ድሮን ቲዩብ DRONE TUBE

ድሮን ቲዩብ DRONE TUBE ሰብስክራይብ ላይክ በማድረግ የመልካም ስራ ልብ እና ጉልበት ይሁኑ

02/04/2025

Ethiopian wonderful team

29/03/2025
27/03/2025

⚠️ አስቸኳይ የማስጠንቀቂያ መልዕክት! ⚠️
በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አደገኛ ሊንኮችን (Links) በተመለከተ
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች (ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ፣ ወዘተ) ከሚያውቋቸውም ሆነ ከማያውቋቸው ሰዎች አጓጊ የሚመስሉ መልዕክቶች ከነማገናኛ ሊንኮቻቸው (links) ጋር በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።
እነዚህ መልዕክቶች በአብዛኛው‼️
"ነጻ የቴሌግራም ፕሪሚየም (Telegram Premium) አካውንት ያግኙ‼️
"በቀላሉ ገንዘብ የሚሰራበት አዲስ መንገድ‼️
"ይህን ሊንክ በመጫን ሽልማትዎን ይቀበሉ‼️
"አስገራሚ መረጃ ለማየት ይህን ይጫኑ!‼️
እና የመሳሰሉ የማታለያ ሀሳቦችን ይዘው ይመጣሉ።
ማስጠንቀቂያው፡‼️
እነዚህ ሊንኮች በውስጣቸው ተንኮል አዘል ሶፍትዌሮችን (ማልዌር) የያዙ ወይም የግል መረጃዎትን ለመስረቅ
(ሀክ ለማድረግ) የተዘጋጁ የማጭበርበሪያ ወጥመዶች ናቸው። ሊንኩን በመጫን ብቻ የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻችሁ (ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ወዘተ) ሊጠለፉ ይችላሉ።
የባንክ መረጃዎቻችሁ ወይም ሌሎች ሚስጥራዊ የግል መረጃዎቻችሁ ሊሰረቁ ይችላሉ።
በስልካችሁ ወይም በኮምፒውተራችሁ ላይ ያሉ መረጃዎች ሊበረበሩ ወይም ሊበላሹ ይችላሉ።
የእናንተን አካውንት በመጠቀም ለሌሎች ወዳጆቻችሁ ተመሳሳይ የማጭበርበሪያ መልዕክት ሊሰራጭ ይችላል።
ምን ማድረግ አለባችሁ ❓
በፍጹም እንዳትከፍቱት‼️ እንዲህ አይነት አጠራጣሪ፣ ያልጠበቃችሁት ወይም ከልክ በላይ አጓጊ የሆነ ሊንክ ሲደርሳችሁ በፍጹም እንዳትነኩት ወይም እንዳትከፍቱት። የላከልዎ ሰው የሚያውቁት ቢሆንም እንኳ ሊንኩን ከመክፈትዎ በፊት በሌላ መንገድ (ለምሳሌ በመደወል) ያረጋግጡ።
ወዲያውኑ አጥፉት‼️ መልዕክቱን እንደደረሳችሁ ወዲያውኑ አጥፉት
መረጃ አጋሩ‼️ ይህን የማስጠንቀቂያ መልዕክት ለጓደኞቻችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁ እና በምታውቋቸው ግሩፖች ላይ በማጋራት ሌሎችም እንዳይጠቁ የበኩላችሁን ተወጡ።
ያስታውሱ‼️ በበይነ መረብ ዓለም በቀላሉ የሚገኝ ነጻ ነገር ወይም በአቋራጭ የሚገኝ ያልተገባ ጥቅም ብዙ ጊዜ የማጭበርበሪያ ወጥመድ ነው።
🔍 የዲጂታል ደህንነታችሁ በእጃችሁ ነው።🔎
ከወንድማችሁ ዳዊት(ድሮን)

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ድሮን ቲዩብ DRONE TUBE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ድሮን ቲዩብ DRONE TUBE:

Share