Ethiopia Today

Ethiopia Today Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopia Today, Media/News Company, Addis Ababa.

30/03/2023

ሰበር ዜና

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።

ሰበር ዜናየፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ቡድን ወደ መቀሌ አቀናየልኡካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስ...
26/12/2022

ሰበር ዜና
የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ቡድን ወደ መቀሌ አቀና
የልኡካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ መሆኑ የገልጿል።
በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራው የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል።
በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም መካተታቸወን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

02/11/2022

ህወሓት ትጥቅ ለመፍታት ተስማማ

Pretoria: the TPLF agrees to disarm after the 2-year bloody war it initiated.

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም  በጅግጅጋ ኤርፖርት  ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህ...
25/10/2022

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም በጅግጅጋ ኤርፖርት ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል።

ጉዳዩ በህግ አግባብ ተይዞ እየተጣራ ሲሆን በቀጣይ ሁኔታው የደረሰበት ደረጃ በሚመለከተው አካል የሚገለፅ ይሆናል።

በማእከላዊ ኮሚቴያችን አባል ላይ በደረሰው ህልፈት ፓርቲያችን ብልፅግና የተሰማውን መሪር ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቿ እና ለትግል አጋሮቿ መፅናናትን ይመኛል።

የመከላከያ ሠራዊት የመቀሌ አየር ማረፊያን ተቆጣጣረ ::ጥምር ጦሩ ተንቤን መክበቡ ታወቋል።
25/10/2022

የመከላከያ ሠራዊት የመቀሌ አየር ማረፊያን ተቆጣጣረ ::
ጥምር ጦሩ ተንቤን መክበቡ ታወቋል።

በድርድሩ የሚሳተፉ የትግራይ ክልል ልኡካን
24/10/2022

በድርድሩ የሚሳተፉ የትግራይ ክልል ልኡካን

የሀብት መጠናቸውን የደበቁ 17 ባለሥልጣናት ጉዳይ ለፍትሕ ሚኒስቴር ተላለፈየሀብት መጠናቸውን ደብቀዋል የተባሉ የ17 ሀብት አስመዝጋቢ ባለሥልጣናትን ጉዳይ ለተጨማሪ ምርመራ ለፍትሕ ሚኒስትር ...
18/10/2022

የሀብት መጠናቸውን የደበቁ 17 ባለሥልጣናት ጉዳይ ለፍትሕ ሚኒስቴር ተላለፈ
የሀብት መጠናቸውን ደብቀዋል የተባሉ የ17 ሀብት አስመዝጋቢ ባለሥልጣናትን ጉዳይ ለተጨማሪ ምርመራ ለፍትሕ ሚኒስትር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ማስተላለፉን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ገልጿል።
ለተጨማሪ ምርመራ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተላልፈው የተሰጡ ባለሥልጣናት፣ ኮሚሽኑ ባደረገው የሀብት አስመዝጋቢዎች የሀብት ማረጋገጥ ሥራ ካስመዘገቡት ሀብት መጠን ውጪ ሀብት ተደብቆ የተገኘባቸው ናቸው ተብሏል። ባለሥልጣኖቹ ያስመዘገቡት የሀብት መጠን እና ከምዝገባ በደበቁት የሀብት መጠን መካከል ከፍተኛ የመረጃ ክፍተት የታየባቸው ናቸውም ተብሏል።
ባለሥልጣኖቹ ኮሚሽኑ ባገኘው መረጃ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ተደርጎባቸው ክስ እንዲመሠረትባቸው መረጃቸው ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መላኩ ተሰምቷል። ሀብት አስመዝጋቢዎች በውሳኔ ሰጪነት ቦታ ላይ ያሉ የመንግሥት አመራሮች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ የማጣረት ሥራውን ሠርቶ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስተላልፏል።

ራያ ግንባርጥምር ጦሩ ከቆቦ 15 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ዋጃን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል።  አላማጣ የነበረው የህወሓት አመራር ህዝቡን ጥሎ ሸሽቷል። ✅ህወሃት መሸነፉን ሲያወቅ ልክ ወል...
13/10/2022

ራያ ግንባር
ጥምር ጦሩ ከቆቦ 15 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ዋጃን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል።
አላማጣ የነበረው የህወሓት አመራር ህዝቡን ጥሎ ሸሽቷል።
✅ህወሃት መሸነፉን ሲያወቅ ልክ ወልድያ ላይ እንዳደረገው ወደ ዋጃም ከባድ መሳሪያ ተኩሷል።
አላማጣ ላይ ኮማንዶው በቆረጣ የተሳካ ስራ ሰርቷል።

ደብረታቦር ዩኒቨርስቲ በአሁኑ ሰዓት******************* ********➢ የ12ኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተፈታኝ  ተማሪዎች የከሰዓቱን ፈተና ተፈትነው ወጥተው አሁን በተረጋጋ መንፈስ ...
11/10/2022

ደብረታቦር ዩኒቨርስቲ በአሁኑ ሰዓት
******************* ********

➢ የ12ኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች የከሰዓቱን ፈተና ተፈትነው ወጥተው አሁን በተረጋጋ መንፈስ እራታቸውን በመመገብ ላይ ይገኛሉ

➢ ለፈተና አሰጣጥ ሥርዓቱ ተገዥ በመሆን ቤተሰብ የጣለባቸውን አደራ መወጣት ትልቅነት ነው

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።አቶ ፍቅሩ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሌሊት በ88 ዓመታቸው ሕይወታቸው ማለፉን ኢዜአ ከቤተሰቦቻቸው ያገኘው...
11/10/2022

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
አቶ ፍቅሩ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሌሊት በ88 ዓመታቸው ሕይወታቸው ማለፉን ኢዜአ ከቤተሰቦቻቸው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ በዋናነት የሚነሱት ጋዜጠኛና ደራሲ ፍቅሩ ኪዳኔ የተወለዱት በ1927 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ነው።
አባታቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ የነበሩ ሲሆን፣ የክለቡን ተጫዋቾች ከትምህርት ቤት ወደ ስታዲየም ይዞ በመሄድ ይታወሳሉ፡፡
በእነዚህ ጊዜያት ሁሉ ከአባታቸው ጋር የመሆን ዕድል የነበራቸው አቶ ፍቅሩ በኋላ የስፖርት አስተማሪ ሆነዋል።
በኢትዮጵያ ሬዲዮና የተለያዩ የአገር ውስጥ የሕትመት ውጤቶች ስለ አገር ውስጥ ስፖርት መዘገብ የጀመሩት አቶ ፍቅሩ በ1943 ዓ.ም በሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በቀጥታ በሬዲዮ ማስተላለፍ የቻሉ የመጀመሪያው የስፖርት ጋዜጠኛ ናቸው።
አቶ ፍቅሩ የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር በ1961 ዓ.ም ሲመሰረት የመጀመሪያው ፕሬዝደንት የነበሩ ሲሆን በብስክሌት ፌዴሬሽን፣ቴኒስ ፌዴሬሽን እና በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በዋና ፀሐፊነት፣ በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት በመሆን አገራቸውን አገልግለዋል፡፡
በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውስጥም በአመራርነት ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የቀድሞ ፕሬዝደንት የነበሩት የኢሳ ሃያቱ አማካሪ ጭምር የነበሩ ፡፡
ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ ኑሯቸውን በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ያደረጉት አቶ ፍቅሩ በሀገሪቷ ለሚገኘው ዕለታዊ የስፖርት ጋዜጣ ለኪፕ እና ሳምንታዊ የእግር ኳስ መጽሔት ፉትቦል ፍራንስ፣ ዶቼቬሌ (የጀርመን ድምፅ) እና ሌሎች የአለም አቀፍ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን መስራት ከመቻላቸው በተጨማሪ “የፒያሳ ልጅ” እና “የስፖርት ጨዋነት ምንጮች” የተሰኙ መጻሕፍት መጻፍ ችለዋል፡፡
ጋዜጠኛና ደራሲ ፍቅሩ ኪዳኔ አንድ ልጅ ያላቸው ሲሆን ሁለት የልጅ ልጆችንም አይተዋል።

 " እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛሉ " - የሲዳማ ክልል ሰላ...
10/10/2022



" እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛሉ " - የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

ዛሬ ጠዋት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናውን ግቢ እና የቴክኖሎጂ ካምፓስ ግቢን የሚያገኛኘው ድልድይ ተደርምሶ በደረሰው ጉዳት እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ እና ሁለት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ይህን የገለፀው የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ነው።

የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " እስከአሁን ባለው ሂደት በጉዳቱ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ፣ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል " ብለዋል።

እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ከሚመለከተው አካል ብቻ በማግኘት እንዲያረጋግጡና እንዲረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Today posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share