እንዳረጋገጡት ጄኔራል ተፈራ ማሞ በይፋ የአማራ ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ተቀላቅ...
01/07/2024

ሰበር ዜና!

ጀነራል ተፈራ ማሞ በይፋ የአማራ ፋኖን ትግል ተቀላቀሉ!

የኢትዮ 251 ሚዲያ ምንጮች እንዳረጋገጡት ጄኔራል ተፈራ ማሞ በይፋ የአማራ ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ተቀላቅለዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ከቤተክርስቲያን መልስ በእግር ጉዞ ላይ እንዳሉ በ"ኮሬ ነጌኛ" ገዳይ ቡድን የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የነበረው ጀኔራል ተፈራ ማሞ፣ ከግድያ ሙከራው ወታደራዊ ጥበባቸውን ተጠቅመው በማምለጥ አሁን ላይ በይፋ የአማራ ፋኖን ትግል መቀላቀላቸውን ኢትዮ 251 ሚዲያ ከፋኖ አመራሮች አረጋግጣለች፡፡

የጄኔራል ተፈራ ማሞ ይፋዊ በሆነ መንገድ የአማራ ፋኖን ትግል መቀላቀል የሕልውና ትግሉን በሞራል፣ በወታደራዊ አመራርና በሕዝባዊነቱ ላይ ከፍ ያለ መነቃቃት እንደፈሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

ጀኔራል ተፈራ ማሞ ገና ከአፍላ ዕድሜቸው ጀምሮ፣ ከ40 ዓመት በላይ የወታራዊ አመራር ልምድ ባለቤትና የሸማቂ ኮማንዶ መሪ በመሆን ወርቃማ የትግል ሕይወት ያሳለፉ ግንባር ቀደሙ ከፍተኛ መኮንን ናቸው፡፡

ከጀኔራል አሳምነው ጽጌና ሌሎች የትግል ጓዶቻቸው ጋር በመሆን የአማራ ልዩ ኃይልን በማደራጀትና የተዋጊነት አቅሙን በማሳደግ በአማራ ሕዝብ ትግል ውስጥ ልዩ ታሪክ መስራታቸው ይታወቃል፡፡

ጀኔራሉ፦ በኮማንዶ ሥልጠና፣ ኢንዶክትሪኔሽን፣ የአደረጃጀት፣ ወታደራዊ ስምሪት፣ ሎጀስቲክስ፣... ቅኝት፣ ተልዕኮ፣ ግዳጅ አፈጻጸም፣ ወታደራዊ ግምገማ፣ መልሶ ማደራጀት፣ የሽምቅ ውጊያ፣ የግንባር ፍልሚያ፣ የአንገት ቦታ ቁጥጥር፣ ገዥ መሬትን ቀድሞ መያዝ፣ ምሽግ ሰበራ፣ ... የተካኑቸው ወታደራዊ ጥበባቸው እንደሆኑ በቅርብ ጓዶቻቸው የተመሰከረላቸው ናቸው።

ጀኔራል ተፈራ ማሞ በይፋ የአማራ ፋኖን ትግል መቀላቀል ተከትሎ የመጀመሪያው ጀኔራል ያደርጋቸዋል፡፡

በጀኔራሉ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን በመከታተል ትኩስ መረጃዎችን ማድረሳችንን እንቀጥላለን፡፡

01/06/2024

አትሙት እኔ አልወድም

Alebachew

ውድ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወገኖቻችን ለ1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ።SHEWA Online
10/04/2024

ውድ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወገኖቻችን ለ1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ።

SHEWA Online

01/04/2024

አካውንታችሁ አላድግ ላላችሁ ምክር ከመከላከያ 😁😁😂😜

ወዮ መከላከያ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SHEWA Online posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share