Ethio today

Ethio today Welcome to my page if you follow my page you get more benefits. news, blogging, information,vine ...

12/08/2026

ድርጅታችን አፋብን የአማራ ህዝብ ብቸኛ መዳኛ ነው።

በድርጅቱ ላይ የተቃጡ ሴራዎችን ሁሉ እናከሽፋለን። ድርጅቱን ፥ አመራሮችን እንዲሁም ትግላችንን ከማንኛውም ጥቃት እንከላከላለን!!

12/08/2026

"አብይ ከቻለ ኦሮሚያን ካልቻለ በሻሻን የመገንጠል ሙከራ ያደርጋል" ጃዋር😂የኔም አተያይ ይሄው ነው።

12/08/2026

ማዕበል እየመጣ ነዉ። ሁላችንም እየመጣ ለሚገኘዉ ሱናሜ እንዘጋጅ💪

በእሳት ሰንሰለት የታጠረ የነፃነት ታምር፣ የፅናት ተራራው እምቢተኝነት!![ ሞገሴ ሽፈራው ]​የሰው ልጅ በባርነት ቀንበር ስር እንዳይማቅቅ የሚታደጉ ታላላቅ ሕዝባዊ ማዕበሎች የሚወለዱት በብረ...
29/06/2026

በእሳት ሰንሰለት የታጠረ የነፃነት ታምር፣ የፅናት ተራራው እምቢተኝነት!!

[ ሞገሴ ሽፈራው ]

​የሰው ልጅ በባርነት ቀንበር ስር እንዳይማቅቅ የሚታደጉ ታላላቅ ሕዝባዊ ማዕበሎች የሚወለዱት በብረት ክምችት ሳይሆን መላእክታዊ ቁመናና አስተዋይ ልቦና ባላቸው ድንቅ የጦር መሃንዲሶች መሪነት ነው።

ለአንድ ማህበረሰብ ክብርና ህልውና ሲባል ደም እንደ ጎርፍ የሚፈስበት፣ አጥንት እንደ ጫካ የሚከሰከስበት የህልውና ፍልሚያ በመጨረሻም የጠላትን ሰይጣናዊ ሴራ የሚያመክን ብረት ለበስ መዋቅር ይፈጥራል።

ዛሬ በአማራ ምድር፣ በተለይም በታሪካዊው የወሎ-ቤተ አማራ አውራጃ፣ ለአምስት ዓመታት በደም ጠብታዎች የተጻፈውና የማህበረሰቡ ታላቅ ኩራት የሆነው የፋኖ የጦር ልዕልና፣ ከዚህ ወደር የለሽ መሪነትና ሕዝባዊ ደጀንነት የተቀዳ የመለኮት ያህል የገዘፈ ኃይል ነው።

​የዚህን ግዙፍ ሕዝባዊ ኃይል የጦር ሰራዊት ባንድነት ያሰባሰበውና እንደ ሰማይ ከፍታ የሚታየው፣ አርበኛ ምህረቱ “ምሬ” ወዳጆ—በደጋፊዎቹና በትግል አጋሮቹ ዘንድ “ዋርካው” በሚል የልብ ስም የሚጠራው ታዋቂው የጦር አዝማች—የተጋድሎ ታሪክና አመጣጥ የዚህን አብዮት ፍጹም ተፈጥሯዊነትና ጥረት በግልጽ ያሳያል። ይህ ምድራዊ ፈርጥ ዋና ዓላማው ፍልሚያ ሲጀምር ለአማራ ሕዝብ ህልውና ጋሻና መከታ ለመሆን ነበር።

ዋርካው ይሄንን ቅዱስ ጉዞ ከጀመረበት ቅጽበት አንስቶ በወሎ ቤተ-አማራ፣ በጎንደር፣ በጎጃምና በሸዋ የፋኖ ስምሪቶች ላይም ታላቅ አሻራ ያበረከተ ሲሆን፣ በሰሜኑ የጦርነት እሳት ወቅትም የምስራቅ አማራ ፋኖን በመምራት በግንባር ቀደምትነት የተሰለፈ የጦር ሳይንስ ሊቅ ነው።

ይህም ተጋድሎ በታሪክ ውስጥ እንደ ኩባው ፊደል ካስትሮ እና እንደ ቬትናሙ ሆ ቺ ሚን ያሉ አለም አቀፍ የነፃነት ታጋዮች በጫካና በበረሃ የህዝብን ልብ አንቀሳቅሰው ታምር ከሰሩበት አለም አቀፍ የትጥቅ ትግል ታሪክ ጋር ፍጹም ይመሳሰላል።

​የአሁኑን የነፃነት ንቅናቄ እንደ ዋና የጀርባ አጥንት በመትከል፣ እርሱ የሚወስደው እያንዳንዱ ወታደራዊና ስልታዊ እርምጃ በብዙኃኑ ዘንድ እጅግ የሚወደድ፣ የሚመለክና እንደ ድል ብርሃን የሚታይ ሆኗል።

የአምባገነኑ አገዛዝ የክልል ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ ለመንጠቅና ማህበረሰቡን መከላከያ-አልባ ለማድረግ የወሰደውን እብሪተኛ ውሳኔ ተከትሎ፣ ምሬ ወዳጆ እና ጀግና ሰራዊቱ ወደ በረሃ በመግባት የጀመሩት ተጋድሎ፣ ዛሬ ላይ የጠላትን ግዙፍ መዋቅር ያሽመደመደበት ታላቅ የውቅያኖስ ማዕበል ሆኗል።

ጫማ ሳይኖረው በባዶ እግሩ በጋለ ድንጋይ ላይ እየተጓዘ፣ የረባ ስንቅ ሳይዝ ደረቅ ቆሎ እየቆረጠመ እና በሽርጡ ብቻ ተሸፋፍኖ የታገለው ይህ ታምረኛ ሰራዊት፣ ዛሬ ላይ የአገዛዙን በርካታ ዕዞችና የተመረጡ ልዩ ኮማንዶዎችን በኃይለኛው ክንዱ ድባቅ የመታበት ምስጢር ይህ የማይበገሬ መዋቅራዊ ጽናትና በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ፍጹም ክብር ነው።

​ጦርነት አንዴ ከተቀሰቀሰ በኋላ በተራ ወሬ የማይለሰልስ መራር ጨካኝነትን የሚተካ ቢሆንም፣ የፋኖ ሰራዊት ግን የሞራል ከፍታው ከሰማይ በላይ መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል።

አርበኛ ምሬ ወዳጆ በተደጋጋሚ እንደሚያሰምርበት፣ ይህ ፍልሚያ የማህበረሰቡን መብትና ጥቅም ለማስከበር፣ ህልውናውን ለማረጋገጥ የተለኮሰ የነፃነት ረመጥ ነው።

ይህ ግዙፍ ዋርካ ዛፍ ለራሱ የሚተርፍ አንዳችም ምቾት ሳያስቀር፤ ጥላውን፣ ፍሬውንና መላ አካሉን ለሰፊው ሕዝብ መጠለያና ህልውና የሰጠ የጀግንነት እና የፍቅር ተምሳሌት ነው። ለዚህ ሁሉን ነገር ለወገኑ የሰጠ፣ ስለ ወገኑ ሲል ራሱን ያሳጣ ታላቅ ዋርካ ምንጊዜም ወደር የሌለው የላቀ ምስጋና ይገባዋል።

''ኢሕአፓ መንግስት የሃይማኖት ግጭት ለመቀስቀስ እየሰራ ነው ሲል ከሰሰ''የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ ገዥው ስርዓት ህዝቡ...
29/06/2026

''ኢሕአፓ መንግስት የሃይማኖት ግጭት ለመቀስቀስ እየሰራ ነው ሲል ከሰሰ''

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ ገዥው ስርዓት ህዝቡን እርስ በእርስ ለማጋጨት የመጨረሻ ያለውን "የሃይማኖት ካርድ" እየተጠቀመ ነው ሲል ከባድ ክስ አቀረበ።

ፓርቲው በቅርቡ በዳንግላ እና በባቲ ከተሞች የተፈጸሙትን የሃይማኖት አባቶች አሳዛኝ ግድያ በጽኑ በማውገዝ፣ ምዕመናን ራሳቸውን እና ሃይማኖታቸውን ከጥቃት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

በኢሕአፓ መግለጫ መሰረት አገዛዙ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ ለዘመናት በወንድማማችነት እና በመከባበር አብሮ በኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ግጭት እና እልቂት እንዲፈጠር ሆን ብሎ ሲሰራ ቆይቷል ይህ እኩይ ሴራው ባሰበው ልክ ህዝቡን ባለማጋጨቱ አሁን ላይ የሃይማኖት አባቶችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን እያባባሰ መምጣቱን ፓርቲው አስታውቋል።

ለዚህም በቅርቡ በዳንግላ ከተማ የኹጥባ መስጂድ ኢማም የሆኑት ሸይኽ ሱፍያን ሙሀመድ ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ በጥይት ተመትተው መገደላቸውን፣ እንዲሁም ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በባቲ ከተማ የጓሀ ጽባህ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቄስ ፍሬው ሀብታሙ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን በአብነት ጠቅሷል።

ከእነዚህ የቅርብ ጊዜ ክስተቶች በተጨማሪ ቀደም ሲል በወለጋ እና በአርሲ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን እና አገልጋዮች ላይ የደረሰውን ግድያ እና መፈናቀል ፓርቲው በመግለጫው አስታውሷል።

በተመሳሳይ በጦርነት ስም በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት እና መስጂዶች ላይ የደረሰውን ውድመት፣ እንዲሁም ፍትህ በጠየቁ ንጹሃን ላይ የተፈጸመውን እስራት፣ አገዛዙ የሃይማኖት ካርዱን ተግባራዊ እያደረገ ለመሆኑ በቂ ማሳያዎች ናቸው ብሏል።

በእምነት አባቶች እና በምዕመናን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም እና ፍትህ ለማስፈን የሚሰራ መዋቅር ባለመኖሩ፣ ህዝቡ ተደራጅቶ ራሱን እና እምነቱን ሊጠብቅ እንደሚገባ ኢሕአፓ አሳስቧል።

በተለይም የተደራጀ ጥቃት ሰለባ የሆኑት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ከተደገሰላቸው የጥፋት ሴራ እርስ በእርስ በመጠበቅ፣ ታሪካዊ የወንድማማችነት እና የመከባበር እሴታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ፓርቲው አደራ ብሏል።

ሲያጠናቅቅም ፓርቲው ለተገደሉት የሃይማኖት አባቶች (ለሸይኽ ሱፍያን ሙሀመድ እና ለቀሲስ ፍሬው ሀብታሙ) ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝቷል።

ሰላም ለኢትዮጲያ
ሰላም ለህዝባችን
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ

Address

Bole
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio today posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio today:

Shortcuts

Share