Gish Media ግሽ ሚዲያ

Gish Media ግሽ ሚዲያ ሀቅ ብቻ።
(2)

ጠቃሚ ቪዲዮ ነው ተመልከቱት
15/10/2024

ጠቃሚ ቪዲዮ ነው ተመልከቱት

In this Video I will show you 3 best websites to make money online How to make money online by YouTube, Upwork and dropshipping ...

የጎንደር ጀግኖች
23/07/2024

የጎንደር ጀግኖች

ኮማንደር አሰግድ መኮንን ካሳተማቸው መፅሐፍት ትቂቶቹ
23/07/2024

ኮማንደር አሰግድ መኮንን ካሳተማቸው መፅሐፍት ትቂቶቹ

23/07/2024

ፖለቲካ ከገባህ
እንደ አማራ: –
አቶ አሰግድ የአማራ ህስብንና የፋኖዎችን ትግል ከድተው ወደ ብልፅግና መግባታቸውን እያወክና የተረጋገጠ መረጃ እያለህ እንኳ ቢሆን በፕሮፓጋንዳው ሜዳ አቶ አሰግድ በፍፁም ክህደት አልፈፀሙም ብለህ ድርቅ ማለትና መካድ ነው ያለብህ!

የአብይ አህመድ የፖለቲካ ስሌት ጠንቅቀን ካወቅነው ቆይተናል። መሰረቱ convince እና confuse መሆኑን ከነገሩን ቆይተዋል።

አቶ አሰግድ ለመንግስት እጃቸውን ሰጡ ካለ አብይ አሀመድ ሰውየው የተያዙት በሌላ መንገድ ነው። በጦርነት ግጥሚያ ወይም በደህንነት ክትትል ያዝካቸው ቢል በፋኖዎች መካከል የሚፈጥረው ውዥንበር አይኖርም። በጦርነት መማረክና በደህነነት ክትትል እጅ ውስጥ ጥንቃቄ ከሌለ ማንም ሊወድቅ ይችላል። እናም በዚያ መልኩ ተያዙ ቢባል ትግሉ ላይ የሚፈጥረው ተፅእኖ አይኖርም ። ለመንግስት እጃቸውን ሰጡ ማለት ትግሉን አላመኑበትም ወይም ከዱ ማለት ነው። ይህ ዜና ሆነ ማለት እሳቸውን ተከትሎ ወይም በእሳቸው እዝ ስር የነበረው በሙሉ እሳቸውን ተከትሎ እጅ ይሰጣል ነው ቁማሩ።

አብይ ማለት እባክሁ ሙፍቲ ሸህ ዑመር ሆይ ? የመጅሊስ ውዝግባችሁን ይፈታ ዘንድ ያግዙኝ ብሎ ሁለት ጊዜ ቤታቸው ድረሰ ሄዶ እግራቸው ላይ ወድቆ ለምኖ የሳቸውን ጀመአ ካስተኛ በኋላ የመጅሊስን ስልጣን በሱ ትእዛዝ በመሳሪያ በተደገፈ ግልበጣ በውልደትም፣በቋንቋም፣በክልልም እሱን ለሚመስሉት ሀጂ ኢብራሂም አሳልፎ የሰጠ ነው።

የኦርቶዶክስ እምነትን ሲበጠብጥ የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ፓስተርን ወይም ሀጂ ኢብራሂም ቱፋን ከፊት አሰልፎ አልነበረም። ቤተ እምነቷን ውስጠ ጓዳዋን የሚያውቀውን ዳንኤል ክረትን ይዞ። በዳንኤል ክብረት ሹመት ኦርቶዶክስ የጨቋኝ ገዢዎች እምነት ነው ብለው አምርረው የሚጠሉት የጎረቤት ቡድኖችና በአፄ ሚኒሊክ ላይ ያቄመው በሙሉ የነበረውን ቅሬታና ጩኸት የሚረሳ አይደለም። ለዳንኤል ክብረት ሺመት ሰጥቶ የዚያኛው ካምፕ ጩኸት ሲጨመርበት አብይ አህመድ የኦርቶዶክስ ወዳጅ መሰለ። በቅርብ ጊዜ ያየነውን ውዝግብ በእምነት ቤቷ ላይ ይፈፅማል ብሎ የገመተ ሰው አልነበረም።

በምርጫ 97 የምርጫ ቅስቀሳ የመጨረሻ ቀን show of public support አቶ በድሩ አደም ያላሉትን
ትግሬ ወደ መቀሌ
ንብረት ወደ ቀበሌ
ተብሎ አጀንዳ ሲፈተልና ሲዶለት አለማው በመለስ ዜናዊ አመራር ከወያኔ የተገፉ አመራሮችና የጦር ሰዎችን ወደ አንድነት ለመመለስ የተሰራ የፖለቲካ ስራ ነበር። እነ ስዬ አብራሀ ከተከበርኩበት ስልጣን አንስተህ እስር ቤት ወርውረኸኛልና ስራህ ያውጣህ አላሉትም መለስን። ይህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን በትግራዋይነት ላይ የመጣ አደጋ ነውና አደጋውን ለመቀልበስ ልዪነታችንና ጠባችንን ወደ ጎን ብለን ትግራዋይነትን ለመታደግ ወደ እናት ድርጅታችን ተነለስን ነበር ያለው ስዬ አብራሀ። ውሸት ላይ ተነስተው የቆመሩት ቁማር ያኮረፈውን ሁሉ ሰብስበው ድርጅታቸውን ከዚያ ማእበል ታደጉ።

Who cares about the truth? ለዚያ ይሆን ማርክሲስቶች ~ political ideology ን በ ~ false consciousness ~ ይከሱ የነበረው?

አብይ አህመድ
> በመሻይኮቻችን ቆምሮ መጅሊስን ለሚመስለውና ለወህቢያ ካስረከበ
> በዳንኤል ክብረት ቆምሮ ኦርቶዶክስን ካመሰ
> ዴቄት አድርገናቸዋል ብሎ ለፕሪቶሪያ ሰላም ከተቀቀመጠ

እዚህ ውስጥ እውነታ ቦታ ነበራትን? በፍፁም!

ወገኔ ቁማሩ ይግባህና አንተም ቆምርና እንኳን የሚካደውን የማይካደውንም ክደህ የዚህ ዘመን የፋኖዎች ትግል ከወጀቡ ሁሉ ጠብቀህና አድነህ ልእልናና ድልህን አውጅ!
hasse

ሰበር ዜና❗ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዘኑ❗Gish Media ግሽ ሚዲያጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ማዘናቸውን ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒ...
14/07/2024

ሰበር ዜና❗
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዘኑ❗
Gish Media ግሽ ሚዲያ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ማዘናቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ጥቃቱን አስደንጋጭ ብለውታል።

ትራምፕ ከጉዳታቸው በፍጥነት እንዲያገግሙ ምኞታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም ተመኝተዋል።

 #ታይላንድ‼️ Attention❗ለስራ ወደ ታይላንድ የሄዱ ኢትዮጵያውያን ለከፍተኛ ስቃይ እየተዳረግን ነው ሲሉ ገልፀዋል። መንግሥት በአስቸኳይ ይድረስልን የሚል ተማፅኖም አቅርበዋል።Gish M...
11/07/2024

#ታይላንድ‼️ Attention❗
ለስራ ወደ ታይላንድ የሄዱ ኢትዮጵያውያን ለከፍተኛ ስቃይ እየተዳረግን ነው ሲሉ ገልፀዋል። መንግሥት በአስቸኳይ ይድረስልን የሚል ተማፅኖም አቅርበዋል።
Gish Media ግሽ ሚዲያ ለስራ ወደ ታይላንድ ባንኮክ ከሄዱ ኢትዮጵያን ውስጥ የታሰሩ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን፣Electric shock እና ግርፊያ እንደሚፈፅሙ አንድ በታይላንድ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ገልፆልኛል። ስልክ እንኳን በሳምንት ለተወሰነ ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚፈቅዱልን ብሏል። ለስራ ተብለን የሄድን ቢሆንም የሚያሰሩን ሌላ ስራ ነው ብሏል፣የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪ ያደረጓቸውም አሉ ብሎኛል። ሴቶቹም እየተደፈሩ ነው ብሏል።
መንግሥት ይድረስልን የሚል ተማፅኖ አቅርቧል። ወደ ታይላንድ ለስራ በሚል ማንም ኢትዮጵያዊ ባይሄድ እመክራለሁ ሲል ገልጿል ።
አሁንም የውጭ ሀገር ፕሮሰስ እያደረጋችሁ ያላችሁ የሀገራችን ልጆች የት ? ለምን ? ስራ እንደምትሄዱ ጠይቁ መርምሩ።

አሁን ላይ በማይናማር እና ታይላንድ ድንበር በሚገኝ ስፍራ እንደ ባርነት የተያዙ የናይጄሪያ፣ የሲሪላንካ... እና የሌሎች የበርካታ ሀገራት ወጣቶች አሉ።

ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ ተከታትሎ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል።

ታይላንድም ይሁን አሜሪካ ፣ ካናዳም ይሁን አውሮፓ ደህንነቱ የተጠበቀ ህጋዊ ስራ ካልሆነ ባትሄዱ ይመከራል።

የሚልኳችሁን ሰዎች በትክክል የት ነው የምንሄደው ? የምናርፈው የት ነው ? የድርጅቱ ስም ምንድነው ? የመስሪያ ፍቃዱ የታለ ? አድራሻው የታለ ? ከዚህ በፊትም የሄዱ ልጆችን አገናኙን ብላችሁ ብጠይቁ የተሻለ ነነው ።

ሳይታገት ታግቻለሁ ብሎ በሃሰት ከባለቤቱ 500,000.00 ብር የተቀበለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ። Mediaየ63 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ እና የ5 ልጆች አባት የሆነው አቶ ገብረ ተንሳኢ ተ...
11/07/2024

ሳይታገት ታግቻለሁ ብሎ በሃሰት ከባለቤቱ 500,000.00 ብር የተቀበለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።
Media
የ63 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ እና የ5 ልጆች አባት የሆነው አቶ ገብረ ተንሳኢ ተክላይ ከወይዘሮ ዘነበች በርሄ ጋር ለ14 አመታት በትዳር ተጣምረው በአሶሳ ከተማ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው 4 ልጆችን አፍርተዋል።

በትዳር ህይወታቸው ውስጥ ምንም አይነት እንከን እንደሌለ የሚገልፀው አቶ ገብረተንሳኢ ተክላይ ወይዘሮ ዘነበችን ከማግባቱ በፊት አንዲት ሴት ልጅ እንዳለችውና እሷም ለብቻዋ አዲስ አበባ እንደምትኖር በመግለፅ ይህንን እኩይ ተግባር ለመፈፀም የተነሳሳውም የግል ልጁን ለመርዳት እንደሆነ ተናግሯል።

ከሚኖርበት አሶሳ ከተማ ወደ ነቀምት ከተማ በመጓዝ " ኦጌቲ" በሚባል ሆቴል ውስጥ ለሁለት ቀናት አልጋ ይዞ በመተኛት ከሆቴሉ አስተናጋጆች የ21 ዓመት ልጅ የሆነውን ወጣት ገመቹ ዮናስን በመግባባት የአጋችና ታጋች ድራማውን አብሮት እንዲሰራና ለዚህም ታግቻለሁ ብሎ ከሚላክለት ብር ላይ 25,000 ብር እንደሚሰጠው በመንገር ያሳምነዋል።

በዚህም መሰረት ባል አቶ ገብረተንሳኢ ተክላይ በሸኔ ታግቻለሁ ብሎ ለባለቤቱ ደውሎ በመንገር ስልኩን ይዘጋል። ሚስት ወይዘሮ ዘነበች የምትይዘው የምትጨብጠው ይጨንቃታል። ከ24 ሰዓታት በኋላ ወጣት ገመቹ ዮናስ ደውሎ ኦነግ ሸኔ ነን አግተነዋል 800,000 ብር ካላስገባሽ ባልሽን አታገኝውም ይላታል። ሚስት እባካችሁ የልጆቼ አባት ነው እንዳትገሉብኝ ለምኘም ቢሆን ያገኘሁትን ብር እልክላችኋለሁ ስትል መልስ ሰጠች።

በወቅቱ ይህ የሃሰት የወንጀል ድራማ ከምዕራብ ዕዝ የመረጃ ሞያተኞች ጆሮ በመድረሱ በከፍተኛ ጥንቃቄ የጉዳዩን መነሻና መድረሻ በመከታተል የተሟላ መረጃና ማስረጃ ለመያዝ መንቀሳቀሳቸውን የዕዙ መረጃ መኮነን ተናግረዋል ።

ወይዘሮ ዘነበችም በዙሪያዋ ያሉ ዘመድ ወዳጆቿን አስተባብራና ያላትን ሁሉ ጨምራ የልጆቿን አባት ለማስፈታት 500,000 ብር ለመላክ አዘጋጅታለች። በሁለተኛው ቀን አጋች ነኝ ያለው ወጣት ገመቹ ዮናስ ደውሎ ባልሽን አትፈልጊውም ? ይላታል ። በፈጠራችሁ አምላክ 4 ልጆች ያለ አባት ማሳደግ አልችልም እያለች በመማፀን ያለኝ 500,000 ብር ነው ልላክላችሁ እና ልቀቁልኝ ትላለች።

ሃሰተኛ አጋችና ታጋች አገኘሁ ባለችው ብር ተስማምተው ገንዘቡን የምትልክበት አካውንት በመላክ ሌላ ነገር ብታስቢ ግን እንገለዋለን ብሎ ያስፈራራታል። ብሩም በወጣት ገመቹ ዮናስ አካውንት ተላከ።

አቶ ገብረተንሳኢ ተክላይ ለገመቹ የገባውን ቃል 25,000 ብር በመስጠት ቀሪውን አውጥቶ የግል ልጁ በሆነችው አካውንት አስገብቶ እንዲቀመጥ ይነግራታል።

ከዚህ ሁሉ በኋላ በንቃትና በትኩረት ጉዳዩ ሲከታተል መረጃና ማስረጃዎችንም ሲያሰባስቡ መቆየታቸውን የገለፁት የምዕራብ ዕዝ የመረጃ ቡድን የሃሰት አጋችና ታጋችን በቁጥጥር ስር በማዋል ገንዘቡንም በፍጥነት ከገባበት አካውንት ተመላሽ እንዲሆን በማድረግ ዋና ወንጀል አድራጊና የወንጀሉ ተባባሪን ለነቀምት ከተማ ፖሊስ አስረክበዋል።

ወይዘሮ ዘነበች በርሄን ከአሶሳ ከተማ በስልክ አናግረን በጉዳዩ ላይ በሰጠችን ቃለ- ምልልስ 14 አመታትን አብሮኝ ከኖረውና ከልጆቼ አባት ይህንን ፍፁም አልጠበቅም። ማመንም ተስኖኛል። በተግባሩ አፍሬአለሁ አንገት የሚያስደፋ ነው። የያዘው ህግ ነው ህግ የሚወስነውን ይወስን ። እውነታን አፈላልገው ለዚህ ሃቅ ላበቁኝ የህግ አካላት ግን ምስጋናዬ ከፍተኛ ነው ስትል ሃሳቧን ሰጥታለች።

 በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ ዛሬ ምሳ ሰዓት አካባቢ ከጁመዓ በኋላ ከመስጊድ ሲወጡ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን  ምንጮች ገልጸዋል።በ...
05/07/2024


በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ ዛሬ ምሳ ሰዓት አካባቢ ከጁመዓ በኋላ ከመስጊድ ሲወጡ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ምንጮች ገልጸዋል።
በዚህ የተነሳ በከሚሴ ከተማ የባጃጅ እንቅስቃሴ ታግዷል ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

አብይ አህመድ እኔን መፈንቀል አትችሉም አሉ❗Gish Media ግሽ ሚዲያምክንያቱን ሲያስረዱም "ወታደር ስለነበርኩና ከዛ ተምሬ ተቋማትን ስለሰራሁ ነው" ብለዋል።በእርሳቸው የውትድርና ዘመን የ...
04/07/2024

አብይ አህመድ እኔን መፈንቀል አትችሉም አሉ❗
Gish Media ግሽ ሚዲያ
ምክንያቱን ሲያስረዱም "ወታደር ስለነበርኩና ከዛ ተምሬ ተቋማትን ስለሰራሁ ነው" ብለዋል።
በእርሳቸው የውትድርና ዘመን የታሰበ የመፈንቅለ መንግስት እንቅስቃሴ እንደነበርና እንዴት ለትምህርት እንዳበቃቸው ግን አላብራሩም።
በተያያዘ ዜና ዛሬ የምክር ቤቱ ስብሰባ ከመካሄዱ በፊት ትናንት በፓርላማው የሚገኙ ቢሮዎች እና ዙሪያው ባልተለመደ መልኩ ከፍተኛ ፍተሻ እንደነበር ከታማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ሰበር ዜና❗የኑሮ ውድነቱ መቀነሱ ተሰማ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት መቀነሱንና ከሌሎች አገሮች የተሻለ መሆኑን ተናገሩ።
04/07/2024

ሰበር ዜና❗
የኑሮ ውድነቱ መቀነሱ ተሰማ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት መቀነሱንና ከሌሎች አገሮች የተሻለ መሆኑን ተናገሩ።

“በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል” - አቶ አበባው ደሳለው፤ የአብን የፓርላማ አባል Gish Media ግሽ ሚዲያበዛሬው የተወካዮች ምክር ቤት መደበ...
04/07/2024

“በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል” - አቶ አበባው ደሳለው፤ የአብን የፓርላማ አባል
Gish Media ግሽ ሚዲያ
በዛሬው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡት 16 የፓርላማ አባላት ሲሆኑ ሁለቱ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች ናቸው። የተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ አባሉ አቶ አበባው ደሳለው፤ መንግስት “የህሊና እስረኞችን ለመፍታት፣ የጅምላ ግድያ እና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማቆም ምን ወስኗል?” ሲሉ ጠይቀዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ኃይሎች ባለፉት 10 ወራት “ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል” ያሉት አቶ አበባው፤ ከጥሰቶቹ ውስጥ “የጅምላ ግድያ” እንደሚገኝበት ተናግረዋል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች “ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል” ሲሉ የፓርላማ አባሉ ተናግረዋል ።

ለዚህ በማሳያነትም በእርሳቸው ምርጫ ክልል ጅጋ፣ በፍኖተሰላም፣ በመርዓዊ፣ በደብረ ኤልያስ፣ በደብረሲና፣ ጎንደር እና ወሎ ተፈጽመዋል ያሏቸውን ግድያዎች ጠቅሰዋል። ጾታዊ ጥቃት እና ድብደባን ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውንም አቶ አበባው አመልክተዋል።

በተለይ በአማራ ተወላጆች ላይ ይፈጸማል ያሉትን “የጅምላ እስር” ጉዳይንም የፓርላማ አባሉ አንስተዋል። አቶ አበባው “ለወራት በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ” ካሏቸው ውስጥ የምክር ቤት አባላት፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና አንቂዎች ይገኙበታል።

“የምክር ቤት አባላትን ስናነሳ፤ የምክር ቤት አባላችን አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኖ መንግስትን ከምዝበራ ያዳነ፣ በሰላማዊ ትግልም በእጅጉ የሚያምን ሰው ነው። አንድ አመት ለሚሞላ ጊዜ በእስር እየማቀቀ ነው ያለው” ሲሉ አቶ አበባው የፓርቲያቸውን የፓርላማ ተመራጭ አስታውሰዋል።

“ሌሎችም በለውጡ ከእርሶ ጋር አብረው የሰሩ፤ እንደ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ካሳው ተሻገር እና አቶ ታዬ ደንደአ ያሉም ‘ለውጡ ስህተት ፈጽሟል፤ በትክክለኛው ጎዳና እየሄደ አይደለም’ ብለው ስለሞገቱ ብቻ ለወራት ታስረዋል” ሲሉም የአብን የፓርላማ አባሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ተናግረዋል።

አቶ አበባው የአማራ ክልል ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑትን የአቶ ሀብታሙ በላይነህ ጉዳይንም በማንሳት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተማጽኖ አቅርበዋል። የአብን አባሉ አቶ ሀብታሙ “ላለፉት አራት ወራት የት እንደገባ አይታወቅም” ያሉት አቶ አበባው፤ ይህን ጉዳይ ቤተሰቡም እኔም ለተለያየ የመንግስት ኃላፊዎች አቤት ብለናል ምላሽ አላገኘንም። ዛሬ እርሶ ምላሽ ይሰጡናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

Address

6 Kilo
Addis Ababa
HORN

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gish Media ግሽ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gish Media ግሽ ሚዲያ:

Share