EBS SPORT

EBS SPORT We love football forever. It is recreation, entertainment, sport & every thing for us!
እግር ኳስን በፌስቡክ

Final Game On Sunday July 19,  22:00.  Argentina and Spain have reached the final of the 2026 World Cup. Argentina, faci...
15/07/2026

Final Game On Sunday July 19, 22:00.
Argentina and Spain have reached the final of the 2026 World Cup. Argentina, facing England for a spot in the final, was trailing 1–0 until the 85th minute but staged a dramatic comeback, scoring two goals to win 2–1 and advance to the championship match. Having reached the World Cup final for the second consecutive time, Argentina will face Spain—who advanced by defeating France—this coming Sunday night.


FIFA World Cup

  🇦🇷 አርጀንቲና በታሪኳ ለሰባተኛ ጊዜ ለፍፃሜ ባለፈችበት ምሽት ሊዮኔል ሜሲ ሀገሩን ለተከታታይ ጊዜ ለፍፃሜ አብቅቷል። ሊዮኔል ሜሲ በምሽቱ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበሉ የአለም ዋ...
15/07/2026

🇦🇷

አርጀንቲና በታሪኳ ለሰባተኛ ጊዜ ለፍፃሜ ባለፈችበት ምሽት ሊዮኔል ሜሲ ሀገሩን ለተከታታይ ጊዜ ለፍፃሜ አብቅቷል።

ሊዮኔል ሜሲ በምሽቱ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበሉ የአለም ዋንጫ ኮከብ ግብ አግቢነቱን በቀዳሚነት መምራት ጀምሯል።

ሊዮኔል ሜሲ በአለም ዋንጫው ታሪክ በ 3️⃣3️⃣ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን በማድረግ ቀዳሚው ተጫዋች ሆኗል።

ሊዮኔል ሜሲ በአለም ዋንጫው 1️⃣2️⃣ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ሪከርዱን ይዞ አስቀጥሏል።

ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ በ 1️⃣3️⃣3️⃣7️⃣ ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን ማድረግ ችሏል።

ነገ ፍጻሜውን የሚያገኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ:- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዓመት ነገ በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ፍጻሜውን ያገኛል፡፡አንድ ቀሪ ጨዋታ እያ...
23/05/2026

ነገ ፍጻሜውን የሚያገኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ:-

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዓመት ነገ በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ፍጻሜውን ያገኛል፡፡

አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው አርሰናል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

አስቀድሞ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው አርሰናል ወሳኝ ተጫዋቾቹን ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ያሳርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኮንፈረንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ያለበት ተጋጣሚው ክሪስታል ፓላስ በተመሳሳይ ለቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች እረፍት እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

አስቀድሞ የወርቅ ጓንቱን ያሸነፈው ስፔናዊው የአርሰናል ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ በጨዋታው ግቡን ሳያስደፍር ለመውጣት ወደ ሜዳ ይገባል።

ዴቪድ ራያ በጨዋታው ግብ የማይቆጠርበት ከሆነ በአንድ የውድድር ዓመት በሊጉ ለአርሰናል 20 ጨዋታዎች ላይ ግብ ያልተቆጠረበት ቀዳሚው ግብ ጠባቂ ይሆናል፡፡

በወድድር ዓመቱ እስካሁን በሊጉ በ19 ጨዋታዎች ግብ ያልተቆጠረበት ዴቪድ ራያ በክለቡ ታሪክ ከመድፈኞቹ የቀድሞ ግብ ጠባቂ ዳቪድ ሲማን ጋር ክብረወሰኑን መጋራቱ ይታወሳል፡፡

በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ያረጋገጠው ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ አስቶንቪላን ያስተናግዳል፡፡

በማንቼስተር ሲቲ ቤት የመጨረሻ ጨዋታቸውን የሚመሩት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከ10 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከቡድኑ ጋር ይለያያሉ፡፡

ከሁለት ዓመታት በኋላ ወደ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መድረክ የተመለሰው ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከብራይተን ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ያረጋገጠው ማንቼስተር ዩናይትድ ነጥቡን ከፍ ለማድረግ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ብራይተን በበኩሉ የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት የሚያደርገው ፉክክር ተጠባቂ ነው፡፡

በጨዋታው ብሩኖ ፈርናንዴዝ አንድ ለጎል የሚሆን ኳስ አመቻችቶ የሚያቀብል ከሆነ በሊጉ በአንድ የውድድር ዓመት በርካታ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ የማቀበል ክብረ ወሰኑን የግሉ የሚደያርግ ይሆናል፡፡

የውድድር ዓመቱ ሲጀምር ለዋንጫ ቅድመ ግምት ካገኙ ቡድኖች መካከል አንዱ የነበረው እና ደካማ የውድድር ዘመን ያሳለፈው ሊቨርፑል በአንፊልድ ብሬንትፎርድን ያስተናግዳል፡፡

አሰልጣኞችን ቢቀያይርም የውጤት ለውጥ ማምጣት ያልቻለው ቼልሲ ከሰንደርላንድ ጋር ይጫወታል፡፡

ከሻምፒየንስ ሊግ ውጪ የሆነው ቼልሲ የዩሮፓ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት በጨዋታው የሚደያርገው ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡

ከሊጉ የመውረድ ስጋት ያለበት ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው ከኤቨርተን ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር ከነገው ጨዋታ አንድ ነጥብ የሚያገኝ ከሆነ በሊጉ መቆየቱን ያረጋግጣል፡፡

ቶተንሃም ከሊጉ የሚወርድ ከሆነ ደግሞ ከፈረንጆቹ 1977 በኋላ ከእንግሊዝ ዋናው ሊግ የሚወርድ ይሆናል፡፡

ሌላው የመውረድ ስጋት ያለበት ዌስትሃም ዩናይትድ በሊጉ ለመቆየት የራሱን ጨዋታ አሸንፎ የቶተንሃም ሆትስፐርን መሸነፍ ይጠብቃል።

በርንሌይ እና ወልቭስ አስቀድመው ከሊጉ መውረዳቸውን ያረጋገጡ ቡድኖች ሲሆኑ ነገ ሦስተኛው ወራጅ ይታወቃል፡፡

ቼልሲ ከማንቼስተር ዩናይትድበ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ከማንቼስተር ዩናይትድ የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡ሁለቱም ቡድኖች የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ...
18/04/2026

ቼልሲ ከማንቼስተር ዩናይትድ

በ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ከማንቼስተር ዩናይትድ የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

ሁለቱም ቡድኖች የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት የሚያደርጉትን ጉዞ አጠናክረው ለመቀጠል የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

በሊጉ ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች የተሸነፈው ቼልሲ ወደ ድል ለመመለስ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡

በአሰልጣኝ ሊያም ሮሲኒየር ቅጣት ተላልፎበት ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ለቼልሲ ግልጋሎት ያልሰጠው ኢንዞ ፈርናንዴዝ በምሽቱ ጨዋታ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አሰልጣኙ አረጋግጠዋል፡፡

በሊጉ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል ያላደረገው ተጋጣሚው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ድል ለመምጣት የሚያደርገው ፉክክር ተጠባቂ ነው፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ በሊድስ ዩናይትድ በተሸነፈበት ጨዋታ በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጣው የተከላካይ ሥፍራ ተጫዋቹ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በምሽቱ ጨዋታ ለቀያይ ሰይጣኖቹ ግልጋሎት አይሰጥም፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሁለቱም ቡድኖች በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ሲያሸንፉ በቀሪው አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በዚህ የውድድር ዓመት በኦልድትራፎርድ ያደረጉትን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ተጠባቂው ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም መደረግ ይጀምራል፡፡

በሌላ የሊጉ ጨዋታ ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው ብራይተንን ያስተናግዳል፡፡

በ30 ነጥብ ወራጅ ቀጣና 18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቶተንሃም ሆትስፐር በሊጉ ከወራጅ ቀጣናው ለመውጣት የሚደያርገው ብርቱ ፉክክር ይጠበቃል፡፡

በሊጉ ከ19ኛ ሳምንት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ድል ማድረግ የተሳነው ቶተንሃም ሆትስፐር ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ያደረገው ተጋጣሚው ብራይተን በበኩሉ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል ይፋለማል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ብራይተን ሦስቱን ሲያሸንፍ ቶተንሃም ሆትስፐር በአንዱ ድል አድርጎ በቀሪው አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ከእነዚህ ጨዋታዎች አስቀድሞ ቀን 8 ሰዓት 30 ላይ ብሬንትፎርድ ከፉልሃም ሲገናኙ ሊድስ ዩናይትድ ከወልቭስ እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ከቦርንማውዝ በተመሳሳይ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ሊጉን አርሰናል በ70 ነጥብ ሲመራው ማንቼስተር ሲቲ በ64 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ በ55 ነጥብ 3ኛ እንዲሁም አስቶንቪላ በተመሳሳይ 55 ነጥብ በግብ ክፍያ አንሶ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ወራጅ ቀጣናው ላይ ቶተንሃም ሆትስፐር፣ በርንሌይ እና ወልቭስ እንደ ቅድም ተከተላቸው ከ18ኛ እስከ 20ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

የሊጉን ኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ በ22 ግቦች ሲመራ÷ ኢጎር ቲያጎ በ21፣ አንቷን ሴሜኒዮ በ15 እንዲሁም ጇ ፔድሮ በ14 ግቦች ይከተላሉ፡:

01/04/2026

Comedian Yasin

24/03/2026

Rayan cherki Confidence over Arsenal

Arsenal Manchester City
Cherki
ReelShort TV

ማንችስተር ሲቲ ሻምፒዮን 🏆 ሆኗል ! ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነዋል። የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች...
22/03/2026

ማንችስተር ሲቲ ሻምፒዮን 🏆 ሆኗል !

ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነዋል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኦሬሊ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ 9️⃣ ኛ የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ዋንጫቸውን አሸንፈዋል።

መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ በ 1993 ድል ካደረጉ በኃላ የካራባኦ ካፕ ዋንጫ ማሸነፍ አልቻሉም።

ማንችስተር ሲቲ ካደረጋቸው 1️⃣0️⃣ የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታዎች 9️⃣ አሸንፏል።

  አርሰናሎች የካራባኦ ካፕ ዋንጫን ከ 33ዓመታታ በኃላ ለማሸነፍ የሚያደርጉት ፍልምያ መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ በ 1993 ድል ካደረጉ በኃላ ዋንጫውን ለማሸነፍ አልቻሉም። አርሰናሎች በሶስት ...
22/03/2026



አርሰናሎች የካራባኦ ካፕ ዋንጫን ከ 33ዓመታታ በኃላ ለማሸነፍ የሚያደርጉት ፍልምያ

መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ በ 1993 ድል ካደረጉ በኃላ ዋንጫውን ለማሸነፍ አልቻሉም።

አርሰናሎች በሶስት አጋጣሚ ለፍፃሜ መድረስ ቢችሉም ባለፉት አመታት አንዱንም ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

በዚህም ባለፉት ሶስት ፍፃሜዎች :-

እ.ኤ.አ 2007 ዓ.ም :- ቼልሲ 2-1 አርሰናል

እ.ኤ.አ 2011 ዓ.ም :- በርሚንግሀም ሲቲ 2-1 አርሰናል

እ.ኤ.አ 2017 ዓ.ም :- ማንችስተር ሲቲ 3-0 አርሰናል

The quarter-finals are looking crazy!I think Arsenal have chance.
19/03/2026

The quarter-finals are looking crazy!
I think Arsenal have chance.

አርሰናል እና ፒኤስጂ ድል አድርገዋል !በሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ አርሰናል ባየር ሌቨርኩሰንን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።መድፈኞቹን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ኢቤሬ ኢዜ እና ዴ...
17/03/2026

አርሰናል እና ፒኤስጂ ድል አድርገዋል !

በሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ አርሰናል ባየር ሌቨርኩሰንን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

መድፈኞቹን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ኢቤሬ ኢዜ እና ዴክላን ራይስ አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በድምሩ 3ለ1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

በሌላ ጨዋታ ፒኤስጂ ከቼልሲ ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ቅቫራስኬሊያ ፤ ባርኮላ እና ማዩሉ አስቆጥረዋል።

ፒኤስጂ በድምር ውጤት 8ለ2 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።

ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን የመልስ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግብ ቪንሰስ ጁኒየር 2x ሲያስቆጥር ለማንችስተር ሲቲ ሀላንድ ከመረብ አሳርፏል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በድምር ውጤት 5ለ1 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EBS SPORT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share