መልካም ዜና Oduu Gaarii Good News

መልካም ዜና Oduu Gaarii Good News Breaking and leaked news

TRUMP DID IT!!!!PEACE PEACE PEACE!!!THE GREATEST PRESIDENT EVER!!
24/06/2025

TRUMP DID IT!!!!

PEACE PEACE PEACE!!!

THE GREATEST PRESIDENT EVER!!

ኢራን ቀይ መስመሩን አልፋለች - የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር**********************ኢራን ቀይ መስመር አልፋለች ሲሉ የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ  ተናገሩ።እስራ...
14/06/2025

ኢራን ቀይ መስመሩን አልፋለች - የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር
**********************

ኢራን ቀይ መስመር አልፋለች ሲሉ የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ተናገሩ።

እስራኤል ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ኢራን ላይ ባደረሰችው ጥቃት የጀመረው የሁለቱ ሀገራት ግጭት ከዚህ የበለጠ እንዳይባባስም ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል።

የኢራንን የተለያዩ ቦታዎች ካጠቃው የእስራኤል ወታደራዊ እርምጃ በኋላ ኢራን ትንናት ማምሻውን በጀመረችው ጥቃት ፡ እስካሁን 150 የሚሆኑ ባለስቲክ ሚሳይሎችን ወደ እስራኤል ትኩሳለች።

ሚሳኤሎቹ በእስራኤል የአየር መቃወሚያ ስረዓት ቢመክኑም የተወሰኑት ኝ መከላከያውን አልፈው በዋና ከተማዋ ቴላቪቭ መሃል ላይ ሲያርፉ ተስተውለዋል።

በተለያዩ የቴልአቪቭ ቦታዎች ላይ በወደቁት የኢራን ሚሳኤሎች ምክንያት የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ምሽቱን የከተማዋ እሳት አደጋ ሰራተኞች መሰማራታቸው ታውቋል።

በዚህ የኢራን የሚሳኤሎች ጥቃት እስካሁን 40 እስራኤላውያን መጎዳታቸውንና የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ሲኤንኤን ዘግቧል ።

ከዚህ ጥቃት በኋላ መግለጫ የሰጡት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ ኢራን አሁን ቀይ መስመር አልፋለች፤ ለዚህም የኢራን መንግስት ዋጋ ይከፍላል ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሴት የጦር ጄት አብራሪ በምርኮ እንዳልተያዘበት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ገለጿል።

በኢራንና እስራኤል ግጭት የእስራኤል ጦር ኢራንን እንዲደበድቡ፤ ከላካቸው የጦር አውሮፕላኖች መሀል ሁለቱን መትቶ መጣሉን የኢራን ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ተስኒም የተባለው ከኢራን መንግስት ጋር ግንኙነት ያለው የዜና ምንጭ፤ በፓራሹት የሚወርድ የጦር ጄት አብራሪ የሚታይበት ተንቀሳቃሽ ምስል ጋር አያይዞ ዜና አሰራጭቷል።

ከተመቱት ሁለት የእስራኤል የጦር ጄቶች መካከል የአንዱ አብራሪ የሆነችው ፓይለት በፓራሹት መውረዷን እና በኢራን ሠራዊት ተማርካ በቁጥጥር ስር እንደምትገኝ ዘግቧል።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ዘገባው ሀሰት ነው የተማረከብን ፓይለት የለም ሲል ማስተባበሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

232 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ አውሮፕላን በህንድ ተከሰከሰ232 መንገደኞችን አሳፍሮ ወደ ለንደን ያመራ የነበረ የህንድ አውሮፕላን ከተነሳ በኋላ መከስከሱ ተሰማ።አውሮፕላኑ ከአህመዳባድ አ...
12/06/2025

232 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ አውሮፕላን በህንድ ተከሰከሰ

232 መንገደኞችን አሳፍሮ ወደ ለንደን ያመራ የነበረ የህንድ አውሮፕላን ከተነሳ በኋላ መከስከሱ ተሰማ።

አውሮፕላኑ ከአህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ በተነሳበት ቅፅበት መከስከሱን ቢቢሲ አስነብቧል።

በወቅቱ 12 የአውሮፕላኑን ሰራተኞች ጨምሮ 232 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን፥ ከተነሳ በኋላ በ190 ሜትር ከፍታ ላይ ከአየር በረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር የመጨረሻ ግንኙነት አድርጓል ተብሏል።

የአደጋው መንስኤ እስካሁን ያልተገለጸ ሲሆን፥ አውሮፕላኑ በመኖሪያ መንደር አካባቢ መከስከሱንም ነው ዘገባው ያመላከተው።

ተፈታለች‼️ጃኒ(ስመኝ ገብሩ) የድሬዳዋን ነዋሪዎች በሙሉ ፍርድ ቤት ቆማ ሺቲ ለብሳ ይቅርታ ጠይቃለች  እንድታሰር ሳይሆን ፍቅርን ልታሳዩኝ ነው እዚህ ያመጣችሁኝ አመሰግናለሁ ብላለች🙏
12/06/2025

ተፈታለች‼️

ጃኒ(ስመኝ ገብሩ) የድሬዳዋን ነዋሪዎች በሙሉ ፍርድ ቤት ቆማ ሺቲ ለብሳ ይቅርታ ጠይቃለች
እንድታሰር ሳይሆን ፍቅርን ልታሳዩኝ ነው እዚህ ያመጣችሁኝ አመሰግናለሁ ብላለች🙏

የድምጻዊ አንዱአለም ጎሳን በዋስ የመፈታትን ውሳኔ በተመለከተ የሟች ቀነኒ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ ምን አሉ ?የቀነኒ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ ፤ " እስከዚች ሰዓት ድረስ ፖሊስም ሆነ ዐቃቤ ሕግ ...
11/06/2025

የድምጻዊ አንዱአለም ጎሳን በዋስ የመፈታትን ውሳኔ በተመለከተ የሟች ቀነኒ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ ምን አሉ ?

የቀነኒ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ ፤ " እስከዚች ሰዓት ድረስ ፖሊስም ሆነ ዐቃቤ ሕግ እዚህ ላይ ደርሰናል ብለው በግልጽ የነገሩን ነገር የለም። እንዲሁ በብላሽ ሦስት ወራት ነጉዷል። የልጃችንን ደምም፣ እውነታም አላገኘንም። ልጄን ለሁለተኛ ጊዜ ነው የገደሏት። " ብለዋል።

ከዚህ በኋላ ምን እንደሚያደርጉ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፥ " ሕግ ውስብስብ ነው፤ ዐቃቤ ሕግ የሚለውን አይተን ለአምላክ እንሰጣለን፤ እንደ ሰው የምንለው ነገር የለም። ቀነኒ ፍትህ እየተነፈገች ነው። ከጅምሩ አንስቶ የነበረ ነው። እኛን ለማድከም እስካሁን አቆዩን እንጂ ሊለቁት ከፈለጉ ቆይቷል። " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ፤ " በዚህ አካሄድ እንሞክር ብለን እንጂ ፍትህ እናገኛለን ብለን አናስብም። ከእሷ ደም የልጁ ታዋቂነት ይበልጣል " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

ታደለ ገብረመድህን በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ!አትሌት ገለቴ ቡርቃ "የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ይፍረደኝ፣ ተዘርፊያለሁ" በሚል ክስ የመሰረተችበት የቀድሞ ባለቤቷ ታደለ ገብረመድህ...
10/06/2025

ታደለ ገብረመድህን በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ!

አትሌት ገለቴ ቡርቃ "የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ይፍረደኝ፣ ተዘርፊያለሁ" በሚል ክስ የመሰረተችበት የቀድሞ ባለቤቷ ታደለ ገብረመድህን በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አትሌቷ ፍትህ ለማግኘት ለህዝብና ለመንግስት ጥሪ ያቀረበች ሲሆን፣ አሁን የቀድሞ ባለቤቷ በቁጥጥር ስር መዋሉ የጉዳዩን ሂደት ወደፊት እንደሚያራምደው ይጠበቃል።

የ50 ሚሊዮን ብር እድለኛ እየተጠበቀ ነው።"በኢትዮጵያ የሎተሪ ሽልማት ታሪክ ግዙፉ የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ  እድለኛ ቁጥር ታወቀ።“1557385” ሆኖ የወጣው የ50 ሚሊየን ብር እድል ጨምሮ...
07/06/2025

የ50 ሚሊዮን ብር እድለኛ እየተጠበቀ ነው።

"በኢትዮጵያ የሎተሪ ሽልማት ታሪክ ግዙፉ የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ እድለኛ ቁጥር ታወቀ።

“1557385” ሆኖ የወጣው የ50 ሚሊየን ብር እድል ጨምሮ በዛሬው እለት ባለእድለኞችን ሚሊየነር የሚያደርጉ ቁጥሮች ወጥተዋል። እድለኞችም እየተፈለጉ ሲሆን ሁለቱ ባለ እድሎች ታውቀዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአሁኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከ 64 ዓመታት በፊት በ50 ሺህ ብር የጀመረው የሎተሪ ዕድል ዛሬ ወደ 50 ሚሊየን አሳድጎ የ50 ሚሊየን ብር ባለ እድል የሚያደርገው ቁጥር በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳራሽ ወጥቷል።

በዚህም መሰረት አንደኛ እጣ የሆነው የ50 ሚሊየን ብር እድል አሸናፊ ቁጥር “1557385” ሆኖ ተመዝግቧል።

በሁለተኛ እጣ የ25 ሚሊዩን ብር አሸናፊ ቁጥር ደግሞ 3076394 ሆኖ ወጥቷል።

3192133 የሎተሪ ቁጥር በሶስተኛ እጣ የ10 ሚሊየን ብር አሸናፊ ቁጥር ሆኖ ሲወጣ “0391021” ደግሞ በአራተኛ እጣ የ9 ሚሊየን ብር አሸናፊ ቁጥር ሆኖ ወጥቷል።

በዲጂታል መንገድ በኢትዮ ሎተሪ ይፋዊ ድረገፅ አማካኝነት ከቆረጡ ደንበኞች መካከል ደግሞ የመጀመሪያ የሆነው እድል በ9ኛ እጣ የ4 ሚሊየን ብር ባለ እድል ሆኖ ሲመዘገብ አሸናፊው ቁጥር ደግሞ 5497274 ሆኖ ወጥቷል።

እጣው ከሚወጣበት ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳራሽ በቀጥታ በተመዘገበው ስልክ ቁጥር ላይ በመደውል ባለ እድለኛውን ማግኘት የተቻለ ሲሆን በዚህም መሰረት የአንቦ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ዶክተር ደመቀ የእጣው አሸናፊ መሆናቸው ተበስሯል።

ከዚህ በተጨመሪም የሚሊየን ሎተሪ በ11ኛ እጣ አሸናፊ ቁጥር 5338402 እጣ ቁጥር በተመሳሳይ በዲጂታል ሎተሪ የተቆረጠ ሲሆን የሁለት ሚሊየን ብር ባለዕድል ሆኗል።

እጣው በወጣ በሰከንዶች ውስጥ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ወደ ባለዕድሉ ስልክ የደወለ ሲሆን በቅርቡ ከውጭ ሀገር መምጣታቸውን የገለፁት እና በገደብ አሳሳ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሀመድ አማን ባለአእድል መሆማቸው ታውቋል።

ዛሬ በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳራሸ‍ ከወጣው እና በአንድ ጀምበር በርካቶችን ሚሊየነር ያደረገውን የሚሊየን የሎተሪ እጣ አሸናፊዎች መካከል የዲጂታል ሎተሪ የቆረጡ አሸናፊዎች ወዲያውኑ ሲታወቁ የወረቀት ሎተሪ ቆርጠው እጣው የወጣላቸው አሸናፊዎች እየተጠበቁ ነው ።

በአለም አደባባይ ያኮራችን ኢትዮጵያዊት ቆንጆ ሞዴል ሀሴት ደረጀ ሀገሯ ስትገባ ደማቅ አቀባበል ተደርግላታል🇪🇹🇪🇹
05/06/2025

በአለም አደባባይ ያኮራችን ኢትዮጵያዊት ቆንጆ ሞዴል ሀሴት ደረጀ ሀገሯ ስትገባ ደማቅ አቀባበል ተደርግላታል🇪🇹🇪🇹

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ 🇪🇹 የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤2. ብፁዕ አ...
23/05/2025

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ 🇪🇹

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦

1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።

ካርዲናል ሮበርት ፐሮቭስት 267ኛው የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ መሆናቸው ታወቀ***********************ካርዲናል ሮበርት ፐሮቭስት 267ኛው የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃ...
08/05/2025

ካርዲናል ሮበርት ፐሮቭስት 267ኛው የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ መሆናቸው ታወቀ
***********************

ካርዲናል ሮበርት ፐሮቭስት 267ኛው የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸው ታውቋል።

ከ40 ሺህ በላይ ምዕመናን ሁነቱን ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መገኘታቸውን የፖሊስ መረጃን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በለሚ ታደሰ

ቪዲዮውን ከዩትዩብ ያስጠፋችው እራሷ ልጅቷ መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ነው!!ፕሮግራሙ ከተላለፈ በሃዋል ደዉላ ቪዲዮ እንዲያጠፉ ካለሆነ እራሷን እንደምታጠፋ ፥ተናግራለች ባለቤቷ እንተቆጣ እንደዉ...
25/03/2025

ቪዲዮውን ከዩትዩብ ያስጠፋችው እራሷ ልጅቷ መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ነው!!
ፕሮግራሙ ከተላለፈ በሃዋል ደዉላ ቪዲዮ እንዲያጠፉ ካለሆነ እራሷን እንደምታጠፋ ፥ተናግራለች ባለቤቷ እንተቆጣ እንደዉም ስልክ ተቀብሎ ስሙን ተናግሮ ባህርዳር እንሚኖር እና የባንክ ሰራተኛ መሆኑን አሳወቆ ቪዲዮ እንዲጠፋ እንደተናገረ ከዛ ሰዓት ጀምሮ ስልካቸዉ ዝግ እንደሆነ ማግኘት እንዳልተቻለ መረጃዎች እያሳዩ ነው!!

ebs ቴለቭዥን ሰተቱን በፍጥነት የሰራውን ስዕተት አርሞ ለህዝቡ እውነታውን መናገር ይኖርበታል፤ ያለበለዛ ይሄ የሚዲያን ስነምግባር የጣሰ እና ያለ ምንም መረጃ ግጭት ቀስቃስ የሆነ ስራ በመስራታቸው በህግ ሊጠየቁ ይገባል።

ኢትዮጵያ ከግብፅ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል ለ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ሌሊት 6 ሰአት ከ ግብፅ አቻው...
21/03/2025

ኢትዮጵያ ከግብፅ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

ለ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ሌሊት 6 ሰአት ከ ግብፅ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።

ጨዋታው ሞሮኮ ላይ በላርቢ ዛውሊ ስታድየም የሚደረግ ሲሆን በኢትዮጵያ በኩል ግብፅን አክብደው እንደማይመለከቱና በከዋክብት የተሞላውን የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ለማቆም መዘጋጀታቸውን አምበሉ አስቻለው ታመነ ተናግሯል።

በቅርብ ሁለት ግንኙነታቸው ኢትዮጵያ ግብፅን 2-0 ያሸነፈችበት የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ላይ የሚጫወቱትን እንደ ሞ ሳላህ ኦማር ማርሙሽን የመሳሰሉ ተጨዋቾችን የያዘው የግብፅ ብሄራዊ ቡድን በ10 ነጥብ የምድቡ መሪ ነው።

በኢትዮጵያ በኩል የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋች አቡበከር ናስር ወደ ብሄራዊ ቡድኑ መመለሱ አዲስ የማጥቃት አማራጭ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

ብሄራዊ ቡድኑ የመጨረሻ ልምምዱን ጨዋታው በሚደረግበት ላርቢ ዛውሊ ስታድየም ያከናወነ ሲሆን ሁሉም ተጨዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መልካም ዜና Oduu Gaarii Good News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share