20/09/2025
"የተሰጠው ሹመት ለእናት ሀገሩ ሲል ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ላለው ሠራዊት አባል ጭምር ነው" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
NBC Ethiopia
። ። ። ። ። ። ። ። ።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አቅርቢነት ለመከላከያ የጦር መኮንኖች ሹመት ሰጥተዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ "በአመራራችሁ ብቃት፤ በትጋታችሁ ልኬታ፤ በስትራቴጅያዊ እሳቢያችሁ፤ ለምትመሩት ሠራዊት ባላችሁ ፍቅር፤ ለተቋማችሁ፣ ለሀገራችሁ እና ሕዝባችሁ ባላችሁ ታማኝነት እና ጽናት፤ እንደወርቅ ተፈትናችሁ ለዚህ ታላቅ ክብር ስለበቃችሁ ምሥጋናዬን አቀርባለሁ" ብለዋል፡፡
ፕረኤዝዳንት ታዬ፣ የኢትዮጵያን የአርበኝነት ውርስ ላስቀጠሉ፣ ለሀገር እና ሕዝብ መታመንን፣ ክብር እና ጌጣቸው ላደረጉ ብሎም በዚህ ሰዓት ኢትየጵያዊ ግዴታቸውን እየተወጡ ላሉ ጀግና የኢትየጵያ ወታደሮች ምሥጋናቸውን አድርሰዋል።
ሹመቱ የተሰጠው ባሳዩት የሥራ ጥንካሬ፣ ታማኝነት እና የሀገር ፍቅር እንደኾነም ነው ለተሿሚወቹ የተናገሩት።
የተሰጠው ሹመት ለእናት ሀገሩ ሲል ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ላለው ሠራዊት አባል ጭምር እንደኾነም እንዲታወቅ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ሹመቱ ለሀገር እና ሕዝብ እንዲሁም ለሚመሩት ሠራዊት ክብር እና ሞገስ በመኾኑ ታላቅ ትርጉም የሚሰጠው ነውም ብለዋል፡፡
የማዕረግ ዕድገት የተሰጠው ከኮሌኔል ወደ ብርጋዴር ጄኔራል፣ ከብርጋዴር ጄኔራል ወደ ሜጀር ጄኔራ፣ ከሜጀር ጄኔራል ወደ ሌተናል ጄኔራል እና ከሌተናል ጄኔራል ወደ ሙሉ ጄኔራልነት ነው፡፡
። ። ።
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ 👇
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV