አገር ሻዉ ሚድያ Nation Show Media

አገር ሻዉ ሚድያ Nation Show Media አገር ሻዉ ሚድያ የዜጎች ድምፅ ነዉ። This page is designed and intended to

ህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አሳውቋል።
14/05/2025

ህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አሳውቋል።

ነፍስ ይማር!  | አንጋፋው አርቲስት እንቁሥላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ተና...
19/01/2025

ነፍስ ይማር!

| አንጋፋው አርቲስት እንቁሥላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

ቡና የምታፈላበት ስቲም ፈንድቶ ሁለት ዓይኗን ያሳጣት ወጣት፣ ታደጉኝ ስትል ተማፅናለች  ትዕግስት ላቀ ታደለ ትባላለች። ተወልዳ ያደገችዉ በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ ደብረ ዘይት ኩችት ...
01/11/2024

ቡና የምታፈላበት ስቲም ፈንድቶ ሁለት ዓይኗን ያሳጣት ወጣት፣ ታደጉኝ ስትል ተማፅናለች

ትዕግስት ላቀ ታደለ ትባላለች። ተወልዳ ያደገችዉ በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ ደብረ ዘይት ኩችት ቀበሌ ነዉ።
ትዕግስት በ2014 የትምህርት ዘመን በሜዲካል ላብራቶሪ በዲፕሎማ ተመርቃለች። ትእግስት ቤተሰቦቿን የመርዳትና ራሷን የመቻል ህልሟ ከፍተኛ ስለነበረ ከ2015 ዓም ጀምሮ በደብረማርቆስ ከተማ ቀበሌ 03 በተለምዶ አብማ አካባቢ ቡና በማፍላትና በመሸጥ ህይወትን አሃዱ ብላ ጀመረች።

ትእግስት ህይወቴ ይቀይራል ያለችዉ የቡና ማፍላት ስራ ለዓይነስዉርነት ዳረጋት።

ነገሩ እንዲህ ነዉ። ትእግስት እንደተለመደዉ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም እንደወትሮዉ ሁሉ ቡናዋን በማፍላት ደምበኞቿን ለማስተናገድ ደፋ ቀና እያለች ነዉ። ደምበኞችም ቡና ለመጠጣት ወንበራቸዉን ላይ ቁጭ ብለዉ ይጠባበቃሉ። ቡናዉን አፍልታ ለመቅዳት ጎንበስ እንዳለች ቡና ያፈላችበት ስቲም ፈንድቶ በአይኖቿ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ።

ቡና ለመጠጣት የተቀመጡ ወጣቶች ተሸክመዉ ወደ ሆስፒታል ተሯሯጡ። ከግራና ቀኝ አይኖቿ መካከል ማለትም ከአፍንጫዋ ከፍ ብሎ የማያቋርጥ ደም ይፈሳል።

የደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ሙያተኞችና የአመራሮች ምስጋና ይግባቸዉና አስታማሚ የሌላትንና በጎ ፈቃደኞች ያደረሷትን ወጣት የነጻ ህክምና እንድታገኝ በማድረግ ደሙ እንዲቆም፤ ጉዳት የደረሰበት አይኗ እንዲታከም ቢያደርጉም ሁለቱም አይኖቿን ብርሃን መመለስ አልተቻለም።

የደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ከግራና ቀኝ አይኖቿ መካከል ማለትም ከአፍንጫዋ ከፍ ብሎ ያለዉ አጥንት በመሰበሩ ለጥበበ ጊዮን ሆስፒታል ሪፈር ብሏታል።

ትእግስት ራሷን በራሷ የምታስተዳድር በመሆኗ ለህክምና የሚሆን ገንዘብ ስለሌላት ደጋግ ኢትዮጵያዊያንን እርዳታ ጠይቃለች።

ትእግስት ''የዓይኔን ብርሃን መመለስ እንኳን ባይቻል የሳሳሁላት ህይወቴ ታደጉኝ'' ስትል እየተማጸነች ነዉ።

✅ ትእግስትን ማግኘት ለምትፈልጉ በ0947890066 ማግኘት የምትችሉ ሲሆን
✅ ገንዘብ ማገዝ ለምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትእግስት ላቀ ታደለ በሚል በተከፈተዉ የሂሳብ ቁጥር 1000657479188 እንድትረዷት በፈጣሪ ስም ትጠይቃለች።

ማገዝ እንኳን ባይችሉ ለሌሎች ያጋሩ

01/08/2024

😢ልጃችንን ከተሳለ ካራ ወገን አትርፉልን😢
===========🤲=========
ወንድማችን ታምራት ተስፋዬ ይባላል። በፓዊ ወረዳ መንደር 4 ቀጠና ሁለት መድህን ቀበሌ ከአባቱ ከአቶ ተስፋዬ ላፊቮና ወ/ሮ ኡርሶንጎ እና ከአባቱ ከአቶ ተስፋዬ ላፌቮ በዚሁ ቀበሌ ተወለደ። ወንድማችን እንደማንኛውም ልጅ ተምሮ ትምህርቱን ጨረሰ። በመቀጠልም በቀን ስራ ጭቃ በማቡካት፣ ጫማ በመጥረግ፣ ቋጠሮና መሰል የጉልበት ስራዎችን እየሰራ የደከሙ ወለጆቹን ጦረ።
ሆኖም ግን ሊቀይራቸው ባለመቻሉ እራሱን ለመቀየር በግልገል በለስ ሀይሉ ኮሌጅ ሶስት አመት በመከታተል በጥሩ ውጤት ተመረቀ።
ሆኖም የድሃውን ልጅ ማን ይፈልገው😢ማንም! ሁሉም ሸሸው፤ እራቀው። ቀጠለ... የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ረዳት በመሆን በፓዊና በሌላ ቦታዎች ለ4 ዓመት ሰራ በመቀጠልም ቁርሱንና እራቱን እየቀጣ በአሸናፊ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ የህዝብ መንጃ ፍቃድ አወጣ።
አሁንም ሰው ከሌለህ ማን ይቀጥርሃል? መኪናውንስ አምኖ ይሰጣል😢 አወ ከባድ ነው።
አሁንም ተስፋ አልቆረጠም ወንድማችን ህይወቱን ቀጠለ.... እየሰራ ቤተሰቦቹን ከሸራ ቤት ወደ 10 ዚንጎ ቆርቆሮ ቤት አሸጋገረ። ለሱ ግን ህይወት በፍጹም ልትመቸው አልቻለችም።
በመጨረሻም ተስፋ ሲቆርጥ ልክ እንደ ሌሎች ወደ ስደት መሄድን መረጠ መጋቢት 6 ከቤቱ ወጣ። ግንቦት 3 ጀቡቲ እንደደረሰ አሳወቀን "ከዚህ በኋላም አምላክ ሲፈቅድ እንገናኛለን ብሎን ስልኩን ዘጋ።" ይሄው ወር አለፈው። ሰሞኑን ግን አብሮት በሄደው ጓደኛው በየመን በርሃ ሲያቋረጥ እንደታፈነ ተነገረን።
ወገኖቻችን እኛ ሀቅም የለንም እኔ እናቱ ውሃ ለጠላ ቤቶች እቀዳለሁ😢 ደረቆት እቆላለሁ። አባቱም እንጨት እየለቀመ ይሸጣል። ይሄው ሁለት ወሩ ጤና ነስቶት እቤት መዋል ከጀመረ ወገኖቼ እናንተ ካልረዳችሁን ታምራትን ማግኘት አልችልም እባካችሁ እርዱኝ ትለናለች ወላጅ እናቱ ወ/ሮ በቀለች ኡርሶንጎ🤲
ይህንን ወንድማችንን በማገዝ ወንድማዊ ግዴታዎን ይወጡ በእህቱ በCBE 1000625594263 ታደለች ተስፋዬ በማለት ይገዙ🤲 አወ ይህንን ለቤተሰቡ አሳቢ ወጣት ለካራ እራት እንዳይሆን ከወዲሁ እንረባረብ ወገኖቻችን🤲
Mitiku Essayas
****ሼር ሼር ሼር ለቅኖች አድርሱልኝ*****

This is unfair, unjust " ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እንከፍላለን " - ካውንስሉበኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ከርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ የቢሾፍቱ ከ...
11/07/2024

This is unfair, unjust
" ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እንከፍላለን " - ካውንስሉ

በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ከርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ኢ-ህገ መንግስታዊ ጥሰት እየፈጸመ እንደሆነ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል አሳወቀ።

ድርጊቱን በመቃወምም መግለጫ አውጥቷል።

ካውንስሉ ፤ የኩሪፍቱ ማዕከል በህጋዊ መንገድ ለቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ ሰነድ ያለው ይዞታ መሆኑን ገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ግን ከቤተ ክርስቲያኒቱን ቦታ ላይ 40 ሺህ ካሬ ሜትር የሚሆነውን በኃይል ለሁለት ለግለሰቦች በመስጠት ኢ ህገመንግስታዊ በደል እንደፈጸመ ጠቁሟል።

ይህንን ጉዳይ አስመልከቶ ከዚህ ቀደም ቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርባ ፍርድ ቤት ቦታው የቃለ ሕይወት ይዞታ መሆኑን ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።

የከተማ አስተዳደሩ የግንባታን ሂደት ሆን ብሎ እያስተጓጎለ ስለነበረ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ለፌደራል መንግስት ቀርቦ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየታየ ባለበት ሁኔታ ትላንት ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ የቤተ ከርስቲያቱ ይዞታ ውስጥ ወታደሮችን እና የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችን ይዞ በመግባት ችካል በማስቀመጥ የቤተ ከርስቲያኒቱን ይዞታ ለግለሰብ በማስተላለፍ ህገ ወጥ ተግባር እንደፈጸመ ካውንስሉ በይፋ አሳውቋል።

ሁኔታው ከባድ እና በወንጌላውያን አምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ ሐይማኖታዊ ጥላቻ ባላቸው ግለሰቦች የተቀነባበረ እንደሆነ ካውንስሉ አመልክቷል።

ጥያቄው ልማት ከሆነ ለምን ቤተ ክርስቲያኒቱ እንድታለማ ቅድሚያ አይሰጣትም ? የሚለው ሐሳብ ላይ መግባባት ኖሮ ቤተ ከርስቲያኒቱ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ሙሉ በሙሉ ጊቢውን ወደ ልማት በመቀየር እየሰራች እንደነበር ተጠቁሟል።

ይህ በሆነት ሁኔታ ነው ለአመታት በይዞታነት የያዘችውን ንብረት በሐይል በመቀማት የተወሰደው።

ካውንስሉ ፤ " የወንጌል አማኞች በዚህ የህልውናችን ጉዳይ ህግ መንግስታዊ መብታችን እስከሚከበር ድረስ ለሚመለከታቸው ለክልሉ እና ለፌደራል መንግስት አካላት ጥያቄያችንን ከማቅረብ ባሻገር ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እንከፍላለን " ሲል አሳውቋል።



የአፋልጉን ተማጽዕኖ😡===========ወጣት ፍቃዱ አሸናፊ ደስታ ይባላል በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል በአዋላጅ ነርስ ሥራ ይሰራ ነበር ዛሬ ሌሊት ከታች የምትመለከቷቸዉን መልዕክቶች በፌስቡክ እን...
09/06/2024

የአፋልጉን ተማጽዕኖ😡
===========
ወጣት ፍቃዱ አሸናፊ ደስታ ይባላል በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል በአዋላጅ ነርስ ሥራ ይሰራ ነበር ዛሬ ሌሊት ከታች የምትመለከቷቸዉን መልዕክቶች በፌስቡክ እንዲሁም በወረቀት አስቀምጦ ተሰዉሯል እስካሁን ጓደኞቹ እየፈለጉት ይገኛሉ ነገር ግን ግለሰቡን ማግኘት እንዳልቻሉ እና የአፋልጉን ተማጽዕኖ ጠይቀዋል! አድራሻዉን ለመጠቆም በዚህ ስልክ ቁጥር መደወል ይቻላል
0922241862

እንኳን ደስ ያለንከእናንተ ደጋግ ወገኖቼ ጋር የጀመርነው በጎ ስራ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ወደ ህጋዊ ተቋም/ፋውንዴሽን ያደገ ስለሆነ እንኳን ደስ አለን እያልኩይህንኑ ስራ በተደራጀ እና በተጠና...
15/04/2024

እንኳን ደስ ያለን
ከእናንተ ደጋግ ወገኖቼ ጋር የጀመርነው በጎ ስራ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ወደ ህጋዊ ተቋም/ፋውንዴሽን ያደገ ስለሆነ እንኳን ደስ አለን እያልኩ

ይህንኑ ስራ በተደራጀ እና በተጠናከረ መልኩ ለመስራት በህጋዊ ተቋም ደረጃ የተመሠረተው ማስተር አብነት ከበደ ፋዉንዴሽን በሁሉም የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በመገኘት አቅመ ደካማና ጧሪ የሌላቸውን እናቶችና አባቶች ከጎዳና ህይወት በማንሳት በቋሚነት ድጋፍ እንዲያገኙ በጽናት ይሰራል።

ይህ ድል የሁላችንም ነዉና በሁሉም ነገር ራሳችሁን ሰጥታችሁ ከጎኔ ለቆማችሁ ዉድ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቼ ፈጣሪ ይስጥልን።

አመሠግናለሁ 🙏

አለመግባባቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ወደ ፈጣሪ መጸለይ ይገባል - የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት***************************************...
17/03/2024

አለመግባባቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ወደ ፈጣሪ መጸለይ ይገባል - የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት
*********************************************
ልዩነቶች እና አለመግባባቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ወደ ፈጣሪ መጸለይ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የንስሐ፣ የምልጃ እና የምስጋና መርሐ -ግብሩ በኢትዮያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እና ወደ ኃላ የማይመለስ እርቅ እንዲፈጠር የወንጌል አማኞች የሚጸልዩበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም መርሐ -ግብሩ ምዕመኑ ለሀገሪቱ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ "ጌታ እንዲረዳው" የሚማልድበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስር ያሉ የተለያዩ ቤተክርስቲያናት መሪዎች፣ አባቶች፣ ዘማሪያን፣ መጋቢዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች የንስሐ፣ የምልጃ እና የምስጋና መርሐ-ግብር ተጀምሯል ***********************************የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች የንስሐ፣ የምልጃ እና የምስ...
17/03/2024

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች የንስሐ፣ የምልጃ እና የምስጋና መርሐ-ግብር ተጀምሯል
***********************************
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች የንስሐ፣ የምልጃ እና የምስጋና መርሐ-ግብር መካሄድ ጀምሯል፡፡

የንስሐ፣ የምልጃ እና የምስጋና መርሐ ግብሩን የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስትያናት ሕብረት ፕሬዚዳንት መጋቢ ጻድቁ አብዶ እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በጸሎት አስጀምረውታል፡፡

ለምን EPA ዘገዬ ?ዛሬ ረፋድ ላይ በድንገት ህይወቱ ማለፉን ኢፕድ ከቤተሰቦቹ ማወቅ ችሏል።አንጋፋው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጠኛ እዮብ ግደይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየአንጋፋው የኢትዮጵያ...
10/03/2024

ለምን EPA ዘገዬ ?
ዛሬ ረፋድ ላይ በድንገት ህይወቱ ማለፉን ኢፕድ ከቤተሰቦቹ ማወቅ ችሏል።
አንጋፋው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጠኛ እዮብ ግደይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አንጋፋው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የዓልዓለም ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እዮብ ግደይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ጋዜጠኛ እዮብ ግደይ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር በአረብኛ ቋንቋ በምትታተመው ዓልዓለም ጋዜጣ ለረጅም አመታት በተለያዩ የሥራ መደቦች አገሩን በታታሪነትና በትጋት አገልግሏል።

ጋዜጠኛ እዮብ ግደይ ህይወቱ እስካለፈበት እለት ድረስም የጋዜጣዋ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሠርቷል።

እዮብ በተለይም ለሙያው ያለው ፍቅርና ክብር ላቅ ያለ በመሆኑ የአገሩን ጥቅምና ክብር የሚያስጠብቁ ልዩ ልዩ ጽሁፎችን በአረቡ ዓለም ጋዜጦች እና ድረገጾች ሳይቀር ማሳተም የቻለ አንጋፋ ጋዜጠኛ ነበር።

ጋዜጠኛ እዮብ ግደይ ዛሬ ረፋድ ላይ በድንገት ህይወቱ ማለፉን ኢፕድ ከቤተሰቦቹ ማወቅ ችሏል።

ጋዜጠኛ እዮብ ግደይ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነበር።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለጋዜጠኛው ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመዶችና የሥራ ባልደረቦቹ መጽናናትን ይመኛል።

መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም

Address

Ethiopia
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አገር ሻዉ ሚድያ Nation Show Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አገር ሻዉ ሚድያ Nation Show Media:

Share