Adulis podcast

Adulis podcast Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Adulis podcast, Addis Ababa.

ወደ Adulis podcast እንዃን በደህና መጡ🙏

ይህ ገፅ በኪነ -ጥበብ : #በታሪክ : #በሳኮሎጂ : #በፍልስፍና:የተመረጡ ፖስቶች : #ቪድዮዎች የምንጋራበት : የምንማማርበት ገፃችን ነው። , በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
ዛሬ 📖 ለ📖 💪ነገ
t.me/Ama1214dream

08/07/2025

''ትልቅ ስኬት በትንሽ ድካም አይገኝም።''

እስኪጸና ድረስ በሚስጥር ያዘው !  ብዙዎቻችን ነገሮችን ወዲያውኑ የማካፈል ልምድ አለብን። ግን አንዳንድ ጊዜ፣ ዝምታ ወርቅ ነው። በተለይ በሕይወታችን ውስጥ ጉልህ የሆኑ ነገሮችን በተመለከተ...
08/07/2025

እስኪጸና ድረስ በሚስጥር ያዘው !

ብዙዎቻችን ነገሮችን ወዲያውኑ የማካፈል ልምድ አለብን። ግን አንዳንድ ጊዜ፣ ዝምታ ወርቅ ነው። በተለይ በሕይወታችን ውስጥ ጉልህ የሆኑ ነገሮችን በተመለከተ ቶሎ ለሌሎች ባናወራቸው ይመረጣል። የሚከተሉት 10 ነጥቦች ሚስጥሮች መሆን ያለባቸው ናቸው።

1. ዕቅዶችህን ለራስህ አድርግ። ግብህ ውድ ነው፣ ስለዚህ ከሌሎች ተጽዕኖ ጠብቀው። ሁሉም ሰው የአንተን ራዕይ አይረዳም ወይም አይደግፍም። እስክትተገብረው ድረስ ዝም በል።

2. የግል ሕይወትህ የአንተ ብቻ ነው። የዕለት ተዕለት ልማዶችህ እና የግል ጉዳዮችህ ሚስጥራዊ ሲሆኑ ይመረጣል። ግላዊነትህ አስፈላጊ ነው፣ ስለዚህ የአኗኗር ዘይቤህን ዝርዝሮች ለራስህ ብቻ አድርጋቸው።

3. የቤተሰብ ጉዳዮች ሚስጥር ናቸው። የቤተሰብ ትስስር ቅዱስ ትስስር ነው። የቤተሰብህን ጉዳዮች ከሌሎች፣ በተለይም ከማታውቃቸው ሰዎች ጋር ከመወያየት ተቆጠብ።
4. • እኔ እበልጣለሁ ከማለት ተቆጠብ። ትህትና በጎነት ነው። መንፈሳዊም ሆነ ምሁራዊ ብልጫህን ከሌሎች ጋር አታውጅ። ድርጊቶችህ እና እውቀትህ ለራሳቸው ይናገሩ።

5• ስኬቶችህን አታውራ። ድርጊት ከቃል በላይ ይናገራል። ስኬቶችህን ማውራት ሳይሆን ስኬቶችህ ራሳቸው ይናገሩ።

6. ሌሎችን አትተች። አሉታዊ ኃይል ከመፍጠር ተቆጠብ። አዎንታዊ ግንኙነት ቁልፍ ነው፤ ስለዚህ ሌሎችን ከማውረድ ይልቅ በመገንባት ላይ አተኩር።

7. የግል መረጃህን አትግለጥ። ደህንነትህ ይቀድማል። አድራሻህ ወይም ስልክ ቁጥርህ የመሳሰሉ የግል መረጃዎችን ለማታውቃቸው ሰዎች ከመስጠት ተቆጠብ።

8• የፖለቲካ አመለካከትህን በአደባባይ አትወያይ። አመለካከቶች የተለያዩ ናቸው። የፖለቲካ አመለካከትህን ለራስህ በማድረግ ሌሎችን አክብር። አንዳንዴ ዝምታ ይሻላል።

9• የገንዘብ ሁኔታህን አትናገር። ገንዘብ ሚስጥራዊ ጉዳይ ነው። ያልተፈለገ ትኩረትን ለማስወገድ የፋይናንስ መረጃህን በሚስጥር አቆይ።

10. ሐሜትና አሉታዊ ወሬዎችን አታሰራጭ። ደግነት ተላላፊ ነው። የሌሎችን ዝና ሊጎዳ ወይም ስሜታቸውን ሊረብሽ የሚችል አሉታዊ መረጃ ወይም ሐሜት ከማሰራጨት ተቆጠብ። ከአሉታዊነት ይልቅ አዎንታዊነትን አሰራጭ።

አስተሳሰብ የሁሉ መሰረት ነው፤ ሌላው ሁሉ ቅርንጫፍ ነው።

ሀብት፣ ጤና፣ ግንኙነቶች፣ ነጻነት ከአስተሳሰብ በኋላ የሚመጡ ናቸው።
Adulis podcast

07/07/2025

🎯🎯🎯 ዓላማ 🎯🎯🎯

ትርጉም ያለው ኑሮ በመኖር በሥራና ኑሮህ ደስተኛ ለመሆን ከሁሉ አስቀድሞ ለህይወትህ ዓላማ አበጅለት።

ዓላማ ሲኖርህ በየቦታው ለዓላማህ መዳረሻ የሚሆኑ፣ ጉዞህን አቅጣጫ የሚያሲዙ እና ፍጥነትህን ለማስተካከል የሚረዱ ግብ እና ምዕራፎች ይኖሩሃል።

ዓላማ ያለው ህይወት እቅድና ግብ ሊኖሩት ያስፈልጋል። ዓላማ ያለው ህይወት እንዲሳካ ሥራ ይፈልጋል። ዓላማ ያለው ህይወት የሚሳካው በእቅድ ሲሠራ እንጂ የተገኘውን ሁሉ በመሥራት አይደለምና ሥራን አቅደህ ሥራ።

ማቀድ ትልቅ የሃሳብ ውጤት ነው። ሳያቅዱ በዘፈቀደ ህይወትን እንደአመጣጡ የሚኖሩ አሉ። ሳያቅዱ በምኞት የሚኖሩ አሉ። አቅደው የሚኖሩ አሉ። እቅዳቸውን በጽሁፍ አስቀምጠው በዝርዝር እየተከታተሉ የሚኖሩ አሉ። አንተ ከየትኛው ነህ?

አቅደህ፣ እቅድህን በጽሁፍ አስቀምጠህ፣ ዘወትር የእቅድህን አፈጻጸም እየተከታተልህና ማስተካከያ እያደረግህ የምትኖር ከሆነ አንተ ከዓለማችን 20% ሰዎች አንዱ ነህ።

ማደራጀት የሌለበት እቅድ ረጅም እድሜ የለውም። ሥራህን ለጥሩ አፈጻጸም እንዲመች እና ሥራን እንዲያቀላጥፍ አድርገህ አደራጅ። ሥራን በዘርፍ በዘርፍ፣ በክፍል ክፍል አድርጎ ማደራጀት እና ሁኔታው ሲቀየርም እንደገና አፍርሶ ማደራጀት የአዋቂዎች እና የብልሆች ተግባር ነው። ያቀድከውን ሥራ ለማስፈጸም ሥራህን በአግባቡ ማደራጀት እና እንደ ሁኔታው በተለያየ መልኩ የአደረጃጀት ቅያሪ እያደረግህ መምራትን እወቅበት። ሁኔታዎች ባሉበት አይቀጥሉምና ሁኔታ ሲቀየር አደረጃጀትን ወይም ሰውን መቀየር ቻልበት። ሁኔታዎች ቢቀየሩም የማይቀየረው ግቡ እንጂ የግብ መዳረሻ መንገድ እና አደረጃጀት ወይም በቦታው የተቀመጠው ሰው አይደለም።

ግብህን ለማሳካት እንዲያስችል አድርገህ ሥራህን በትክክል አደራጅ። ባደራጀኸው የሥራ መደብ ላይ ትክክለኛ እና ተገቢ ሰዎችን ማስቀመጥ እና ሁኔታዎች ሲቀያየሩም ያለ ይሉኝታ አደረጃጀትህን ወይም ሰዎችን መቀየር ከቻልህ አንተ ከዓለማችን 10% ሰዎች አንዱ ነህ።

ተግባር የእቅድ ነፍስ መዝሪያ ነው። እቅድን ተከትሎ መተግበር ብዙ ሰው ይቸገራል። መሥራት እና እቅድና የአደረጃጀት መስመርን ተከትሎ መሥራት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው። እቅድና የአደረጃጀት መስመርን ተከትለው ዘወትር ሳይታክቱ በግባቸው ነጥብ ላይ አትኩረው የሚሠሩ ሰዎች ጥቂት ናቸው። ሌላው ሲሄድ ሲመለስ፣ ሲጀምር ሲያቋርጥ፣ ከአንዱ ሥራ ወደ ሌላው ሲቀይርና ሲቀያይር እድሜውን የሚፈጅ ነው።

የጀመሩትን ሳይታክቱ ሠርተው ከሚያጠናቅቁት ውስጥ ለመሆን ትኩረት እና መስመርን መጠበቅ፣ ዘወትር ራስን ማነቃቃትና ማበርታት እና የአእምሮ መዛልና በአዳዲስ ምኞት ከመወሰድ እና ለችግር ከመንበርከክ ራስን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። እነዚህ ሰዎች ከዓለማችን 4% ያህል ናቸው። እነዚህ ሰዎች ጎራ ውስጥ ለመገኘት የህይወት ዓላማ፣ ከፍ የለ የግብ እምነት እና ትኩረት፣ የማይናወጥ ዲሲፕሊን እና ብርቱ ጥረት ያስፈልጋል።

የሥራ አቅጣጫን ይዞ መሥራት ብቻውን ለስኬት በቂ አይደለም። አቅጣጫ የሌለው ፍጥነት ከመርበትበትና ትርጉም ከሌለው ዙረት ውስጥ የሚመደብ ነው። አቅጣጫውን ሳታውቅ አትፍጠን። ስትፈጥን በትክክለኛው መስመር ውስጥ ፍጠን። ያለመስመርህ ከምትፈጥን በትክክለኛው መስመር ውስጥ ቀስ ብለህ ብትጓዝ ይሻላል። ሆኖም በትክክለኛው መስመር ውስጥ ቀስ ብሎ መጓዝ ብቻውን በቂ አይደለም። ሁኔታው ተቀይሮ መንገዱ በዝናብ በረዶና ጎርፍ እንዲሁም ናዳ ከመዘጋጋቱ በፊት ፈጥነህ ገና ጠዋት ሳለ በረሃውን አቋርጥ። ትክክለኛ መስመር ውስጥ ከሆንክ ምን ያዘገይሃል? በትኩረት ወደፊት ገስግስ። በትክክለኛ መስመር ውስጥ ከሆንክ ወለም ዘለም ሳትል የጉዞህን ፍጥነት እየለካህ በትክክለኛው ፍጥነት ወደፊት ገስግስ። ዘግይተህ ከሆነ ፍጥነትህን ጨምር። እንዲህ ያሉ የጉዟቸውን ትክክለኛ አቅጣጫ ይዘው ፍጥነታቸውን እየለኩና እያስተካከሉ በግባቸው ላይ አትኩረው የሚጓዙ ሰዎች እጅግ ጥቂት ናቸው። እነዚህ 1% ናቸው። አንተ ከእነዚህ 1% ሰዎች ውስጥ ነህ?

ዋረን በፌትን ተመልከት! ዳላይ ላማን ተመልከት! ቢኒያም በለጠን ተመልከት!

እነዚህ 1% ሰዎች ህይወታቸውን ያለ ግርግር እና ጭንቀት የሚመሩ ናቸው።

እነዚህ ሰዎች ግባቸው አንድ ነው። ትኩረታቸውም ግባቸው ላይ ነው።

አትበታተን!

07/07/2025

በየቀኑ አንድ ማይል በእግር መጓዝ የተረጋገጡ የጤና ጥቅሞች፡-

1. የደም የስኳር መጠን ለመቀነስ ይረዳል

2. የደም ግፊት መጠንን ለመቀነስ ያግዛል

3. መጥፎ የሰዉነት ስቦችን ለመቀነስ ይረዳል

4. ሰዉነታችንን ከ1000 በላይ የካሎሪ መጠንን ለማቃጠል ይረዳል

5. የጡትንና የትልቁ አንጀት ለካንሰር ህመም ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል

6. የአይን ግፊት መጠን(ግላኮማ)ን ለመቀነስ ይረዳል

7. በስትሮክ ምክንያት የሚከሰትን የሞት መጠን ለመቀነስ ይረዳል

8. የልብ ህመም ተጋላጭነትን ይቀንሳል

9. ጭንቀትን ይቀንሳል

10. ድብርትን ያቀላል

11. የትኩረት ችግር ባላቸዉ ልጆች ላይ ትኩረትን በማሻሻል የፈጠራ ችሎታቸዉን ለማሳደግ እንዲሁም በራስ የመተማመን አቅማቸዉን ለማዳበር ይረዳል፡፡

12. ስር በሰደደ የመተንፈሻ አካል ችግሮች ምክንያት በተደጋጋሚ ሆስፒታል የመተኛት እድልን ይቀንሳል።

05/07/2025

👉ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምቀው ዘውትር ቢጠጡ እነዚህን 10 የጤና ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡
1. ጉበቶን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳሉ፡፡ለብ ባለ ውሃ ውስጥ የሎሚውን ጭማቂ (ፈሳሽ) ብቻ ሳይሆን የሎሚው ልጣጭ ጭምር ከተን የምንጠጣ ከሆነ ደረጃ 2 የጉበት ፀረ- መርዝ ማስወገድ ተግባራን ያከናውናል፡፡
2. ጉበቶ ሐሞት እንዲያመነጭ በማበረታታት ቅባታማ ምግቦችን ሰውነቶ እንዲፈጭ ይረዳል፡፡
3. ሎሚ ከፍተኛ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ ስላለው ሕዋሳታችን(cells) እንዳይወድሙ ይጠብቃቸዋል፡፡
4. በሎሚ ውስጥ ያለው አንቲ- ኦክሲደንት እና ፌቶኬሚካልስ የጉበት ሕዋሳት እንዲታደሱ ይረዳል፡፡
5. በሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የምግብ ስርዓተ ልመትን ያፋጥናል እንዲሁም የኩላሊት ጠጠርን (kidney stone) ያሟሟል፡፡
6. ሎሚ ከሰውነት ውጭ አሲድ ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ አልካላይን ነው ስለሆነም በሰውነት ውሰጥ ያለውን የፒ ኤች ደረጃ ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳል በተጨማሪም በሽታን ይከላከላል፡፡
7. በሎሚ ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ጠንካራ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከል አቅም እንዲኖረን ያስችላል፡፡
8. ሎሚ የደም ቅባትን በመሰባበር በዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን የሀሞት ድንጋይዎች(gall stones) በሰውነታችን ውስጥ እንዳይፈጥር ያግዛል፡፡
9. ሎሚ ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ስላላው የዩሪክ አሲድ መጠንን በመቀነስ ሰዎች በሪህ (Gout) እና የአጥንት አንጓ
10. ብግነት (Arthritis) እንዳይጠቁ ይጠብቃቸዋል፡፡

11. ሎሚ ከአንደንድ የካንስር በሽታዎችም ይከላከላል፡፡
Adulis podcast

04/07/2025

📖📖📖 ህይወትና እውነት🔔🔔🔔

1. ‹‹የዘጠኝ ወር እርጉዝ በማግባት በአንድ ወር የራስህን ልጅ ልትወልድ አትችልም››

2. ‹‹ዛሬ ዛፍ ጥላ ስር የምንቀመጠው የሆነ ጊዜ ላይ የሆነ ሰው ዛፉን ስለተከለው ነው፡፡››

3. ‹‹ዝናህን ለመገንባት ሃያ ዓመት ይወስድብሃል፡፡ ዝናህን ለማበላሸት ግን ሃያ ደቂቃ በቂህ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ካሰብክ ነገሮችን በተለያየ መንገድ ታከናውናቸዋለህ፡፡››

4. ‹‹ባልገባህ ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት አታድርግ››

5. ‹‹ስጋት ወይም ፈተና የሚመጣው የምትሰራውን ባለማወቅ ነው፡፡››

6. ‹‹በአንድ ገቢ ብቻ ጥገኛ አትሁን፡፡ ሁለተኛ የገቢ ምንጭ ፍጠር››

7. ‹‹በአሜሪካ ቢዝነስ ቁጭ ብሎ ማሰብ ያልተለመደ ነው፡፡ እኔ ግን ብዙ ጊዚዬን የማጠፋው ቁጭ ብዬ በማሰብ ነው፡፡

8. ‹‹በጣም አስፈላጊው ኢንቨስትመንት በራስህ ላይ የምታደርገው ነው፡፡››

9. ‹‹የማትፈልገውን የምትገዛ ከሆነ የምትፈልገውን ወዲያው ትሸጣለህ፡፡››

10. ‹‹ከመጥፎ ሰው ጋር ጥሩ ውል ማሰር አትችልም፡፡

11. ‹‹ደስተኛ ሰዎች የሚደሰቱት ምርጥ ነገር ስላላቸው አይደለም፡፡ እነሱ የሚደሰቱት ያላቸውን ነገር አክብረውና ወደው ስለያዙ ነው፡፡

12. ‹‹በመኝታህ ሰዓት ገንዘብ ለማግኘት አስበህ አዲስ መላ ካልፈጠርክ እስክትሞት ትሰራለህ፡፡

13. ‹‹አጥፍተህ የቀረህን አትቆጥብ፡፡ ከቁጠባ በኋላ የተረፈህን አጥፋ፡፡››

14. ‹‹ብዝሃነት ወይም ሁለገብ ዕውቀት ከመሐይምነት ይከላከላል፡፡

15. ‹‹ታማኝነት በጣም ውዱ ስጦታ ነው፡፡ ይሄን ስጦታ ከርካሽ ሰዎች አትጠብቅ፡፡››

16. ‹‹ያልተለመደ ከሆነ ሰዎች ብዙ ጊዜ ትክክለኛውን ነገር ከመስራት ሊያስቆሙህ ይሞክራሉ፡፡

17. ‹‹በዓለም ላይ ሐይል ያለው ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር ነው፡፡

18. ‹‹ሁልጊዜም ሐብት ማግኛ ምርጡ መንገድ ለራስህ ዋጋ መስጠት ነው፡፡

19. ‹‹አነባለሁ፣ አነባለሁ፣ አነባለሁ! በቀን ውስጥ ከአምስት እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ አነባለሁ፡፡››

20. ‹‹ብዙ በተማርክ ቁጥር ብዙ ታገኛለህ። ››

ብዙ ለመማር ዝግጁ ከሆናችሁ አስተማሪ ሃሳቦች የምናጋራባቸውን የማህበራዊ ገፆቻችንን በመከተል ቤተሰብ ሁኑ። ታተርፋላችሁ:-

facebook 👉 Adulis podcast
------------------------
የትኞቹን አባባሎች ወደዳችኋቸው? አድርጉልን

አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ ማድረግን አትርሱ 🙏

🕕        🔔       🗝         🚶‍♂️     🏃‍♀️   ✈️
04/07/2025

🕕 🔔 🗝 🚶‍♂️ 🏃‍♀️ ✈️

04/07/2025

💪📖የስኬት መርሆች ✊📖

1. ተስፋ አድራጊ መሆን ረጅም ርቀት ይዞህ ይሄዳል፡፡

በጣም አስከፊ በሆኑ ጊዜያት እንኳ ተስፋ ባለመቁረጥ ችግሮችን መጋፈጥና ለመቀየር መቁረጥ የመፍትሄ መላ እንዲመጣልን ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ፣ ጨለምተኛ አትሁን፡፡

2. መርህ፣ አቋም፣ ያመንክበት ጉዳይ ይኑርህ ነገር ግን ለመስተካከል ቦታ ይኑርህ፡፡

በደረስክበት እውቀት መሰረት በነገሮች ላይ አቋም ሊኖርህ ይገባል፡፡ ነገር ግን የህይወት ዘመን ሁሉ ተማሪ ከሆንክ በአንድ ወቅት የያዝከው አቋም ትክክል እንዳልሆነ ስትረዳ ያመንክበትን ጉዳይ ማስተካከል ይኖርብሃል፡፡

3. አዋዋልህን እና ጓደኞችህን ምረጥ፡፡

አስተሳሰብህን እና ድርጊትህን በገንቢ ጎን ከሚተቹና ከሚገነቡ ሰዎች ጋር የምታደርግ ከሆነ በየጊዜው እየተሻሻልክ የምትሄድ ሰው ትሆናለህ፡፡ ባህሪህ እና ህይወትህ እያደር የሚመስለው የጓደኞችህን ነው፡፡

4. መሆን የምትፈልገውንና መስራት የምትፈልገውን በጊዜ አውቀህ ጀምር፡፡

በወጣትነት ጀምረህ መርጠህ የምትሄበት መንገድ እያደር አንተንም እየቀረፀህ ስለሚሄድ በዛው የመቀጠል እድል ይጨምርልሃል፣ አይቻልም ለሚሉህ በቀላሉ ላትሸነፍ ትችላለህ፣ በእድሜህ ብዙ ሳትገፋ ስኬታማ እና ብዙ ተፅእኖ አምጪ ትሆናለህ፡፡ የራስህን ራእይ የማትገነባ ከሆነ ሌሎች ቀጥረውህ ራእያቸውን እንድትገነባላቸው ያደርጉሃል፡፡

5. ከሌሎች ጎበዞች ጋር በጥምረት ስራ፡፡

ከጎበዞች ጋር በጥምረት ስትሰራ አንተ የማታውቃቸውን ነገሮች ያሳውቁሃል፣ አንተ ልታገኛቸው የማትችላቸውን ሰዎች እንድታገኝ እድል ይከፍቱልሃል፣ ይበልጥ ወደፊት ያራምዱሃል፡፡

6. በቅፅበት ከፍተኛ ደረጃ እደርሳለሁ አትበል፡፡

ከትምህርት ቤት አንደወጣህ ወዲያው ሃብታም፣ ባለስልጣን፣ ወይም ስኬታማ እሆናለሁ ብለህ አትጠብቅ፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ቢኖርህ እንኳ ስኬታማ ለመሆን ብዙ ልምድ ያስፈልግሃል፡፡

7. ስለ ስህተቶችህ ሌሎችን ሳይሆን ራስህን ውቀስ ተማርባቸው፡፡

ስህተቶች እንድንቆጭባቸው ሳይሆን እንድንማርባቸው ካደረግን ደግመን አንሰራቸውም፡፡

8. በተቀጣጠለ መንፈስና መሰጠት ስራ፡፡

መርጠህ ወይም ፈልገህ የምትሰራውን ስራ በከፍተኛ ትጋት፣ መሰጠት፣ መቀጣጠል የምታደርግ ከሆነ ስራ አስደሳችና ቀላል ይሆንልሃል፡፡ የምትሰራው ስራ ውስጥ እነዚህ ነገሮች ከጠፉ ወይም የምትሰራው የሚሰለችህ ከሆነ የምትሰራው ነገር የውስጥ ፍላጎትህን ማንፀባረቁ አጠራጣሪ ነው፡፡

9. ምርጡ ትምህርት ቤት ኮሌጅ ሳይሆን ህይወት ነው፡፡

ምንም ያህል መፅሀፎች ብታነብ፣ ፈተናዎችን ብትወስድና ብታልፍ፣ በህይወት ሂደት የምትማረውን ያህል ብቁ አያደርጉህም፡፡ ስራዎች እና የስራ ሃላፊዎች ያስተምሩሃል፣ ያበቁሃል፡፡

10. እውነተኛ ኑሮና ህይወት በቴሌቪዥን እንደምታየው አይደለም፡፡

ኑሮ ቲቪ ላይ ስታይ እንዳለው ካፌዎች ሄዶ ዘና ማለት ከመሰለህ ተሳስተሃል፡፡ ስራ ሰርተህ ኑሮህን ህይወትህን ለመለወጥ ተንቀሳቀስ፡፡

11. ህይወት ሁሌም የቀና አይደለም፡፡

በህይወት ጉዞህ ትገጫለህ ትወድቃለህ፡፡ ኑሮ ፈተና ነው፣ ጌም መሳይ ነው፣ ተነስተህ እስኪሳካልህ ጉዞህን ቀጥል፡፡

12. የራስ ስራ መስራት ድፍረትና ብከስርም እሰራለሁ ማለትን ይጠይቃል፡፡

ቢዝነስ በአንድ ጎኑ አንደ ቁማር ነው፡፡ 100% ማሸነፍ መቻልህን ቀድመህ እርግጠኛ መሆን አትችልም፡፡ ከቁማር የሚለየው ግን ማጥናት፣ ማቀድና፣ ሁኔታዎችን እያየህና እየቀያያርክ በጥንቃቄ መተግበር መቻልህ ነው፡፡

13. ለስኬታማነት ትእግስት እና ጠንክሮ መስራት ያስፈልግሃል፡፡ በአቋራጭ የሚመጣ ዘላቂ ስኬት የለም፡፡

14. ለራስህ ክብር ይኑርህ፣ በማንነትህ ኩራ፡፡

እያንዳንዳችን የተለያየን ስለሆንን ራስህን ከሌላው ጋር እያወዳደርክ ዝቅተኝነት አይሰማህ፡፡ በሌላው ውስጥ የሌለ አንተ ውስጥ ያለ ችሎታ ስላለ ፈልገህ አግኘው፣ ተቀበለው፣ እዛ ላይ አተኩር፣ አዳብረው፣ በራስህ ተማመን፡፡ ስኬታማ የምትሆነው በዚህ መንገድ ነው፡፡

15. ራስህን አታሳብጥ፡፡

ስኬታማና ታላቅ የመሆን ራእይ መሰነቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ላይ ብትወጣ ነገ ደግሞ ታች መውረድ ሊገጥምህ ይችላል፡፡ ላይ መውጣትህ የብዙ ነገሮች ጥምር ውጤት ስለሆነ ራስህን አይነኬና ልዩ ፍጡር አድርገህ አታስብ፡፡

16. ነገሮችን በቀና በመውሰድ ተማር፡፡

በስራህ ያልተደሰቱብህ ደንበኞችና ትችቶቻቸው፣ ስህተቶችህ፣ ውድቀቶችህ ታላቅ የመማሪያ መሳሪዎች ናቸው፡፡ ከነዚህ የሚመጣውን አስተያየትና ትችት አጣመህ አትመልከት፣ ተማርባቸው፣ ራስህን ለውጥባቸው፡፡

17. በአለም ስላለው ከፍተኛ ድህነት፣ የሃብት ልዩነት፣ ችግር አስብ፡፡

ቴክኖሎጂና ሃብት እየተስፋፋ በሄደ መጠን አለም ከቀድሞ ይልቅ የተሻለች ቦታ እየሆነች ነው፡፡ ነገር ግን ብዙዎች የሚኖሩት አስከፊ ድህነት፣ በሽታ፣ ወዘተ ደግሞ ሊቀየር የሚገባው እና የሚችል መሆኑን አስብበት፡፡

18. ስኬትህን አካፍል፡፡

አንተ ከፊትህ ከነበሩት ስኬታማ ሰዎች ታሪክና ፍሬአቸው እንደ ተነቃቃህ፣ እንደተማርክ እና እንደተጠቀምክ ሁሉ አንተም የስኬትህን ምክንያቶች እና ውጤቶች ለሌሎች አካፍል፡፡ መሪነት ሌሎችን ለስኬት ማብቃት ነው፡፡

19. አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኤነርጂ፣ እና ባዮ ሳይንስ ጥሩ የትምህርት ዘርፎች ስለሆኑ እነዚህን ተማሩ፡፡

እነዚህ የትምህርት ዘርፎች ወደፊት ከፍተኛ ተፅእኖ የሚፈጠርባቸው ናቸው፡፡

20. ደሃ ሆነህ ተወልደህ ከሆነ ጥፋቱ የአንተ አይደለም፤ ደሃ ሆነህ ልትሞት ከሆነ ግን ጥፋቱ የአንተ ነው፡፡

የትኞቹን ምክሮች ወደዳችኋቸው? አድርጉልን።

ምክሮቹን አስተማሪ ሆነው ካገኛችሁኋቸው ሌሎችም ደርሷቸው ይማሩባቸው ዘንድ እያደረጋችሁ 🙏

Adulis podcast

04/07/2025

1. ኃላፊነት ውሰዱ (Be Proactive)

ጅብ ከሄደ በኋላ የውሻ መጮህ ምንም ውጤት አያመጣም፤ ትርፉ ድካም ነው፡፡ ውጤት የሚያመጣው ጅቡ ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ በማነፍነፍ ድምጽ ማሰማት ነው፡፡ ሁኔታዎችን፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ዓለምን ወዘተ የሚወቅሱ ሰዎች በህይወታቸው የረባ ቁም ነገር አያከናውኑም፤ ሁልጊዜም ኃላፊነትን የሚያሸክሙት ከእነሱ ውጪ ላለ ሌላ አካል ነው፡፡ ኃላፊነትን መሸከም ስንችል ነው የህይወታችንን ጉዞ አቅጣጫ መወሰን የምንችለው፡፡

የተሸከርካሪውን መሪ ለሌላ አካል አሳልፈን ሰጥተን የምፈልገው ቦታ አይደለም የደረስኩት፤ በፈለኩት ፍጥነት አይደለም እየተጓዝኩ ያለሁት ወዘተ ልንል አንችልም፤ ብንልም ዋጋ የለውም፡፡ የጉዞውን አቅጣጫ፣ ፍጥነት እና አድራሻ የሚወስነው አሽከርካሪው ነው፡፡

ልምዳችን መውቀስ፣ ጣት መጠቆም፣ ራስን መከላከል ወዘተ ከሆነ እውነቱን ለመናገር የሚወቀስ ነገር ማግኘት አይከብድም፡፡ ዘወትር የእናቴ መቀነት አደናቅፎኝ ነው ማለት ህይወታችን ባለህበት እርገጥ እንዲሆን በር ወለል አድርጎ ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ለውጥ ለማምጣት፣ የራሳችን ሰዎች ለመሆን፣ ውስጣችንን ድል ለማድረግ ወዘተ ሁልጊዜም ለገዛ ራሳችን ህይወት ሙሉ ኃላፊነት እንውሰድ፡፡ ቃላችንን የምናከብር፤ በአልንበት ቦታ የምንገኝ፤ በገዛ ራሳችን ጥረት የምንፈልገውን ማንኛውንም ዓይነት ነገር እጃችን ለማስገባት መጓዝ ያለብንን ያህል ርቀት መጓዝ የምንችል ሰዎች እንሁን፡፡

“ስራ እኮ ጠፋ! እኔ ምን ላድርግ?!” ከማለታችን በፊት ስራ ለማግኘት የምንችለውን ድንጋይ በሙሉ መፈንቀላችንን እርግጠኛ እንሁን፤ ቀጣሪዎች የሚፈልጉትን ዕውቀት እና ክህሎት ይዘን ለመገኘት ጥረት እናድርግ፤ የተለመደውንም ያልተለመደውንም አማራጭ እንፈትሽ፡፡ ሳይኮሎጂስቶች “Life is 10 % what happens to us and 90 % how we react to it” ይላሉ፡፡ የህይወታችንን አብዛኛውን (90 %) ክፍል በምንፈልገው መልኩ መስራት እንችላለን ማለት ነው፡፡ የምናጭደው የዘራነውን ነው፡፡

2. የምትፈልጉትን ነገር አስቀድማችሁ እወቁ (Begin with the End in Mind)

ስቴቨን ኮቬይ “ነገሮች ሁለት ጊዜ ይፈጠራሉ” ይላል፡፡ የመጀመሪያው ፈጠራ የሚጠናቀቀው አእምሮአችን ውስጥ ነው፡፡ ከቤት ከመውጣታችን በፊት የምንሄድበትን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ከአንድ እና ሁለት፣ አምስት እና አስር ዓመት ወዘተ በኋላ ምንድን ነው ማግኘት፣ ማድረግ፣ መሆን ወዘተ የምንፈልገው?

ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ መስጠት ነገሮቹ በተጨባጭም ወደ ህይወታችን የሚመጡበትን ዕድል ከፍ ያደርጋል፡፡ “We rise to the level of our expectations” ይባላል፡፡ የምናገኘው የምናስበውን ነው፤ የምንደርሰው እንደርሳለን ብለን የምናስበው ከፍታ ድረስ ነው፡፡ ግባችንን ማወቃችን ትኩረታችንን ለመሰብሰብ ይረዳናል፤ ከነፈሰው ጋር አንነፍስም፤ በፈተና መካከል ጸንተን እንቆማለን፡፡

ሳይኮሎጂስቶች የህይወታችንን ግብ በቅጡ ለመለየት የሚረዳን አንዱ ሁነኛ መንገድ “የቀብራችን ዕለት እንዲነበብ የምንፈልገውን የህይወት ታሪካችንን መወሰን ነው” ይላሉ፡፡ ቁጭ ብለን ልናስብበት ይገባል፡፡

3. ቅድሚያ ለሚገባቸው ነገሮች ቅድሚያ ስጡ (Put First Things First)

“ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት” ይባላል፡፡ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገሮች ቅድሚያ መስጠት አለብን፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም፡፡ ኮቬይ እንዲህ ይላል፡- “ራሳችሁን ከእነዚህ ሶስት አጉል ልምዶች በአንዱ መውቀስ ቢኖርባችሁ በየትኛው ነው የምትወቅሱት? (1) መስራት ያለብኝን ነገር በቅደም ተከተል መለየት አልችልም፤ (2) በአስቀመጥኩት ቅደም ተከተል መሰረት መስራት አልችልም፤ (3) በወሰንኩት ቅደም ተከተል መሰረት ለመስራት አስፈላጊው ቁርጠኝነት የለኝም፡፡

ብዙ ሰዎች ቁርጠኝነቱ የለኝም ነው የሚሉት፡፡ ጠለቅ ብለን ከመረመርነው ግን እውነቱ ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እውነቱ ቅደም ተከተሉ ውስጣችን በጥልቀት አለመስረጹ ነው፡፡ ልምድ 2ን ማለትም የህይወት ግባችንን አስቀድመን በሚገባ ለይተን በሚገባ ውስጣችንን መቅረጽ አለመቻላችን ነው”::

4. በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ ተመሩ (Think Win-Win)

ከተቃራኒ ፆታ ጀምሮ እስከ የንግድ ስራ ግንኙነት ድረስ በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ መመራት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ “አዎ! በሚገባ አምንበታለሁ፡፡ በእኩል ተጠቃሚነት መርህ ነው ህይወቴን የምመራው፡፡” ትሉ ይሆናል፡፡ እንደምትሉት እንደምትኖሩ ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ለማሸነፍ ከመጣር ይልቅ እንዴት በጋራ እኩል ተጠቃሚ ለመሆን ጥረት አድርጉ፡፡

የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ከሌላው ከፍ ብሎ ለመታየት፣ ልክ ሆኖ ለመገኘት ወዘተ ከመጨነቅ ይልቅ በጋራ እኩል እንዴት ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ማሰብ እና ይህንን መርህ በየትኛውም የግንኙነታችን መረብ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ይበልጥ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

5. መጀመሪያ ለመረዳት ጥረት አድርጉ (Seek First to Understand then to Be Understood)

መጀመሪያ ስንረዳ የሚረዱንን እናገኛለን፡፡ ብዙ ጊዜ ግን በአንጻሩ ጊዜያችንን የምናጠፋው ሰዎች እንዲረዱን በመፍጨርጨር ነው፡፡ ቆም ብለን “ምንድነው እስኪ እያሉ ያሉት? ልክ ይሆኑ ይሆን? በየትኛው ማዕዘን ነው እነሱ ጉዳዩን ያዩት?” ወዘተ ብሎ በቀናነት ማሰብ እና ሰዎችን ለመረዳት ጥረት ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ሰዎችን የመረዳት ችሎታችን ጥሩ ሲሆን የሚረዱንን ሰዎች ቁጥርም ይጨምራል፡፡

6. ቅንጅት፦ 1 + 1 = 3 (Synergy)
“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ትልቅ መልዕክት ያለው አባባል ነው፡፡ በጋራ የሚሰሩ ስራዎች በግል ከሚሰሩ ስራዎች ይልቅ የላቀ ውጤት ያመጣሉ፡፡ አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብም፡፡ ሩጫን በመሰለ የግል ጥረትን በከፍተኛ ሁኔታ በሚጠይቅ የውድድር ዘርፍ እንኳን አትሌቶቻችን ሲተባበሩ የሚያስመዘግቡትን አንጸባራቂ ድል እናውቀዋለን፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ በጋራ የመስራትን መንፈስ ማዳበር ጠንካራ ያደርጋል፤ የበዛ ፍሬም ያፈራል፡፡ አብረን መብላት ብቻ ሳይሆን አብረን መስራትንም ባህላችን እናድርግ፡፡ ስቴቨን ኮቬይ እንደሚለው “አንድ ሲደመር አንድ ከሁለት በላይ ነው”፡፡

7. መጋዛችሁን ሳሉ (Sharpen the Saw)

ስቴቨን ኮቬይ መጽሐፉ ውስጥ ግሩም አፈ ታሪክ አለ፡፡ አንድ ተጓዥ መንገደኛ በአንድ ጫካ ውስጥ አቋርጦ ሲያልፍ አንድ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ላቡ ጠፍ እስከሚል ድረስ ያለምንም እረፍት እንጨት ሲቆርጥ ይመለከታል፡፡ ተጓዡ መንገደኛ ቆም ይልና የመጋዙን መደነዝ አስተውሎ ኑሮ “ወዳጄ! ለምን መጋዝህን ዕረፍት ወስድህ አትስለውም?” ይለዋል፡፡ ልፋ ያለው እንጨት ቆራጭ “አይ ለሱ እንኳን ጊዜ የለኝም” የሚል የዋህ ምላሽ ይሰጠዋል፡፡ ይኼ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ዕረፍት ወስዶ መጋዙን ቢስል በተሻለ ቅልጥፍና ብዙ እንጨት መቁረጥ እንደሚችል አልተረዳም፡፡

የተራ ቁጥር ሰባት ልምድ መልዕክት ቀላል እና ግልጽ ነው፡፡ በቂ ዕረፍት ምንጊዜም አድርጉ ነው፡፡ ከስራ በኋላ ራሳችሁን ዘና የማድረግ ልምምዱ ይኑራችሁ፡፡ መዝናናት ለጊዜው ከሚሰጠው ደስታ ባሻገር ለቀጣይ ስራ ያዘጋጃል፡፡ ሁልጊዜም እንደምለው ትልልቅ ኩባንያዎች ወጪ ችለው፣ ወርሃዊ ደሞዝ መክፈላቸውን ሳያቋርጡ ሰራተኞቻቸውን የሚያዝናኑት በጣም ቸር ስለሆኑ አይደለም፡፡ ይልቁንም የተዝናና ሰራተኛ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚሆን እና እነሱንም ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡

አንድ አንድ ሰዎች “እኔ መዝናናት አይሆንልኝም” ይላሉ፡፡ “መዝናናት ራሱን የቻለ ችሎታ ነው” ይላል አንድ ሌላ ወዳጄም፡፡ በመሆኑም “እንዴት እንዝናና?” የሚል ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች እነዚህን የመዝናኛ አማራጮች እንድትፈትlቸው እጋብዛለሁ፡- ዋና ዋኙ፤ ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር አስደሳች ጊዜ አሳልፉ፤ ዮጋ ስሩ፤ ዳንስ ደንሱ፤ ከከተማ ከተቻለም ከሀገርም ወጣ ብላችሁ ጎብኙ፤ ደስታ ይሰጠኛል ብላችሁ የምታስቡትን የትርፍ ጊዜ የመዝናኛ አማራጭን (Hobby) ሞክሩ፡፡

03/07/2025

🌀24ቱ የምንጊዜም የህይወት ህጎች🌀
Adulis podcast / ✅ከመናገርህ በፊት→አስብ፣

✅ከመፈረምህ በፊት→አንብብ፣

✅ከማስተማርህ በፊት→ተማር፣

✅ከመምከርህ በፊት→ተግብር፣

✅ከመቁረጥህ በፊት→ለካ፣

✅ከማጉደልህ በፊት→ተካ፣

✅ከመዋጥህ በፊት→አላምጥ፣

✅ከመገንዘብህ በፊት→አድምጥ፣

🌀ከማመንህ በፊት→አረጋግጥ፣

🌀ከመረከብህ በፊት→ቁጠር፣

🌀ከመወሰንህ በፊት→መርምር፣

🌀ከመስራትህ በፊት→አቅድ፣

🌀በትጋት ሳይሆን በብልሃት ስራ፣

🌀ከመተኮስህ በፊት→አልም፣

🌀ከመተቸትህ በፊት→አጣራ፣

🌀ከመብላትህ በፊት→ስራ፣

✴ከመሞትህ በፊት→ነሰሃ ግባ፣

✴ከመሄድህ በፊት→ተስፋ ሰንቅ፣

✴ስትወያይ→ሁን አስተዋይ፣

✴ስትናደድ→ቶሎ ብረድ፣

✴ስትናገር→በቁምነገር፣

✴ስትቸገር→መላ ፍጠር፣

✴ስትቀመጥ→ቦታ ምረጥ፣

✴ስትወስን→ቆራጥ ሁን!!

#ከወደዱት ሼር ያድርጉት

ወንዶች በጣም እስኪዘገይ ድረስ ችላ የሚሏቸው 13ቱ የወደፊት እጣ ፈንታን ገዳዮች፤  fans ይህ የማታውቁት ንፁህ እውነት ነው። መንደሬዎችንና አሉባተኞችን እርሳ — ራስህን እየጎዳህ ነው። ...
03/07/2025

ወንዶች በጣም እስኪዘገይ ድረስ ችላ የሚሏቸው 13ቱ የወደፊት እጣ ፈንታን ገዳዮች፤ fans

ይህ የማታውቁት ንፁህ እውነት ነው። መንደሬዎችንና አሉባተኞችን እርሳ — ራስህን እየጎዳህ ነው።

ይህንን ብቻ በደንብ ተገንዘብ፦

1️⃣ ሴቶች፣ ሴቶች፣ እና አሁንም ሴቶች። አዎ፣ ለትኩረት ሶስት ጊዜ ተጠቅሷል። አብዛኞቹ ወንዶች ባዶ ደስታዎችን በማሳደድ ህይወታቸውን ያበላሻሉ። ትንሽ ገቢህን የማያከብሩህ ሴቶች ላይ ታጠፋለህ። ለአንተ ለማይጨነቁልህ ሰዎች ስትል ጊዜህን፣ ጉልበትህን እና ሰላምህን ትሰዋለህ። ብዙ ሴቶች በማወቅህ የዋንጫ ሽልማት የለም — የማይታዩ ጠባሳዎችና የባከኑ ዓመታት ብቻ ናቸው የሚኖሩህ።

2️⃣ ቁማር — የእጣ ፈንታ ካንሰር። አስደሳች ይመስልሃል? “አንድ ተጨማሪ ውርርድ” ሁሉንም ነገር ሊያስከፍልህ ይችላል። ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ሰላምህንና ስምህን። እመነኝ በዕድል አታሸንፍም — በክህሎት፣ በዲሲፕሊን እና በስራ ነው የምታሸንፈው።

3️⃣ አልኮል — የሰከረ ሰው እጣ ፈንታ ይዘገያል። ከምታጠራቅመው በላይ ትጠጣለህ። እኩዮችህ ንብረት ሲወርሱ አንተ የሃንጎቨር (የስካር ድካም) ትወርሳለህ። ደሞዙን በባር (ቡና ቤት) የሚያጠፋ ሰው ለልጆቹ ሀፍረትን ያወርሳል።

4️⃣ ጊዜ ማባከን — ቀስ ብሎ የሚገድል ገዳይ። አንተ ስትዞር፣ ስታወራ፣ ስለ እግር ኳስ ስትከራከር ሌሎች ወንዶች ብዙ ነገሮችን ይገነባሉ። ጊዜ ገንዘብ ነው። ጊዜህን አባክን ህይወት ታባክንሃለች።

5️⃣ ማጭበርበር (በአቋራጭ መክበር) — ፈጣን ገንዘብ፣ ፈጣን መከራ። ዛሬ ልትኩራራ ትችላለህ ግን ከውስጥ ትበሰብሳለህ። ፈጣን ገንዘብ ውድ ነው — ሰላምህን፣ የወደፊትህን እና ነፍስህን ያስከፍላል። አቋራጭ ሁሌም መንገድ ሳይሆን ራስን የማጥፋት ማስታወሻ ነው።

6️⃣ ማጨስና አደንዛዥ ዕፆች — ሱስ የሚያሲዝ ቀስ በቀስ ሞትን የሚጠራ። ጋንጃ፣ ክኒኖች፣ ኮኬይን። እንደ መዝናኛ ይጀምራል — በመንፈስ ጭንቀት፣ ስራ ማጣት እና ከባድ ድብርት ያበቃል። እየደነዘዝክ ትታመማለህ ግን መጥፊያህን እያፋጠንክ ነው።

7️⃣ ስንፍና — ውስጣዊው ጠላት። የምትሰራው ስራ ስለሌለህ ደሃ ነህ። ያለ ምንም ጥረት ቀላል ህይወት ትፈልጋለህ። ከስኬት በላይ እንቅልፍን የምትወድ ከሆነ ድህነት ያስተኛሃል።

8️⃣ ራስን የመግዛት እጦት። ተግሣጽ የሌለው ሰው የራሱ ጭንቅላት ላይ የተነጣጠረ ሽጉጥ የያዘ ሰው ነው። ምንም ልማዶች፣ ምንም ወሰኖች፣ ምንም ራስን መቆጣጠር የለም። ደካማ ወንዶች ራሳቸውን ያጠፋሉ።

9️⃣ ወላጆችህን አለማክበር። ወላጆችህን ስትሰድብ፣ ስትተዋቸው — በረከቶችህ ሲደርቁ ተመልከት። ህይወት ወዲያው ላታስቀጣህ ትችላለች፣ ግን ፈጽሞ አትረሳም።

🔟 ለህልውና በሌሎች ላይ መደገፍ። ሕይወቱን በመለመን የሚያሳልፍ ሰው ያለ ክብር ይሞታል። ለመሰረታዊ ነገሮች በሰዎች ላይ መደገፍ አቁም — የራስህን መደገፊያ ገንባ።

1️⃣1️⃣ መጥፎ ጓደኞች — የእጣ ፈንታ ገዳዮች። ከ5 ቀልደኞች ጋር ነው የምትጓዘው? ህይወትህ ሰርከስ ቢሆን አትደነቅ። የጓደኞችህ ስብስብ የወደፊትህን ይወስናል።

1️⃣2️⃣ ማህበራዊ ሚዲያን ለማስደመም መኖር። እንደ ንጉስ መለጠፍ፣ እንደ ገበሬ መኖር። ባዶ የባንክ ሂሳብ እያለህ አይፎን መግዛት። ቲክቶክ ካልሰራህበት የቤት ኪራይህን አይከፍልም ወንድሜ፣ ስልክህን ወይ ሥራበት ወይ ሽጠው።

1️⃣3️⃣ ስሜታዊ ድክመት — የማይታይ ወጥመድ። ለስላሳ ልብ፣ ዜሮ ተጋላጭነት። ውድቅ ሲደረግ መፍረስ። በውድቀት ጊዜ ተስፋ መቁረጥ። ህይወት ከባድ ነች። አንተ ደግሞ ጠንካራ ሁን።

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ፦

የደከሙ ውሳኔዎችህ ለሚፈጥሩት ነገር ሰይጣንን መውቀስ አቁም። እጣ ፈንታ በራስ-ሰር (በራሱ) የሚመጣ አይደለም — የሚገነባ ነው። በላብ። በስትራቴጂ። በመስዋዕትነት። ልማዶችህን ካላስተካከልክ፣ ልማዶችህ ያጠፉሃል።

ስለሆነም አሁኑኑ ጀምር፦

✔️ ጊዜህን ተቆጣጠር
✔️ እውነተኛ ክህሎቶችን ገንባ
✔️ መጥፎ ነገርን አስወግድ
✔️ አስተሳሰብህን አጠንክር
✔️ የሚጠቅምህን አሳድድ፣ (ሴቶችን) አይደለም

ወንድ ሆነህ ተወልደሃል — እንደ ወንድ ሁን!!!
Adulis podcast

ሁለቱ ገንዘብ-ነክ ምርጫዎቻችን  fans  በወቅቱ ያለንበት የገንዘብ አቅም ደረጃ ምንም ሆነ ምን፣ የገንዘብ አያያዝን አስመልክቶ ሁለት አይነት አማራጮች እንዳሉን ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ 1....
03/07/2025

ሁለቱ ገንዘብ-ነክ ምርጫዎቻችን
fans
በወቅቱ ያለንበት የገንዘብ አቅም ደረጃ ምንም ሆነ ምን፣ የገንዘብ አያያዝን አስመልክቶ ሁለት አይነት አማራጮች እንዳሉን ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡

1. ተቋቁሞ መቆም (surviving)

ያለንን ገቢ አብቃቅተንና በበጀት አውጥተን ኑሮን ለመቋቋም ስንታገል የሚታይ ልምምድ ነው፡፡

ማድረግ የምንችለው፡- የገቢያችንን መጠን ስሌት በመስራት ያለንበትን ደረጃ በሚገባ ማወቅ፡፣ የወጪን ሁኔታ በንቃት መከታተል፣ ገንዘብ-ነክ ግቦችን ማውጣት፣ ከገቢያችን አንጻር የበጀት እቅድን ማውጣት፣ ገቢና ወጪን በየጊዜው መገምገምና ማስተካከያ ማድረግ፡፡

2. ተጣጥሮ ማደግ (thriving)

ካለንበት ወቅታዊ ሁኔታ ባለፈ ሁኔታ ግልጽ የሆነን እድገት የምንከተልበት ልምምድ ነው፡፡

ማድረግ የምንችለው፡- የገቢ ምንጫችን ወደ ምን ደረጃ ሊያድግ እንደሚገባው አስቀድሞ ማሰብ፣ የገንዘብ ገቢ ምንጫችንን የማሳደጊያ መንገዶችን መፈለግ፣ ተጨባጭና ሊመዘን የሚችል እቅድ ማውጣት፣ ገንዘብን፣ ጊዜንና እውቀትን ኢንቨስት ማድረግ፣ በየጊዜው እንዳለው ወቅታዊ ሁኔታ አቅማችንን ማሳደግን መቀጠል፡፡

በገንዘብ አቅማችን እያደግን ለመሄድ ተቋቁሞ ለመቆም ከመታገል ደረጃ ተጣጥሮ ወደማደግ ደረጃ መሸጋገር የግድ ነው፡፡
Adulis podcast

Address

Addis Ababa

Telephone

+251905264394

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adulis podcast posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Adulis podcast:

Share