KOBO TIMES

KOBO TIMES Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from KOBO TIMES, Media/News Company, Addis Ababa.

20/07/2025

እንደ ሀበሻ ግን አቋላጭ ና አሽቃባጭ አለ በዲማው🙄

26/03/2022

የዋግኽምራ አማራ በሐሆኑ ብቻ ከጦርነቱ የተረፋት በረሃብ አለንጋ እየተቀጡ ነው።

20/03/2022

ራያያያያ❤

በመካነሰላም ፖሊሶች በጥይት ተመትቶ ባህር ዳር ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበረው የምስራቅ አማራ ፋኖው ዲሽቃ ተኳሽ አስር አለቃ አረጋ ዘውዱ ህይወቱ አልፏል፡፡ባህርዳር:- መጋቢት 04/2014...
13/03/2022

በመካነሰላም ፖሊሶች በጥይት ተመትቶ ባህር ዳር ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበረው የምስራቅ አማራ ፋኖው ዲሽቃ ተኳሽ አስር አለቃ አረጋ ዘውዱ ህይወቱ አልፏል፡፡

ባህርዳር:- መጋቢት 04/2014 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ

በጠላት የተከበበው የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለመመከት ወደ ትግል የገባው ፋኖ አረጋ ዘውዱ በሚታገልለትና ወገኔ በሚለው የመካነሰላም ፖሊስ በተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አልፏል፡፡

ያኔ የመንግስት አመራርና አጠቃላይ የጸጥታ መዋቅሯ በሜሴጅ መልክት እየተለዋወጠ ሁሉም ለጠላት አሳልፎ ጥሏት የሄደችው መካነሰላም ከተማ ከጠላት ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው ካቆዩአት ጀግኖች አንዱ ዘርፈው ሊሸሹ በነበሩት የብአዴን ነውረኞች መገደሉ ተረጋግጧል፡፡

የመካነሰላም ከተማ ነዋሪ ብቻ ሳይሆን … መላው የአማራ ሳይንት እና የቦረና ሳይንት ህዝብ በነቂስ ወጥተህ የጀግናህን ሽኝት በጀግና ማዕረግ ፈፅመህ ለጀግናህ ክብርህን ለብአዴን ነውረኞች ቁጣህን አሳይተህ በሰላም ወደቀየህ ተመለስ።
ሌላውን ከጀግናው የአስከሬን ሽኝት በኋል ምከርበት።
ሀብታሙ አያሌው

13/03/2022

የአማራ ሕዝብ ራሱን ለትግል ያዘጋጅ!
*****
የአማራ ብሔርተኝነት ስትራቴጂክ ስህተት የኖኅ መርከብ ልሁን ማለቱ ነው። ብሔርተኝነቱ አይጡንም ጉርጡንም አግተልትሎ መጓዙ የእንፉቅቅ እንዲራመድ አድርጎታል። ሕዝባችንን ለሥርዓታዊና መዋቅራዊ ባርነት አሳልፈው የሰጡ አካላትን «ውሻም ቢሆን የራሴው ውሻ ነው» በሚል አቅፎ መጓዙ ጠውሌ ስህተት ነበር። ያ ስህተት የብሔርተኝነቱን ኦርጋኒክ መሪዎችና የለውጥ አንቀሳቃሾች ዞሮ እስኪበላ ድረስ መታገሳችን ደግሞ ብርቱ ዋጋን እያስከፈለን ይገኛል።

በነገራችን ላይ በፋኖ ላይ እየተደረገ ያለው ዘመቻ በገዥው ፓርቲ ሰዎች ብቻ የሚመራ አይደለም፤ በአካልም በስምም የምናውቃቸው፥ ሕዝባችን በነፃ አውጭነት ተስፋ የሚያደርግባቸው የፖለቲካ መናፍቃንም ከጉትጎታ እስከ ውሳኔ ሰጪነት አብረው የተሳተፉበት እንጂ! ትግሉ ከራስ ወንድሞችና እህቶች ጋር በመሆኑ አድካሚ ቢሆንም ዳግም ስህተት ሳንፈጽም በድል እንወጣዋለን። ታላቁ የአማራ ሕዝብ ሆይ፥ ራስህን ለትግሉ አዘጋጅ።

ሕዝብን የናቀ፥ ወደቀ!

ክርስቲያን ታደለ

አብን የኦነግን ካርታ ፎቶ ኮፒ አድርጎ መንቀሳቀስ ባይጀምርም... ከአቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ከዶክተር ደሳለኝ ጫኔና ከዶክተር ቴዎድሮስ... ውጭ ያሉት አብዛኞቹ አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካ...
13/03/2022

አብን የኦነግን ካርታ ፎቶ ኮፒ አድርጎ መንቀሳቀስ ባይጀምርም... ከአቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ከዶክተር ደሳለኝ ጫኔና ከዶክተር ቴዎድሮስ... ውጭ ያሉት አብዛኞቹ አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካዳሚዎች ሆነዋል። አብዛኞቹ አመራሮችም የአማራን የሕልውና ጥያቄ በቤት እና መኪና ቀይረው ትግላቸውን አጠናቅቀዋል።

ስለሆነም ፋኖዎች ቢገደሉ፣ አማራዎች ቢፈናቀሉ፣ አሸባሪዎች ዳግም ወረራ ቢፈጽሙ፣ የአማራ ሕዝብ ባልፈጸመው ጥቃት ቢወገዝ.... መግለጫ እንኳን ለማውጣት ልምምጥ የሚያስፈልጋቸው ዳተኞች ሆነዋል።

እናም የአማራን የመኖር ያለመኖር ጥያቄ በፍርፋሪ የሸጡ የአብን አመራሮችን አስወግዶ በአዲስ አመራር በመተካት ፓርቲውን ማስተካከል ካልተቻለ ከዚህ በኋላ አብን ከተባለ ጥቅመኛ ፓርቲ የሚጠበቅ ድል ቀርቶ ቅንጣት ታክል ትግል አይኖርም።

አሳዬ ደርቤ

13/03/2022

ከትግራይ ክልል ወደ አማራ ክልል ቆቦ እየገቡ ስላሉ ሰዎች በውስጥ ካደረሳችሁኝ በርካታ አስተያየቶች መካከል ሶስቱ እንደሚከተለው ቀርበዋል።👇





25/10/2021

ሀይቅ ትጣራለች እንድረስላት❗️
➖➖➖➖➖➖➖➖
ሀይቅ በወራሪው ጁንቴ ከተያዘች 4 ቀን ሆናት፣ ይሄ ንግድ ባንክ አጠገብ ፎቶ ተነስተው ካላየ በስተቀር ከተማ ያልተያዘ ለሚመስለው ገልቱ አይገባውም: ብዙ ሰው እየሞተ ነው: ዋሄሎ፣ ቀጤ፣ አሙሞ፣ ዳውቻ፣ ጎበያ እና ሌሎችንም የገጠር አከባቢዎች ነፃ ሳይወጡ ሀይቅ ነፃ አቶጣም፡ ቡዙ ኪሳራ ከመድረሱ በፊት እንፍጠን❗️
( )

ለማሻ ከተማ ነዋሪወች  በሙሉ!!================እስካሁኑ ሰዓት ባለን መረጃ መሰረት አንድም የጠላት ሀይል የበሽሎ ድልድይን ያለፈ የለም በተሳሳተ መረጃ ቤት ንብረታችሁን ለሌባ ለቃች...
25/10/2021

ለማሻ ከተማ ነዋሪወች በሙሉ!!
================
እስካሁኑ ሰዓት ባለን መረጃ መሰረት አንድም የጠላት ሀይል የበሽሎ ድልድይን ያለፈ የለም በተሳሳተ መረጃ ቤት ንብረታችሁን ለሌባ ለቃችሁ አትሂዱ!
#1ኛ.በያላችሁበት ቦታ ተረጋግታችሁ ሀብትና ንብረታችሁንና አካባቢያችሁን ጠብቁ
#2ኛ.የከተማችን ወጣቶች በየቁልፍ በሩና በመግቢያ መንገዶች ሁሉ ፀጉረ ልውጦችን ተከታተሉ
#3ኛ.የጠላት ሀይል ባሰፈሰፈበት የተሬ አካባቢ የተሳካ የድሮን ድብደባ ተካሂዷል።
#4ኛ በጉና ግንባር ተጨማሪ ሀይል እየጠየቅን መሆኑን አውቃችሁ የሚፈጠሩ አዳድስ ክስተቶች ካሉ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

#የወረዳው ወቅታዊ ጉዳዮች ኮማንድ ፓስት!!

የተደበደብኩበት እውነተኛ ምክንያት! (እስከንድር ነጋ)" ከጎኔ ለቆማችሁት ሁሉ፣ ልባዊ ምስጋና ይድረሳችሁ። "እስክንድር ነጋ፤የኅሊና እስረኛ፤ ቂሊንጦ፤ አዲስ አበባለሰሚው ግራ እንደሚገባ እረ...
25/10/2021

የተደበደብኩበት እውነተኛ ምክንያት! (እስከንድር ነጋ)

" ከጎኔ ለቆማችሁት ሁሉ፣ ልባዊ ምስጋና ይድረሳችሁ። "

እስክንድር ነጋ፤
የኅሊና እስረኛ፤
ቂሊንጦ፤ አዲስ አበባ

ለሰሚው ግራ እንደሚገባ እረዳለሁ። በእኔ ዕድሜ ተደብዳቢም ሆነ ደብዳቢ የሚባል ሰው አያምርበትም። መደባደብ የሕፃናት ዘመን መለያ ነው። ግን እኮ በአንድ እጅ ማጨብጨብ አለመቻሉም ሌላ እውነታ ነው። በየትኛውም ዕድሜ ቢሆን፣ የግድ መደባደብ የሚፈልግ ካለ፣ ደብዳቢና ተደብዳቢ ይኖራል። ምንም ማድረግ አይቻልም። በዚህኛው ትዕይንት ደግሞ፣ አስደብዳቢም የተጨመረበት ስለሆነ፣ ነገሩን አወሳስቦታል።

ተደብዳቢ የሆንኹበትን ሂደት አልገባበትም። የአስደብዳቢዎቼ ወጥመድ ውስጥ መዘፈቅ ነው የሚሆነው። ለመማታት መጀመሪያ የሰነዘርሁት እኔ እሆናለሁ ብሎ የሚያስብ ይኖራል ብዬ አልገምትም። አውዱን ለማስቀመጥ ይህ ይበቃል። ሊደበድበኝ አስቀድሞ ስለሰነዘረብኝ በዙ ማለት ከንቱ ልፋት ነው የሚሆነው። ታላቁ መፅሐፍ እንደሚለው፣ የሚያደርገውን አያውቅምና፣ ወደ ቀናው መንገድ እንዲመለስ ፈጣሪ ይርዳው። በዚህ ልለፈው።

ከደብዳቢው በስተገርባ ስላሉት አስደብዳቢዎቼ ግን፣ ቢያንስ ትንሽ ማለት አለብኝ። ለሕዝባችን ጠቃሚ መረጃ አለኝ።

በዚህ ጊዜ፣ ሀገራችን የሞትና ሽረት ትንቅንቅ ላይ ናት። ትንቅንቁን እነ ዐብይ አህመድ ካሸነፉ፣ ኢትዮጵያ በኦ.ህ.ዴ.ድ. በሚመራ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ሥር ሆና እንደ ሀገር ትቀጥላለች።

በአንፃሩ፣ ሕወሓት ካሸነፈ፣ ሁለት አማራጮች ይኖራሉ። ሕወሓት በቀዳሚነት በሚፈልገው አማራጭ፣ ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ወደ አራትና አምስት ሀገራት ትበተናለች። ይህ የማይሆን ከሆነ፣ እንደ ቦዝኒያ ትሆናለች። ፈረንጆቹ እንደ ቦዝኒያ መሆንን "ቦዝንፊኬሽን - Bosnification" ይሉታል። ይህ ማለት፣ ማዕከላዊ መንግሥቱ በይፋ የለም ባይባልም፣ በተግባር ግን እንደ ሌለ የሚቆጠር ይሆናል። እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ለእኛ እንግዳ አይደለም። በታሪካችን "ዘመነ መሳፍንት" በሚለው መጠሪያ እናውቀዋለን።

ጉዳዩ ይህንን ያህል ክብደት እያለው፣ እንደ እኔ ፖለቲካ ውስጥ ያለ ሰው ዝም ማለት አይችልም። ፖለቲካ ያለ ሀገር ሊኖር አይችልም። ሁለቱም የሕወኃት መንገዶች ሀገር የሚያጠፉ ናቸው።

ግን፣ ይህ ማለት፣ ኢትዮጵያን የምንፈልጋት ሰዎች ለእነ ዐብይ ጭፍን ድጋፍ መስጠት አለብን ማለት ነው ወይ? እኔ፣ "አይደለም፤ ድጋፋችን ጭፍን መሆን የለበትም" ባይ ነኝ። በተለይ፣ እነ ዐብይ ጦርነቱን መምራት እንዳቃታቸው በግልፅ እየታየ ባለበት በዚህ ጊዜ።

ይህ አቋሜ ነው ደብዳቢ እንዲላክብኝ ያስደረገው። ለአሁኑ ይህን ብቻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይወቅልኝ። ሌላውን ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

ለጊዜው አጥንቴ ተሰብሯል። በዚህ ብቻ በማለፉ ቸሩ መድኃኒዓለምን አመሰግነዋለኹ። ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ጥቃት ማድረስ ይከብዳቸዋል።

ከጎኔ ለቆማችሁት ሁሉ፣ ልባዊ ምስጋና ይድረሳችሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠበቅ፣ ይባርክ!

"ወደ ወሎ መዝመት ኢትዮጵያን የመታደግ ጉዳይ ነው!" የኮ/ል ደመቀ  ዘውዱ መልዕክት➖➖➖➖ አሸባሪውንና ወራሪውን ኃይል ባህሪን ጠንቅቀን እናውቀዋለን። በደረሰበት ቦታ ሁሉ እስኪያልፍ ድረስ ...
24/10/2021

"ወደ ወሎ መዝመት ኢትዮጵያን የመታደግ ጉዳይ ነው!"

የኮ/ል ደመቀ ዘውዱ መልዕክት
➖➖➖➖

አሸባሪውንና ወራሪውን ኃይል ባህሪን ጠንቅቀን እናውቀዋለን። በደረሰበት ቦታ ሁሉ እስኪያልፍ ድረስ "ከእናንተ ጋር ችግር የለብኝም" ቢልም ሕዝብን ከማጥፋት ወደኋላ አይልም። ሕዝባችን ላይ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ያደረሰውን ግፍና በደል እናውቀዋለን። አሁኑ በተያያዘው የጦር ወረራው በየደረሰበት ቦታ ገና እግሩን ከመትከሉ ነው ሕዝብ እየጨፈጨፈ ያለው። በዚህ ወቅት ወሎ ላይ ያለ የሌለ ኃይሉን ይዞ ለጦር ወረራ ዘምቶብናል። ለዚህ መድሃኒቱ እሱ በጀመረው መንገድ መዝመት ነው። ይህ ወረሪ ኃይል እየፈጸመ ያለውን መጠነ ሰፊ ወረራ መላ ኢትዮጵያውያን በሙሉ አቅማቸው ሊመክቱት ይገባል።

ጀግናው የወሎ ሕዝብ ከቦታው ባለመልቀቅና የጠላትን የእንቅስቃሴ መረጃዎች ለወገን ጦር በመስጠት፣ ምቹ ሁኔታ ሲያገኝ ጠላትን በጋራ በማጥቃት ሊያግዝ ይገባል። ‹ይህ ወራሪ ኃይል መጣ› ብሎ መሸሸ የለበትም። ራያ ላይ የሸሸውን ወልዲያ ላይ ዝም አይለውም። ወልዲያ ላይ የሸሸውን ደሴ የመግባት ዕድል ቢያገኝ ዝም አይለውም። ስለሆነም ሕዝባችን አንድ ልብ መካሪ፤ አንድ ቃል ነጋሪ ሁኖ እንዲመክት ወገናዊ ጥሪየን አቅርባለሁ፡፡

በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የምትኖሩ የዐማራ ልጆች እንዲሁም መላ ኢትዮጵያውያን በወሎ ግንባር ያሰፈሰፈውን ወራሪ ኃይል በመመከት ወሎ ታሪካዊ የፍፃሜው ቦታ እንዲሆን ለማድረግ ርብርብ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ንቅናቄ መሀል ሀገር ያለውን ኢትዮጵያዊ ኃይል ያካተተ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ አሁን የሚጠበቀው ከሌላ ቦታ ወደ ወሎ መዝመት አንጅ ከወሎ መውጣት አይደለም፡፡

መላው የአማራ ሕዝብ ደመኛ ጠላቱ የሆነው ትህነግ ወሎ ላይ የከፈተውን የጦር ወረራ በማክሸፍ ህልውናውን ማፅናት አለበት፡፡

መዝመት የሚችል ይዝመት። ገንዘብ ያለው በገንዘብ ያግዝ። መኪና ያለው መኪናውን ለዘመቻ ያውል። ሁሉንም አቅም አሟጦ በመጠቀም ወራሪው ኃይል ወሎ ላይ ግብአተ መሬቱ ሊፈፀም ይገባል፡፡

አሸባሪውና ወራሪው ኃይል የፈፀመው ወረራ የአማራ ጉዳይ ብቻ አይደለም። በመላ ኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመ ነው። በዜጎቿና በክብሯ አልፎም በሉአላዊነቷ ላይ የተቃጣ በመሆኑ ወደ ወሎ መዝመት ኢትዮጵያን የመታደግ ጉዳይ ነው፡፡ ወራሪው ኃይል ከሁሉም አካባቢ ተጠራርቶ ሲወረን እኛም ከመላ ኢትዮጵያ ተጠራርተን ወደ ወሎ መዝመት አለብን። በተባበረ ክንድ ወራሪውን ኃይል እስካልደመሰሰን ድረስ እንደ አማራም፣ እንደ ኢትዮጵያም ሰላም ማግኘት አንችልም።

ጥንቃቄ ይደረግ❗️➖➖➖➖➖ከሰአታት በፊት ማንነታቸው ያልታወቁ 28 ግለሰቦች በሎጊያ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጬ ነበር: ይህም ዜና በሌሎች ሚዲያዎችን ሲዘዋወር ታዝቤለሁ: አሁን ባደ...
23/10/2021

ጥንቃቄ ይደረግ❗️
➖➖➖➖➖
ከሰአታት በፊት ማንነታቸው ያልታወቁ 28 ግለሰቦች በሎጊያ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጬ ነበር: ይህም ዜና በሌሎች ሚዲያዎችን ሲዘዋወር ታዝቤለሁ: አሁን ባደረኩት ማጣራት ግለሰቦቹ ከራያ ቆቦ መተው ብር ከደሴ እና ከኮምቦልቻ አውጥተው ወደ ራያ ቆቦ የሚመለሱ የራያ ቆቦ ተወላጆች መሆናየውን ሰምቻለሁ፣ ብራቸው እንዲመለስላቸውና ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ለሚመለከተው አካል አሳስባለሁ❗️
( )
Afarovich mohammed

Address

Addis Ababa

Telephone

+251925020490

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KOBO TIMES posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to KOBO TIMES:

Share