Ethiopia Hagere

Ethiopia Hagere Free Ideas are shared here

31/12/2021
29/12/2021

“ኢትዮጵያ የእንግዴ ልጇን እየቀበረች ነው”
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
“ኢትዮጵያ የእንግዴ ልጇን እየቀበረች ነው”- ኮሎኔል ጌትነት አዳነ የአገር መከላከያ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር
ኢትዮጵያ የእንግዴ ልጇን እየቀበረች ነው ሲሉ የአገር መከላከያ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ተናገሩ።
የአገር መከላከያ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፤ ኢትዮጵያ የተገላገለችውን ልጅ ስታቅፍ በተመሳሳይ የእንግዴ ልጇን እየቀበረች ነው ሲሉ ተናገሩ።
አገራችን ኢትዮጵያ አሁን በመታረስ ላይ ናት። በመታረስ ሂደት አንድም የወለዱትን ማቀፍ አንድም የእንግዴ ልጅን መቅበር የተለመደ ነው ። ሴት ልጅ ስትታረስ የደረቀ አናት ካለ የሚቀባ ነገር ይቀባል። የቆሸሸ አካል ካለም ይታጠባል፤ የኢትዮጵያም ዕውነታ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
እናት ስትወልድ ሳይጠራ የሚያልፍ ነገር እንዳይኖር ጥንቃቄ ይደረጋል። ከዚህ ባለፈ ብቻዋን እንዳትሆን ጥበቃ ሊደረግላት ይገባል። አገራችንም በተመሳሳይ የመታረስ ጊዜዋ ላይ ነችና ልክ አራስ እናት የሚያስፈልጋት ድጋፍና እንክብካቤ ሁሉ ያስፈልጋታል ብለዋል።
እናት በመታረስ ጊዜዋ ጠንክራና ቆማ እንድትሄድ መታገዝ ትፈልጋለች። አገራችንም እንዲሁ ፈታኝ ጊዜዋን አልፋ እንድትሄድ እገዛ ትፈልጋለች። በተግባር እንደታየውም በጀግኖች ልጆቿ አማካኝነት የገጠማትን ፈተና ሁሉ እያሸነፈች እዚህ ደርሳለች ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ በኋላም ሠራዊቱም የአገር ዳር ድንበር በጀግንነቱ እያስከበረ ይቀጥላል ብለዋል።
ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ሆነን የኢትዮጵያን የእንግዴ ልጆችን እንቀብራለን፤ በቴክኖሎጂውም እራሳችንን እያሳደግን እንቀጥላለን። መከላከያም ከጀግኖች ልጆቿን ይዞ የማይወጣው ተራራ የማይሻገረው ሸጥ አይኖርም። ኢትዮጵያ የተፈተነችበትን ሁሉ አውድ ታሸንፋለች ብለዋል።

29/12/2021

backed terrorist Group

23/12/2021

ነጭ ዓለምን በቅኝ ግዛት ይዞ የነበረው ዘመናዊ ጠመንጃ በመፈልሰሙ እንጅ የተለየ ጀግንነት ኖሮት አልነበረም። ዛሬም ዓለምን በድጋሜ በመዳፌ ስር ካላስገባሁ የሚለው፣ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ተማምኖ እንጅ ከሰው በላይ የሚያደርገው ወኔ ኖሮት አይደለም። ወኔና ጀግንነት ያለውስ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ነው። ከ ኢትዮጵያ ጋር በጀግንነት የሚወዳደሩት ጃፓኖችንና ቬትናሞችን የመሳሰሉ የጥንት ታሪክ ያላቸው አገሮች እንጅ የጦር መሳሪያ ያጀገናቸው አንግሎ ሳክሰን ምዕራብያውያን አይደሉም።
ነጮች ድሮንን የፈለሰሙት አንበጣ ሊያባርሩበት ወይም ጌታቸው ረዳ እንደሚለው ለልጆቻቸው መጫወቻ አሻንጉሊት ይሆን ዘንድ አይደለም። ድሮን በህግ ያልተከለከለ የጦር መሳሪያ ነው። ከጦር አውሮፕላን የሚለየውም ሰው አልባ መሆኑ ብቻ ነው። ስለዚህ ድሮን መጠቀምን እንደ ወንጀል ለማሳየት የሚደረገው ሙከራ፣ በራስ ላይ እንደመተኮስ የሚቆጠር ነው። አሜሪካ ሲጠቀምበት ቅዱስ፣ ኢትዮጵያ ስትጠቀምበት እርኩስ እንዲሆን ተብሎ የተፈጠረ የጦር መሳሪያ የለም።
እኔን የሚያሳስበኝ ልጆቻችን እንዲህ አይነቱን ውጤታማ ቴክኖሎጂ በምን ያክል ብቃት ይጠቀሙበታል የሚለው ጥያቄ ነው። መንግስት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰጠው ትኩረት በጣም ጥሩ ቢሆንም መድረኩን በሚፈለገው መጠን አስፍቶታል ወይ ለሚለው ጥያቄ በቂ መልስ የለኝም። ቢሆንም በትላልቅ ተቋማት የሚሰሩ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሰዎች፣ የመንግስት ፖሊሲ ምንም ይሁን ምን፣ አገራቸውን የሚያግዙበት ጊዜ አሁን መሆኑን መንገር ያስፈልጋል።
የወደፊቱ ጦርነት ከምድር ይልቅ በሰማይ ላይ ይሆናል። ነጮችን በቴክኖሎጂ እድገት ፈጥነን ካልያዝናቸው፣ እነሱ ከላይ ሆነው ሲወጉን፣ እኛ ከስር አንጋጠን እያየን ልናልቅ እንችላለን። የድሮን ቴክኖሎጂ በክላሽ መፎከር የሚያበቃበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን እየነገረን ነው። ይህን ቴክኖሎጂ የራሳችንን ፈጠራ አክለንበት በብዛትም በጥራትም ልንይዘው ይገባል።
የኢትዮጵያ ሰራዊት ያሸነፈበትን ምክንያት በሌላ ቦታ ላይ ገልጫለሁ። የጽሁፌ አላማ ድሮን መጠቀምን እንደ ወንጀል ለማሳየት ለሚሞክሩት ምላሽ ለመስጠት ብቻ መሆኑ ይታወቅልኝ።
ፋሲል የኔዓለም

  ARMY
18/12/2021

ARMY

18/12/2021

Congratulation Ethiopians
ወልዲያ ነፃ ወጣች።
18 Dec 2021 - Ethiopian forces fully clear out TPLF from North Wollo zone, recapturing its strategic capital - Weldia.
Sanqa, Sirinqa, Haran, Gobyen, Robit, Qobo towns plus Hamusit, Estayish, Ahun Tegegne, Dilb, Kul Mesk and surrounding areas fully cleared of TPLF.
Source: Office of the Prime Minister - Ethiopia

10/12/2021

ሸርቅ ኦንላይን ጋዜጣ
ኢትዮጵያውያን 98 በመቶ አሸንፈዋል። አለም ካሰበው በተቃራኒው ቆመው አለምን አስደምመዋል። ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ለመቆጣጠር የትንሽ ሰአት መንገድ የቀረውን አማፂ አለበት ላይ በመጨረስ በመጨረስ አዲስ ክስተት ሰርተዋል።
የአለም ህዝብ ሲጠበቀው የነበረውን አዲስ መንግስት፣ አሜሪካ የመሰረተችው የጥምር ብሔር ሽግግር ሀሳብ አሜሪካ ላይ ቆሞ እንዲቀር አድርገዋል። ከቱርክ በመቀጠል ሁለተኛውን አስደሚማ ነገር ለአለም ህዝብ አሳቀዋል። አይቻልም የተባለው የቱርክ መፈንቅለ መንግስት በህዝብ መከሰሩ፣ አያቅተውም የተባለው የህወሓት ግስጋሴ ተሰብሮ መቅረቱ እነዚህ ሁለቱ የአለም ህዝብ የምንግዜም ድንቅ ክስተት ሆነው ይኖራሉ
ሱሌማን አብደላ

  The Land of Braves!
10/12/2021

The Land of Braves!

Terara Network was founded on September 26, 2020 by veteran Ethiopian jour… Ted Media needs your support for ተራራ ኔትዎርክን እናጠናክር Support Terara Network

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Hagere posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share