PRESS Ethiopia

PRESS Ethiopia News

16/04/2023

#ትንሳኤ

እንኳን አደረሳችሁ !

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።

በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።

የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን !

መልካም በዓል !

16/04/2023

የሱዳን ነገር ከቁጥጥር እየወጣ ይሆን ?

የአል-ሱዳኒ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ያሲር አብዱላህ ሀገሪቱ ወደ ከፋ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራች እንደሆነ አስጠንቅቋል።

በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው ብሏል።

እስር በርስ የሚደረገውን ግጭት ለማስቆም በሰራዊት አመራሮች በኩል ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ከሌለ ሁኔታው እጅግ ወደ ከፋ ሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራ ነው ሲል ገልጿል።

ይህ ሁኔታ በአጠቃላይ ሀገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን የገለፀው ያሲር አብዱላህ በዚህ ውስጥ ማንም አሸናፊ የለም ብሏል።

ዛሬ ካርቱም ውስጥ በሱዳን ጦር እና RSF (ፈጥኖ ደራሽ) መካከል የከፋ የከተማ ውስጥ ውጊያ ጭምር ሲካሄድ ነበር።

ሁለቱም ወገኖች በየፊናቸው ድል እየተቀዳጁ መሆኑንና አንዱ የአንዱን መሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተፈላለጉ መሆኑን በሚያወጧቸው መግለጫዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።

በጄነራል አል - ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር በሄሜቲ የሚመራውን RSF " አማፂ " ቡድን ብሎ በይፋ ጠርቶታል። ዳጋሎም (ሄሜቲ) ተሸሽገው የሚገኙ በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኛ ናቸው በማለትም ማንኛውም ዜጋ ከእሳቸው ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው አሳስቧል።

ጦሩ RSF እስካልፈረሰ ድረስ በምንም ለድርድርም ይሁን ለንግግር እንደማይቀመጥ አስገንዝቧል።

በጄነራል ሄሜቲ የሚመራው RSF በበኩሉ ድል እየተቀዳጀ መሆኑንና " ወንጀለኛ ናቸው " ያላቸውን አል ቡርሃንን #ለማሰር እያሳደዳቸው መሆኑን ገልጿል ያሉበትንም ደርሼበታለሁ ብሏል፤ ቡርሃን ግራውንድ ስር #ተደብቀው የህዝብ ልጆችን እንዲዋጉ እየገፋፉ ነው ብሏል።

16/04/2023



የግብፅ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጋሪብ አብደል ሃፌዝ ፥ በሱዳን ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን ነው ብለዋል።

ቃል አቀባዩ ሱዳን ውስጥ ልምምድ የሚያደርጉ የግብፅ ሃይሎች ስለመኖራቸው ተናግረው ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ የቃል አቀባዩ ማብራሪያ የተሰጠው ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመሩት RSF (ፈጥኖ ደራሽ) በሰሜን ሱዳን ሜሮዌ " ውስጥ የግብፅ ወታደሮች ' #መማረካቸውን ' በቪድዮ ካሳየ በኃላ ነው።

16/04/2023



" የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ሁሌም ቢሆን አዲስ አበባ በሯ ክፍት ነው " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ኢትዮጵያ በሱዳን የተከሰተውን ግጭት በትኩረት እየተከታተለችው እንደምትገኝ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የሱዳን ወንድማማች ፓርቲዎች ወደ ሰላም ንግግር እንዲመለሡ ጥሪ ባቀረቡበት የአረብኛ ቋንቋ መግለጫ ነው።

ዶ/ር ዐቢይ በመልዕክታቸው የሱዳን ወንድማማች ፓርቲዎች ከግጭት አባባሽ ድርጊቶች ተቆጥበው ፤ የተፈጠረውን ግጭት በውይይት እንዲፈቱ እና ግጭቱን እንዲያረግቡ የሰላም ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስትም የተፈጠረውን ግጭት በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን አሳውቀዋል።

የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት እና የአፍሪካን ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ ለመስጠት አዲስ አበባ ሁሌም ቢሆን በሯ ክፍት እንደሆነ ገልጸዋል።

16/04/2023



የRSF መሪ የሆኑት ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሱዳን ጦር አዛዥ የሆኑትን አብዱል ፈታህ አል ቡርሃንን " ወንጀለኛ " ናቸው ብለዋቸዋል።

የመሩትን ጦርም በመፈንቅለ መንግስት ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።

ሄሜቲ ወታደሮቻቸው ወደ ግጭት ተገደው መግባታቸውን አመልክተዋል።

የሱዳን ጦር አዛዥ ሀገሪቱን እንዳወደመ የገለፁት ዳጋሎ ጦራቸውን እያሸነፈ መሆኑንና ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍኑ ፤ ያለው ሁኔታም በቅርቡ እንደሚቋጭ ተናግረዋል።

የጦር ሃይሉ ዋና አዛዥ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ለአልጀዚራ እንደተናገሩት RSF በጦር ኃይሉ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከጠዋቱ 9 ሰዓት ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። የአልጀዚራ ሂባ ሞርጋን "እና በሁለቱ ወገኖች መካከል ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ የሆኑት ያኔ ነበር" ስትል ተናግራለች።

በሌላ በኩል ፤ የጦር ሃይሉ ዋና አዛዥ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል፤ RSF በጦር ኃይሉ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ዛሬ ጥዋት ጥቃት መሰንዘራቸውን ተናግረዋል።

በሁለቱ ወገኖች መካከል ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ የሆኑት ያኔ እንደነበር ተነግሯራ።

በሱዳን ግጭቶች አሁንም መቀጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል። ይህን ተከትሎ ጎረቤቷ ቻድ ።

16/04/2023



በሱዳን ካርቱም ግጭቱ አሁንም መቀጠሉ ታውቋል።

በተለይ በማዕከላዊ ካርቱም ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ የተመላከተ ሲሆን ግጭት የተባባሰው በሪፐብሊኩ ቤተ መንግስት እና በአል-ማክ ኒምር ድልድይ አካባቢ ነው ተብሏል።

ኤርፖርቶችን ለመቆጣጠር አሁንም ድረስ ውጊያ እየተደረገ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል የሱዳን ጦር አየር ኃይል ፤ " የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎችን ዋና ዋና ቦታዎችን በአየር ላይ ማጥቃት መቀጠሉ ተሰምቷል።

ሌ/ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል እስካሁን ያላንቀሳቀሱት የጦር ቤዝ እና ጥሩ የሚባል ተጠባባቂ ኃይል እንዳላቸው አመልክተዋል።

ቡርሃን ካርቱም የገባው ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ግጭቱ/ ጦርነቱ በዚህ ከቀጠለ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ካርቱም ጦራቸውን እንደሚያስገቡ አስጠንቅቀዋል።

በሱዳን እየሆነ ባለው ነገር በርካቶች ስጋት ላይ የሚገኙ ሲሆን እስካሁን በግጭቱ ምክንያት 3 ሲቪሎች መገደላቸው ታውቋል።

የሳዑዲ አረቢያ እና የግብፅ አየር መንገዶች ከ/ወደ ሱዳን የሚደረጉ በረራዎችን ሰርዘዋል።

ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ሀገራት ነገሮች እንዲረግቡ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

16/04/2023

ካርቱም ውስጥ ምን እየሆነ ነው ?

በሱዳን በአገሪቱ ጦር ሠራዊት እና በተጽእኖ ፈጣሪ ነው በሚባለው " ፈጥኖ ደራሽ ሚሊሻ " መካከል በካርቱም ውጊያ ተቀስቅሶ ከተማው በቶክስ እየተናወጠ ነው።

ዛሬ በመዲናዋ ከፍተኛ የተኩስ እና ፍንዳታ ተሰምቷል።

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የካርቱም ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ተቆጣጥሪያለሁ ያለ ሲሆን፤ የብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን ለመቆጣጠር የተኩስ ልውውጥ እየደረገ መሆኑን ከሰዓታት በፊት አሳውቋል።

ፍጥጫው እንዴት ጀመረ ?

በሁለቱ ኃይሎች መካከል ለተፈጠረው ፍጥጫ ምክንያት በወታደራዊ አስተዳደር ስር የቆየችውን ሱዳን ወደ ሲቪል መንግሥት ለማሻገር በቀረበው ሃሳብ የተነሳ ነው።

ሄምቲ በሚለው ቅጽል ስማቸው በሚታወቁት በጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወደ አገሪቱ ጦር ስለሚቀላቀልበት ሁኔታ አንዲሁም ኃይሉን ማን ይመረዋል በሚለው አለመግባባት ተፈጥሮ ባለፉት ቀናት ውጥረት ሰፍኖ ነበር።

ሁለቱ አካላት ምን አሉ ?

ዛሬ የተኩስ ድምጽ መሰማት የጀመረው በማዕከላዊ ካርቱም ውስጥ በሚገኘው የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት አቅራቢያ ነበር።

(አርኤስኤፍ) የሚባለው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ምን አለ ?

በዋና ከተማዋ በስተደቡብ ከሚገኙት ካምፖቹ መካከል አንዱ ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረበት ገልጿል።

የሱዳን ጦር ሠራዊት ምን አለ ?

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ተዋጊዎች የጦር ኃይሉን ዋና መ/ቤት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው ብሏል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተዋጊዎች በካርቱም እና በሌሎች የሱዳን ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ በርካታ የጦር ሠራዊት ካምፖች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ብላል።

ግጭቶች እየተካሄዱ መሆኑ የገለፀው ጦሩ ፤ ሠራዊቱ አገሪቱን የመጠበቅ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ብሏል።

ሱዳን ...

ከሁለት ዓመት በፊት በሱዳን ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ በኋላ የጦር ጄኔራሎች ሉዓላዊ ምክር ቤት የሚባል አካል አቋቁመው አገሪቱን እየመሩ ይገኛሉ።

አርኤስኤፍ የተባለው ፈጥኖ ደራሽ ሚሊሻ በኃያሉ ጄኔራል እና የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራ ነው።

የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት የሆኑት ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሐን ደግሞ የአገሪቱን ጦር ኃይል ይመራሉ።

ሱዳንን ወደ ሲቪል መንግሥት ለማሸጋገር የቀረበው ዕቅድ የአርኤስኤፍ ኃይሎችን ከአገሪቱ ጦር ሠራዊት ጋር በማዋሃድ የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ከስምምነት ሳይደረስበት ቆይቷል።

አርኤስኤፍ ውህደቱ በአስር ዓመታት እንዲዘገይ ፍላጎት ያለው ሲሆን፣ የአገሪቱ ሠራዊት ግን በሁለት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ይፈልጋል።

በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ውጥረት በተካረረበት ጊዜ አርኤስኤፍ ኃይሎቹን ሐሙስ ዕለት ሜሮዌ ውስጥ ባሉ የመንግሥት ኃይሎች አቅራቢያ አሰማርቷል።

ጄኔራል ቡርሃን በሚቋቋመው ሲቪል መንግሥት ውስጥ የሚመሠረተውን የተዋሃደ የአገሪቱን ጦር ማን መምራት አለበት በሚለው ጥያቄ ዙሪያ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ከጄኔራል ዳጋሎ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸው ነበር።

(ቢቢሲ)

16/04/2023

ጠቅላይ ኢተማዦር ሹሙ ምንድነው ያሉት ?

የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ኢተማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፥ " ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት የለም " ብለዋል።

ይህንን ያሉት የክልል ልዩ ሃይሎችን በፌዴራልና የክልል የጸጥታ ተቋማት መልሶ የማደራጀት ስራ የመከላከያ ጀነራሎች፣ ፌዴራል ፖሊስ እና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ሲገመገም ነው።

ፊልድ ማርሻሉ ምንድነው የተናገሩት ?

" የክልል ልዩ ሃይሎች እንደገና በመደራጀታቸው ህብረ ብሄራዊ ጠንካራ የጸጥታ ተቋም ይገነባል።

የክልል ልዩ ኃይሎች አደረጃጀት ህጋዊ አለመሆን፣ በክልሎች መካከል እንደ ስጋት መተያየት እንዲሁም ችግሮችን በሃይል ለመፍታት የሚደረገው እንቅስቃሴ አደረጃጀቱን ለመቀየር አስገድዷል።

በአሁኑ ወቅት በሁሉም ክልሎች መልሶ የማደራጀት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀትና መዋቅር የለም።

በመሆኑም የጸጥታ መዋቅሩ መከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ ሲሆን በክልል ልዩ ኃይሎች ስም ተልዕኮም ሆነ ግዳጅ የሚቀበል ኃይል አይኖርም።

ከዚህ በኋላ በመረጡት አደረጃጀት መሰረት ሁሉንም ወደ ተመደቡበት የማጓጓዝና ወደ ስልጠና የማስገባት ስራ ይከናወናል። "

24/09/2022
 እስር ላይ ከነበሩ ጋዜጠኞች መካከል እስካሁን ስይፈታ የቆየው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ዛሬ ረቡዕ ከእስር መፈታቱ ተገልጿል። [ https://t.me/tikvahethiopia/65538 ]" ተራራ...
06/04/2022



እስር ላይ ከነበሩ ጋዜጠኞች መካከል እስካሁን ስይፈታ የቆየው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ዛሬ ረቡዕ ከእስር መፈታቱ ተገልጿል። [ https://t.me/tikvahethiopia/65538 ]

" ተራራ ኔትዎርክ " የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ አቋቁሞ ሲሰራ በነበረበት ወቅት ታህሳስ 1 ቀን የታሰረው ጋዜጠኛ ታምራት ከ118 ቀናት እስር በኃላ መፈታቱን የሚሰራበት ሚዲያ አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ታምራት ከታሰረ በኃላ በተደጋጋሚ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን በ50 ሺህ ብር ዋስ ነው ከእስር የተፈታው።

ከዚህ ቀደም ጋዜጠኛ መአዛ መሃመድ፣ ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት ኢያስፔድ ተስፋዬ ፣ ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ፣ የአሶሴትድ ፕረስ (AP) ጋዜጠኛ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ ከእስር መፈታታቸው ይታወቃል።

 የተባበሩት መንግታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ በሪፖርቱ ከጥቂት ቀናት በፊት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል የተላከው የህክምና ቁሳቁስ መቐለ ቢደርስም አጋር አካላት በነዳጅ እጥረት ም...
19/02/2022



የተባበሩት መንግታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ በሪፖርቱ ከጥቂት ቀናት በፊት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል የተላከው የህክምና ቁሳቁስ መቐለ ቢደርስም አጋር አካላት በነዳጅ እጥረት ምክንያት ወደ በክልሉ ወዳሉ ጤና ተቋማት መላክ እና ማከፋፈል አልቻሉም ሲል ገልጿል።

በተለይም ከ800 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችን ወዳስጠለለው የሰሜን ምእራብ ዞን ማድረስ አልተቻለም። በዞኑ ከአጠቃላይ የውስጥ ተፈናቃይ 1.8 ሚሊዮን 44 % ይሸፍናል ሲል አመልክቷል።

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግን የተነሳውን የነዳጅ እጥረት ቅሬታ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል።

የኮሚሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ደበበ ዘውዴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃል "መድሃኒቱን መቐለ ያስገባው አጋር አካል መድሃኒቱን የሚያጓጉዙበት ነዳጅ ያጣል ተብሎ አይታሰብም" ብለዋል።

አቶ ደበበ ፤ " ህወሃት ከኮምቦልቻ የዘረፈው ነዳጅ በእራሱ ብዙ ነው። በመሆኑም ድጋፉን ለማጓጓዝ የነዳጅ ችግር ገጥሞናል እየተባለ የሚነሳው ጉዳይ በምክንያትነት ማቅረቡ ውሃ የሚቋጥር አይደለም " ሲሉ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ እስካሁን ባለው ሂደት “ኢንተርናሽናል ኮሙኒቲ ኦፍ ሬድ ክሮስ”፣ “ዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ”፣ “ፕላን ኢንተርናሽናል”፣ የዓለም ጤና ድርጅት፤ “ሴቭ ዘ ቺልድረን” እና “ዩኒሴፍን” ጨምሮ 8 ያህል ተቋማት ወደ ትግራይ ክልል መድኃኒት ማስገባታቸው ተረጋግጧል ብሏል።

ባለፈው ሳምንት በ“ኢንተርናሽናል ኮሙኒቲ ኦፍ ሬድ ክሮስ”፣ “ዎርልድ ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን”፣ “ዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ” አማካኝነት 41 ሜትሪክ ቶን መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች መቐለ መድረሱን አሳውቋል።

ተጨማሪ 107 ሜትሪክ ቶን መድኃኒቶች ለማድረስ ዝግጅት መደረጉንና የካርጎ በረራ እየተጠበቀ መሆኑን ገልጿል።

 በከባድ መሣሪያ ጥቃት 10 የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸውን ተሰማ።ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት የአፋር ክልል ነዋሪ የሆኑት አቶ ሁሞ ኢብራሂም ከቀናት በፊት በተፈጸመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት...
19/02/2022



በከባድ መሣሪያ ጥቃት 10 የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸውን ተሰማ።

ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት የአፋር ክልል ነዋሪ የሆኑት አቶ ሁሞ ኢብራሂም ከቀናት በፊት በተፈጸመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ሚስታቸውንና 5 ልጆቻቸውን አጥተው እጅግ ከባድ ሐዘን ውስጥ እንደሚገኙ ቢቢሲ ዘግቧል።

ቢቢሲ በጎ ፈቃደኞችንና ከአካባቢው የወጡ ሰዎችን በማነጋገር በሰራው ዘገባ ባለፈው ማክሰኞ የካቲት 8 ምሽት በተፈፀመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት 10 የአንድ ቤተሰብ አባላት ተገድለዋል።

በጥቃቱ 10 የቤተሰብ አባሎቻቸው የተገደሉባቸው አቶ ሁሞ እና ቤተሰባቸው ይኖሩ የነበረው 'አዳ' የምትባል ትንሽ ከተማ ነበር።

ከተማዋ ከበርሃሌ 15 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ እንደሆነች በሰመራ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ሁሞ የቅርብ ዘመድ አቶ ያሲን ከድር ገልፀው አጠቃላይ ዘመድ በከባድ ሐዘን ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።

በጥቃቱ ልጆቻቸውን ይዘው በመሸሽ ላይ ከነበሩት የቤተሰብ አባላት መካከል 5 ህጻናት፣ እናት፣ የእናት እናት [አያት]፣ የእናት ወንድምና የአባት እህት 2 ልጆች መሆናቸው ተገልጿል።

አባወራው አቶ ሁሞ ቀድመው ከአካባቢው ተፈናቅለው ወጥተው ስለነበር በቤተሰባቸው ላይ ከደረሰው አደጋ ሊተርፉ ችለዋል። ሙሉ ቤተሰባቸውን ያጡት አባት ሐዘኑን ሊቋቋሙ በማይችሉት ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

"ምግብ አይበሉም። እንደ ድንገት የወረደባቸውን መዓት መቋቋም አልቻሉም። የሃይማኖት አባቶች እያጽናኑዋቸው ነው" ሲሉም ከባድ የሃዘን ስሜት ላይ መሆናቸውን አቶ ያሲን ተናግረዋል።

ቢቢሲ አቶ ሁሞን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም በደረሰባቸው መሪን ሐዘን ምክንያት ከማንም ጋር እንደማይነጋገሩ ዘመዶቻቸው መግለፃቸውን በዘገባው ጠቅሷል።

ከሟቾች በተጨማሪ 13 ሰዎች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸው ዱብቲ ሆስፒታል ይገኛሉ።

Address

Bole
Addis Ababa
FOLDER

Telephone

+251941028973

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when PRESS Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to PRESS Ethiopia:

Share