01/01/2026
፨ሰላም ማለት ምን ማለት ነው?፨
ሰላም ማለት፡- በየትኛውም መልኩ ከማንኛውም ሰላምን ሊያውኩ ከሚችሉ ሁከትና ሌሎች ተግባራት፣ ከስጋት ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኖ መኖር ሲሆን ምንም እንኳን በሰላም ለመኖር ከጦርነት፣ ከሁከት፣ ከግጭትና ከብጥብጥ ወዘተ ከመሳሰሉት የሰላም ተፃራሪዎች ሁሉ ነፃ መሆን ቢሆንም
በአጠቃላይ የሰላም ፅንስ ሀሳብ ከግጭት ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆን ማለት ሳይሆን በማንኛውም መልኩ ነፃ በሆነ መንገድ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ አብሮ በሚኖረው ማህ/ሰብ መካከል በመተሳሰብ፣ በመደጋገፍ፣ በመወያየትና በመቻቻል በአንድነት መኖር መቻልና ችግሮች በሚፈቱበት ደረጃ ላይ ማድርስ መቻል ነው፡፡
፨የሰላም እሴት ምንድን ነው?
የሰላም እሴት ማለት የባህሪ የአመለካከት የአኗኗር ወዘተ የእሴቶች ስብስብና ዘይቤ ነው፡፡
የሰላም እሴት ከጦርነት ከአመፅ ከሽብር ወዘተ ከመሳሰሉት ባህሎች /ተግባሮች/እነዚህን ተግባራት ማንኛውንም ከሁከትና ብጥብጥ የሚጸየፍ የተፈጠሩ ግጭቶችን ሁሉ በውይይትና በመግባባት የመፋታት ባህል መሻጋገር ማለት ነው፡፡
👉ዜጎች አለመግባባትን በሰላማዊ ውይይትና ድርድር እንዲሁም ከማንኛውም ሁከት ነፃ በሆነ መልኩ መፍታት የሚቻልበትን ጥበብ ከተገነዘቡ፣ አሉታዊ የሆኑ ደንብና ስርዓቶችን ሲቀርፉ ሰላም መገንባታቸውን ያሳያል፡፡
👉ህ/ሰቡ በዘልማድ ከሚደነግገው የወንዶች የበላይነት ወደ ህገ-መንግስታዊ የፆታ እኩልነት የአመለካከት አድማሱን በማስፋት ግንዛቤውን ሲይዝ የሰላም ባህል ተሸጋጋሪ መሆኑን ያሳያል፡፡
👉በህ/ሰቡ (በዜጎች) ዘንድ የሚታዩ መከፋፈሎች ተቀርፈው አንድነት እና መተሳሰብ በዜጎችና በግለሰቦች ዘንድ ተፈጥሮ ሲታይ የሰላም እሴት ተምሳሌትን ያሳያል፡፡
👉በማንኛውም ወቅትና ጊዜ ዲሞክራሲያዊ ትግልና ተሳትፎ በነፃነት የመግለጽ ስርዓት በሰፊው ሲለመድ እና በህ/ሰቡ (በዜጎች) ሲተገበሩና ተቀባይነታቸው ሲጎለብት የሰላም እሴትን ያሳያሉ፡፡
👉ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ግልጽ ግንኙነት ሲኖርና ዜጎች እንደ መርህ ወይም መመርያ ሲጠቀሙበት ማየት የሰላም እሴት ተምሳሌትን ያሳያል፡፡
👉 ሁሉም ሰው ሰብአዊ መብትን ማክበር የተለመደ ተግባር ሆኖ ሲታይ፣ መንግስት በህጋዊ መንገድ የዜጎችን ደንብና ስርዓት መሰረት ባደረገ መልኩ ስልጣንን በአግባቡ ሲጠቀም ማየት እና መገልገል የሰላም እሴትን ያሳያል፡፡
👉 መንግስት ኢ-ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ስልጣንን ከማራዘም እና ከማጠናከር ይልቅ አለም አቀፋዊ ለሆኑ የዜጎች ህግና መብት መከበር ተሳትፎና ድጋፍ ሲያደርግ መመልከት የሰላም እሴትን ያመላክታል፡፡
👉 በዜጎች ደንብና ስርዓት ለውጥ ውስጥ እድገት ከገንዘብ እና ከሃብት አቅም ይልቅ ለማህ/ሰቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖማያዊና ፖለቲካዊ እድገትና ለውጥ በማተኮር ፍትሃዊና ዘላቂነቱ የተረጋገጠ አካባቢያዊ መስተጋብር ሲኖር የሰላም እሴት ያሳያል፡፡ በሌላ መልኩ የሰላም አደናቃፊዎች ደግሞ
1️⃣የግል አረዳድ
2️⃣የተዛባ ግላዊ ቅድመ ትንቢያ
3️⃣ አድሎአዊ አሰራር እና ማግለል
ነገሮችን አስቀድሞ አጠቃሎ ማየት ሲሆን ብዙውን ጊዜ የሰላምና የግጭት ትንተና እንደማሳያ ነው፡፡
ምንጭ፦ማህበራዊ ሚዲያ