23/01/2025
#ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ
ዛሬ ጥር 15 ቀን 2017 የትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችን ወክለው በሰጡት መግለጫ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመበተን፣ ስርዓት አልበኝነትን ለማንገስ እና ሰራዊቱን ለመበተን ከተልዕኳቸው ውጪ ከህገወጥ ቡድን ጋር በመሆን በግልፅ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል።
ይህ መግለጫ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የማይታወቅ ሲሆን በማንኛውም መስፈርት ህጋዊም ሆነ ሞራላዊ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። ጊዜያዊ ካቢኔው የሰራዊት አዛዦችን ያልተለመደ ውሳኔ ለማየት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። ሁኔታውን ከተመለከትን በኋላ ለህዝባችን ሰፊ ማብራሪያ እንሰጣለን ብለዋል።
የሰራዊቱን ከፍተኛ አዛዦች በመወከል የወጣው የዚህ ህገ መንግስት ይዘት በግልፅ መፈንቅለ መንግስት በማወጅ የፕሪቶሪያን ስምምነት አደጋ ላይ ጥሏል። መላው ህዝባችንን አደጋ ላይ የጣለ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔም ነው ይህ ወዲያውኑ መቆም አለበት ብለዋል። ይህ ካልሆነ የህዝባችንና የጸጥታ ሃይላችን አንድነት አደጋ ላይ ይወድቃል።
ሁሉም የጸጥታ ሃይሎች ይህንን ህገወጥ ውሳኔ ውድቅ እንዲያደርጉ እና ከዚህ ውጪ የትኛውንም ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዳያደርጉ እናሳስባለን ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው አስታውቋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
መቐለ