
25/08/2024
ሰበር ዜና!
"ኮለኔል ጨምሮ ከአንድ መቶ በላይ ምርኮኛ በዛሬው ውጊያ ይዘናል።" አርበኛ ደረጀ በላይ
የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ በአገዛዙ ሠራዊትና ካድሬዎች ላይ በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ጀብዱ ተጎናጽፏል።
ከ300 በላይ ክላሽ በተጨማሪ ስናይፐርና ብሬን ለፋኖ ገቢ የሆኑ ትጥቆች ናቸው።
የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረጀ በላይ ለኢትዮ 251 ሚዲያ እንዳስታወቀው፤ አንጸባራቂው ድል የተገኘው በጎንደሬ በጋሻውና በጌምድር ክፍለ ጦሮች ሲሆን በተለይም በአይሸሽም ብርጌድ ነው። "በቅርቡ የተሰዋውን ጀግናውን አዋጊ ሻለቃ ገበየሁን ታሳቢ በማድረግ በስሙ የተከፈተው ዘመቻ በከፍተኛ ድል ታጅቦ ቀጥሏል" ያለው አርበኛ ደረጀ፤ በተጋድሎው መቶ የአገዛዙ ሠራዊት በምርኮ መያዙን አርበኛ ደረጀ በላይ ገልጿል።
አርበኛ ደረጀ በላይ አክሎም፤ አንድ ኮሎኔልና ሌሎች ኢንስፔክተሮችም በምርኮ መያዛቸውን አስታውቋል። ሰሞኑን የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ያስመዘገባቸውን ድሎች ያስታወሰው አርበኛ ደረጀ በላይ፤ የምዕራብ ጎንደር ዞን አመራሮች ላይም የማያዳግም እርምጃ መወሰዱን ለኢትዮ 251ሚዲያ አስታውቋል።
የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረጀ በላይ ሰሞኑን፤ "የወንድነት መፈታተሻ ልዩ የትግል ጥሪ" ማቅረቡ ይታወሳል። የጠላት ሠራዊት ከአማራ ክልል አንድም ትጥቅ ይዞ መውጣት የለበትም የሚለው የአርበኛው የክተት ጥሪን ተከትሎ፤ የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ሁሉም ክፍለ ጦሮች በውጊያ ላይ እንደሚገኙ ኢትዮ 251 ሚዲያ ከዕዙ አመራሮች ሰምታለች።