
01/07/2025
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች ቁጥር 10 ሚሊዬን መድረሱን ገለጸ
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄለፑት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፤ተቋሙ ወደ ስራ በገባ በ4 አመታት ውስጥ 10 ሚሊዬን የሚጠጉ ደንበኞች ማፍራቱን ተናግረዋል፡፡
ይህ ቁጥርም ባለፉት 90 ቀናት የደንበኞች አጠቃቀም ላይ የተመሰረተ መረጃ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ተቋሙ ዲጂታል ኢትዮጰያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ሀላፊነት እየተወጣ መሆኑን በመግለጫው ላይ አንስተዋል፡፡
ተቋሙ ጠንካራ የቴሌኮም እና የዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶች መሰረተ ልማት ላይ ባለፉት 4 አመታት ከ300 ቢሊዬን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አመላክተዋል፡፡
አሁን ላይ የአራተኛው ትውልድ ኔትወርክ በግማሽ በላይ በሚሆን ደንበኞች ተጠቃሚ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን 150 በላይ ከተሞች ይህን የሚያሳልጡ መሰረተ ልማት ግንባታዎች መደረጋቸውን የገለፁት የሳፋሪኮም የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ዶክተር አንዱለም አድማሴ ናቸው፡፡
ተቋሙ በየዕለቱ 31 ሺ ደንበኞችን እያገኘ መሆኑን በመግለፅ በተለይም አሁንም ድረስ የቴሌኮም አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች ደንበኞችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶክተር አንዷለም አክለውም በቀጣይ ሶስት አመታት ደንበኞችን ከ15 እስከ 17 ሚሊዬን ለማድረስ እንደሚሰራ ገልፀዋል፤፤
ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ 900 ሰራተኞች ያሉት ሲሆን 20 ሺ የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ በተዘዋዋሪ የስራ እድል እንዲያገኙ ማድረጉን ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
#መናኸሪያሬዲዮ #መናኸሪያኤፍኤም #ራዲዮ #ሬዲዮ